Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格。 * - 译解目录

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

含义的翻译 章: 优素福   段:
فَلَمَّا ذَهَبُواْ بِهِۦ وَأَجۡمَعُوٓاْ أَن يَجۡعَلُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ لَتُنَبِّئَنَّهُم بِأَمۡرِهِمۡ هَٰذَا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
እርሱንም ይዘውት በሄዱና በጉድጓዱ ጨለማ አዘቅት ውስጥ እንዲያደርጉት በቆረጡ ጊዜ (ሐሳባቸውን ፈጸሙበት)፡፡ ወደእርሱም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ ይህንን ሥራቸውን በእርግጥ ትነግራቸዋለህ ስንል ላክንበት፡፡
阿拉伯语经注:
وَجَآءُوٓ أَبَاهُمۡ عِشَآءٗ يَبۡكُونَ
አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት፡፡
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّا ذَهَبۡنَا نَسۡتَبِقُ وَتَرَكۡنَا يُوسُفَ عِندَ مَتَٰعِنَا فَأَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُؤۡمِنٖ لَّنَا وَلَوۡ كُنَّا صَٰدِقِينَ
«አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡ ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡ አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም» አሉ፡፡
阿拉伯语经注:
وَجَآءُو عَلَىٰ قَمِيصِهِۦ بِدَمٖ كَذِبٖۚ قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٞۖ وَٱللَّهُ ٱلۡمُسۡتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ
በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ፡፡ (አባታቸው) «አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ ስለዚህ መልካም ትዕግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው» አለ፡፡
阿拉伯语经注:
وَجَآءَتۡ سَيَّارَةٞ فَأَرۡسَلُواْ وَارِدَهُمۡ فَأَدۡلَىٰ دَلۡوَهُۥۖ قَالَ يَٰبُشۡرَىٰ هَٰذَا غُلَٰمٞۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَٰعَةٗۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ
መንገደኞችም መጡ፡፡ ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ፡፡ አኮሊውንም (ወደ ጉድጓዱ) ሰደደ «የምስራች! ይህ ወጣት ልጅ ነው» አለ፡፡ ሸቀጥ አድርገውም ደበቁት፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
阿拉伯语经注:
وَشَرَوۡهُ بِثَمَنِۭ بَخۡسٖ دَرَٰهِمَ مَعۡدُودَةٖ وَكَانُواْ فِيهِ مِنَ ٱلزَّٰهِدِينَ
በርካሽ ዋጋም በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት፡፡ በእርሱም ከቸልተኞቹ ነበሩ፡፡
阿拉伯语经注:
وَقَالَ ٱلَّذِي ٱشۡتَرَىٰهُ مِن مِّصۡرَ لِٱمۡرَأَتِهِۦٓ أَكۡرِمِي مَثۡوَىٰهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدٗاۚ وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلِنُعَلِّمَهُۥ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِۚ وَٱللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِۦ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «መኖሪያውን አክብሪ፡፡ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አላት፡፡ እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው፡፡ አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥٓ ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 优素福
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格。 - 译解目录

穆罕默德·萨迪克和穆罕默德·塔尼·哈比卜翻译。由拉瓦德翻译中心负责开发,附上翻译原文以便发表意见、评价和持续改进。

关闭