Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 伊斯拉仪   段:
مَّن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡعَاجِلَةَ عَجَّلۡنَا لَهُۥ فِيهَا مَا نَشَآءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلۡنَا لَهُۥ جَهَنَّمَ يَصۡلَىٰهَا مَذۡمُومٗا مَّدۡحُورٗا
18. ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሁሉ ለእርሱ ከእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ብቻ ለምንፈልገውም ብቻ እናስቸኩልለታለን:: ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል:: ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል።
阿拉伯语经注:
وَمَنۡ أَرَادَ ٱلۡأٓخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعۡيَهَا وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ كَانَ سَعۡيُهُم مَّشۡكُورٗا
19. የመጨረሻይቱን ዓለም የፈለገ እና እርሱ አማኝ ሆኖ ለእርሷ ተገቢ የሆነን ሥራ የሠራ ደግሞ እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል::
阿拉伯语经注:
كُلّٗا نُّمِدُّ هَٰٓؤُلَآءِ وَهَٰٓؤُلَآءِ مِنۡ عَطَآءِ رَبِّكَۚ وَمَا كَانَ عَطَآءُ رَبِّكَ مَحۡظُورًا
20. ሁሉንም እነዚህንም እነዚያንም ከጌታህ ስጦታ በዚህ ዓለም እንጨምርላቸዋለን:: የጌታህም ስጦታ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም::
阿拉伯语经注:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ فَضَّلۡنَا بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ وَلَلۡأٓخِرَةُ أَكۡبَرُ دَرَجَٰتٖ وَأَكۡبَرُ تَفۡضِيلٗا
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳስበለጥን ተመልከት:: የመጨረሻይቱም ሀገር በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የላቀች ናት::
阿拉伯语经注:
لَّا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقۡعُدَ مَذۡمُومٗا مَّخۡذُولٗا
22. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና::
阿拉伯语经注:
۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنًاۚ إِمَّا يَبۡلُغَنَّ عِندَكَ ٱلۡكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوۡ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفّٖ وَلَا تَنۡهَرۡهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوۡلٗا كَرِيمٗا
23. (የሰው ልጅ ሆይ!) ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ባንተ ዘንድ ሆነው ከወላጆችህ አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ!» እንኳን አትበላቸው:: አትገላምጣቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ቃል ብቻ ተናገራቸው::
阿拉伯语经注:
وَٱخۡفِضۡ لَهُمَا جَنَاحَ ٱلذُّلِّ مِنَ ٱلرَّحۡمَةِ وَقُل رَّبِّ ٱرۡحَمۡهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرٗا
24. (ልጅ ሆይ!) ለሁለቱም የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው። «ጌታዬ ሆይ! በሕጻንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ለእነርሱም እዘንላቸው።» በልም።
阿拉伯语经注:
رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمۡۚ إِن تَكُونُواْ صَٰلِحِينَ فَإِنَّهُۥ كَانَ لِلۡأَوَّٰبِينَ غَفُورٗا
25. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው:: ታዛዦችም ብትሆኑ ወይም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች ሁሉ መሓሪ ነው::
阿拉伯语经注:
وَءَاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِ وَلَا تُبَذِّرۡ تَبۡذِيرًا
26. (የሰው ልጅ ሆይ!) ለዝምድና ባለቤት ሁሉ ተገቢ መብቱን ስጥ:: ለምስኪንና ለመንገደኛም እንዲሁ መብቱን ስጥ:: (በሁሉም ነገር ላይ) ማባከንንም አታባክን::
阿拉伯语经注:
إِنَّ ٱلۡمُبَذِّرِينَ كَانُوٓاْ إِخۡوَٰنَ ٱلشَّيَٰطِينِۖ وَكَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لِرَبِّهِۦ كَفُورٗا
27. አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና:: ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 伊斯拉仪
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭