Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 拜格勒   段:
وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ كُلَّمَا رُزِقُواْ مِنۡهَا مِن ثَمَرَةٖ رِّزۡقٗا قَالُواْ هَٰذَا ٱلَّذِي رُزِقۡنَا مِن قَبۡلُۖ وَأُتُواْ بِهِۦ مُتَشَٰبِهٗاۖ وَلَهُمۡ فِيهَآ أَزۡوَٰجٞ مُّطَهَّرَةٞۖ وَهُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑትንና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መሆኑን አብስራቸው:: በእርሷም ፍራፍሬ በተለገሱ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) «ይህማ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው።» ይላሉ:: (እርሱ ተመሳሳይ ሆኖ ይሰጣቸዋል) ለእነርሱም በውስጧ ንጹህ ሚስቶች አሏቸው:: እነርሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَسۡتَحۡيِۦٓ أَن يَضۡرِبَ مَثَلٗا مَّا بَعُوضَةٗ فَمَا فَوۡقَهَاۚ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فَيَعۡلَمُونَ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡۖ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَيَقُولُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۘ يُضِلُّ بِهِۦ كَثِيرٗا وَيَهۡدِي بِهِۦ كَثِيرٗاۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِۦٓ إِلَّا ٱلۡفَٰسِقِينَ
26. አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝም ትሁን ከሷም በላይ የሆነን ነገር ምሳሌ ከማድረግ አያፍርም። እነዚያማ ያመኑት ምሳሌው ከጌታቸው የተነገረ እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: እነዚያ የካዱ ግን «አላህ በዚህ አባባል ምንን ምሳሌ ፈልጎበት ነው?» ይላሉ:: አላህ በምሳሌው ብዙዎችን ያሳስታል:: በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል:: በእርሱም አመጸኞችን እንጂ ሌላን አያሳስትም::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهۡدَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مِيثَٰقِهِۦ وَيَقۡطَعُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
27. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኃላ የሚያፈርሱ፤ እንዲቀጠልም አላህ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድር ላይ ሁከት የሚፈጥሩ ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::
阿拉伯语经注:
كَيۡفَ تَكۡفُرُونَ بِٱللَّهِ وَكُنتُمۡ أَمۡوَٰتٗا فَأَحۡيَٰكُمۡۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يُحۡيِيكُمۡ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
28. (እናንተ ከሓዲያን ሆይ!) ሙታን የነበራችሁትን ሕያው ያደረጋችሁ፤ ከዚያም የሚገድላችሁ፤ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁና ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትሆኑ እንዴት በአላህ ትክዳላችሁ!
阿拉伯语经注:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
29. አላህ ያ በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሲል የፈጠረ ጌታ ነው:: ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበና ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና፡፡
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 拜格勒
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭