Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 易卜拉欣   段:

ኢብራሂም

الٓرۚ كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ إِلَيۡكَ لِتُخۡرِجَ ٱلنَّاسَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ بِإِذۡنِ رَبِّهِمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ፤ ምስጉን ወደ ሆነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው::
阿拉伯语经注:
ٱللَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَوَيۡلٞ لِّلۡكَٰفِرِينَ مِنۡ عَذَابٖ شَدِيدٍ
2. ወደ እዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ወደ ሆነው ጌታ ወደ አላህ መንገድ (ታወጣ ዘንድ ):: ለከሓዲያን ሁሉ ከብርቱ ቅጣት ወዮላቸው::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ يَسۡتَحِبُّونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا عَلَى ٱلۡأٓخِرَةِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبۡغُونَهَا عِوَجًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ضَلَٰلِۭ بَعِيدٖ
3. እነዚያ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ የሚወዱና ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚያግዱ፤ መጥመሟንም (ደካማ ጎኗን) የሚፈልጓት ናቸው:: እነዚያ በሩቅ ስህተት ውስጥ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا بِلِسَانِ قَوۡمِهِۦ لِيُبَيِّنَ لَهُمۡۖ فَيُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
4. ከመልዕክተኞች ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም:: አላህ የሚፈልገውንም ያጠምማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነውና::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنۡ أَخۡرِجۡ قَوۡمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرۡهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٖ
5. ሙሳን ወገኖችህን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ:: የአላህንም ቀናት አስገንዝባቸው በማለት በተዓምራታችን አጠናክረን በእርግጥ ላክነው:: በዚህ ውስጥ በብዙ ታጋሽና በብዙ አመስጋኝ ለሆኑት ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተዓምራት አሉበት::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 易卜拉欣
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭