Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 * - Mục lục các bản dịch


Ý nghĩa nội dung Chương: Al-'Araf   Câu:
وَلَقَدۡ جِئۡنَٰهُم بِكِتَٰبٖ فَصَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ عِلۡمٍ هُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
52. ከእውቀት ጋር የዘረዘርነው የሆነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ህዝቦች መመሪያና እዝነት ሲሆን አመጣንላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأۡوِيلَهُۥۚ يَوۡمَ يَأۡتِي تَأۡوِيلُهُۥ يَقُولُ ٱلَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَآءَ فَيَشۡفَعُواْ لَنَآ أَوۡ نُرَدُّ فَنَعۡمَلَ غَيۡرَ ٱلَّذِي كُنَّا نَعۡمَلُۚ قَدۡ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
53. የዛቻውን ፍጻሜዉን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም):: ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን ግን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት መጥተዋል። ለእኛስ ያማልዱን ዘንድ አማላጆች አሉን? ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው የተለየ ስራ እንድንሰራ ዘንድ ዕድሉ ይሰጠናልን?» ይላሉ:: በእርግጥም ራሳቸውን ይከስራሉ:: ይቀጥፉት የነበረው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ያገኙታል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُغۡشِي ٱلَّيۡلَ ٱلنَّهَارَ يَطۡلُبُهُۥ حَثِيثٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتِۭ بِأَمۡرِهِۦٓۗ أَلَا لَهُ ٱلۡخَلۡقُ وَٱلۡأَمۡرُۗ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
54. (ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱدۡعُواْ رَبَّكُمۡ تَضَرُّعٗا وَخُفۡيَةًۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِينَ
55. ጌታችሁን ተናንሳችሁና ተዋርዳችሁ በድብቅ ለምኑት:: እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بَعۡدَ إِصۡلَٰحِهَا وَٱدۡعُوهُ خَوۡفٗا وَطَمَعًاۚ إِنَّ رَحۡمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٞ مِّنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
56. ምድር ከተበጀች በኋላ አታበላሿት:: አላህን ፈርታችሁና ከጅላችሁ ተገዙት:: የአላህ እዝነት ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ ቅርብ ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَهُوَ ٱلَّذِي يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشۡرَۢا بَيۡنَ يَدَيۡ رَحۡمَتِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَقَلَّتۡ سَحَابٗا ثِقَالٗا سُقۡنَٰهُ لِبَلَدٖ مَّيِّتٖ فَأَنزَلۡنَا بِهِ ٱلۡمَآءَ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِۚ كَذَٰلِكَ نُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
57. አላህ ያ ንፋሶችን ከዝናብ በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው:: ከባዶችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ሆነ አገር እንነዳዋለን:: በእነርሱም ውሃን እናወርዳለን:: እናም ከፍሬዎች ሁሉ በእነርሱ እናወጣለን:: ልክ እንደዚሁ ሙታንን ከመቃብር እናስወጣለን:: ይህን የምንለው ትገነዘቡ ዘንድ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Al-'Araf
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 - Mục lục các bản dịch

穆罕默德·宰尼·泽海伦丁,由非洲学院发行

Đóng lại