Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 穆米尼奈   段:

አል-ሙዕሚኑን

قَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ
1.ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ተሳካላቸው)::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي صَلَاتِهِمۡ خَٰشِعُونَ
2. እነዚያም በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሆኑት፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنِ ٱللَّغۡوِ مُعۡرِضُونَ
3. እነዚያም ከመጥፎ ነገር ሁሉ የራቁ::
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ
4. እነዚያም ዘካን በአግባቡ ሰጪዎች፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ
5. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤
阿拉伯语经注:
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ
6. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ሴት ባሪያዎች ላይ ካልሆነ በቀር (ብልቶቻቸውን ጠባቂ የሆኑት)፤ እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና።
阿拉伯语经注:
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ
7. ከዚህ ሌላ በሆነ መንገድ (ስሜታቸዉን ሊያረኩ) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ የአላህን ወሰን አላፊዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ
8. እነዚያም ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
9. እነዚያም በስግደቶቻቸው ላይ (ሁለንተናዋን) የሚጠባበቁ የሆኑት
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡوَٰرِثُونَ
10. እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡفِرۡدَوۡسَ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
11. እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን) የሚወርሱ ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٖ مِّن طِينٖ
12. በእርግጥ ሰውን (አደምን) ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ جَعَلۡنَٰهُ نُطۡفَةٗ فِي قَرَارٖ مَّكِينٖ
13. ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ خَلَقۡنَا ٱلنُّطۡفَةَ عَلَقَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡعَلَقَةَ مُضۡغَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡمُضۡغَةَ عِظَٰمٗا فَكَسَوۡنَا ٱلۡعِظَٰمَ لَحۡمٗا ثُمَّ أَنشَأۡنَٰهُ خَلۡقًا ءَاخَرَۚ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحۡسَنُ ٱلۡخَٰلِقِينَ
14. ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ስጋ አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጭዋንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን:: አጥንቶችንም ስጋን አለበስናቸው። ከዚያም (በዉስጡ ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው:: ከቅርፅ ሰጪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ከሁሉ ላቀ።
阿拉伯语经注:
ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ
15. (ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ
16. ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ
17. በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን:: ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም::
阿拉伯语经注:
وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَسۡكَنَّٰهُ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابِۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ
18. ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን:: በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው:: እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን::
阿拉伯语经注:
فَأَنشَأۡنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ لَّكُمۡ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ
19. በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች አትክልቶችን ለእናንተ አስገኘንላችሁ:: በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَشَجَرَةٗ تَخۡرُجُ مِن طُورِ سَيۡنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهۡنِ وَصِبۡغٖ لِّلۡأٓكِلِينَ
20. ከሲና ተራራም የምትወጣ ዛፍ በቅባትና ለበይዎች መባያ በሚሆን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةٗۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ
21. (ሰዎች ሆይ!) እናንተም በግመል፤ በከብት በፍየልና በበግ መገምገሚያ አላችሁ:: በሆዶችዋ ውስጥ ካለው ወተት እናጠጣችኋለን:: ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ
22. በእርሷም ላይና በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
23. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው። ወዲያዉም «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን?» አላቸው።
阿拉伯语经注:
فَقَالَ ٱلۡمَلَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيۡكُمۡ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةٗ مَّا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ
24. ከህዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል። አላህም ቢፈልግ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር። ይህንንም የሚለውን በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም።
阿拉伯语经注:
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلُۢ بِهِۦ جِنَّةٞ فَتَرَبَّصُواْ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٖ
25. «እርሱ እብደት ያለበት ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: በእርሱም እስከ ጊዜው ድረስ ተጠባበቁ።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ
26. ኑሕም «ጌታዬ ሆይ! ስለ አስተባበሉኝ እርዳኝ።» አለ።
阿拉伯语经注:
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ أَنِ ٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسۡلُكۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ مِنۡهُمۡۖ وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ
27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና።
阿拉伯语经注:
فَإِذَا ٱسۡتَوَيۡتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلۡفُلۡكِ فَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
28. አንተም አብረውህ ካሉት ፍጡሮች ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ በል: «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከበደለኛ ህዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው።
阿拉伯语经注:
وَقُل رَّبِّ أَنزِلۡنِي مُنزَلٗا مُّبَارَكٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ
29. «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የሆነን ማውረድ አውርደኝ:: አንተም ከአደላዳዮች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል።
阿拉伯语经注:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ وَإِن كُنَّا لَمُبۡتَلِينَ
30. በዚህ ውስጥ ለሃያልነታችን አያሌ ተዓምራት አሉበት:: እነሆ እኛ (የኑሕን ሰዎች) ፈታኞች ነበርን::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ
31. ከዚያ ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::
阿拉伯语经注:
فَأَرۡسَلۡنَا فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
32. በውስጣቸዉም ከእነርሱ የሆኑን መልዕክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን።
阿拉伯语经注:
وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَتۡرَفۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يَأۡكُلُ مِمَّا تَأۡكُلُونَ مِنۡهُ وَيَشۡرَبُ مِمَّا تَشۡرَبُونَ
33. ከህዝቦቹም እነዚያ የካዱት ሰዎች በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ህይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። ከምትበሉት ምግብ ይበላል፤ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል።
阿拉伯语经注:
وَلَئِنۡ أَطَعۡتُم بَشَرٗا مِّثۡلَكُمۡ إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ
34. «የናንተው ብጤያችሁ የሆነን ሰው ብትታዘዙ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናችሁ።
阿拉伯语经注:
أَيَعِدُكُمۡ أَنَّكُمۡ إِذَا مِتُّمۡ وَكُنتُمۡ تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخۡرَجُونَ
35. «‹እናንተ ሞታችሁ አፈርና አጥንቶችም በሆናችሁ ጊዜ እናንተ ከመቃብር ትወጣላችሁ› በማለት ያስፈራራችኋልን?
阿拉伯语经注:
۞ هَيۡهَاتَ هَيۡهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ
36. «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ከእውነት ራቀ፤ በጣም ራቀ
阿拉伯语经注:
إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ
37. «እርሷ (ህይወት) ማለት ቅርቢቱ ህይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን። ህያዉም እንሆናለን። እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም" (አሉ)።
阿拉伯语经注:
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا وَمَا نَحۡنُ لَهُۥ بِمُؤۡمِنِينَ
38. «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: እኛም በእርሱ አማኞች አይደለንም።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ
39. መልዕክተኛዉም «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ በእነርሱ ላይ እርዳኝ።» አለ።
阿拉伯语经注:
قَالَ عَمَّا قَلِيلٖ لَّيُصۡبِحُنَّ نَٰدِمِينَ
40. አላህም «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥፋታቸው በእርግጥ ተጸጻቾች ይሆናሉ።» አለው።
阿拉伯语经注:
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ بِٱلۡحَقِّ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ غُثَآءٗۚ فَبُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
41. ወዲያዉም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፤ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው:: ለበደለኞች ህዝቦችም ከእዝነት መራቅ ተገባቸው::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قُرُونًا ءَاخَرِينَ
42. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::
阿拉伯语经注:
مَا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ
43. ማንኛይቱም ህዝብ ጊዜዋን አትቀድምም:: ከጊዜያቸዉም አይቆዩምም::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا تَتۡرَاۖ كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةٗ رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُۖ فَأَتۡبَعۡنَا بَعۡضَهُم بَعۡضٗا وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَۚ فَبُعۡدٗا لِّقَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ
44. ከዚያም መልዕክተኞቻችንን በተከታታይ ላክን፤ ማንኛይቱንም ህዝብ መልእክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት። ከፊላቸውንም በከፊሉ በጥፋት አስከታተልን፤ ወሬዎችም አደረግናቸው፤ ለማያምኑም ህዝቦች ከእዝነታችን መራቅ ተገባቸው።
阿拉伯语经注:
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ
45. ከዚያ ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችንና በግልጽ ማስረጃ ላክናቸው::
阿拉伯语经注:
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا عَالِينَ
46. ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ ላክናቸው። ድሮውም የኮሩና የተንበጣረሩ ህዝቦችም ነበሩ።
阿拉伯语经注:
فَقَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لِبَشَرَيۡنِ مِثۡلِنَا وَقَوۡمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ
47. «ህዝቦቻቸው ለኛ ተገዢዎች ሆነው ሳሉ ብጤያችን ለሆኑ ሰዎች እናምናለን?» አሉ።
阿拉伯语经注:
فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡلَكِينَ
48. አስተባበሏቸዉም፤ ከጠፊዎችም ሆኑ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ
49. ሙሳንም ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው::
阿拉伯语经注:
وَجَعَلۡنَا ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةٗ وَءَاوَيۡنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبۡوَةٖ ذَاتِ قَرَارٖ وَمَعِينٖ
50. የመርየምን ልጅ ዒሳንና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው:: የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ሆነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው::
阿拉伯语经注:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُواْ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٞ
51. እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ሁሉ ብሉ:: በጎ ስራንም ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝና::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱتَّقُونِ
52. ይህችም በአንድ አምላክ የማመን ህግጋት አንድ መንገድ ስትሆን ሃይማኖታችሁ ናት:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ::
阿拉伯语经注:
فَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ زُبُرٗاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ
53. ከዚያም ተከታዮቻቸው ሃይማኖታቸውን በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፤ ህዝቦች ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው::
阿拉伯语经注:
فَذَرۡهُمۡ فِي غَمۡرَتِهِمۡ حَتَّىٰ حِينٍ
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስከ ጊዜያቸዉም ድረስ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው::
阿拉伯语经注:
أَيَحۡسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٖ وَبَنِينَ
55. ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን?
阿拉伯语经注:
نُسَارِعُ لَهُمۡ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ بَل لَّا يَشۡعُرُونَ
56. በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው እንደሆነ ያስባሉን? አይደለም፤ ይህ ሁሉ እነርሱን ለማዘናጋት መሆኑን አያውቁም።
阿拉伯语经注:
إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ خَشۡيَةِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ
57. እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የሆኑት፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ
58. እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራት የሚያምኑት፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمۡ لَا يُشۡرِكُونَ
59. እነዚያም በጌታቸው የማያጋሩት፤
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِينَ يُؤۡتُونَ مَآ ءَاتَواْ وَّقُلُوبُهُمۡ وَجِلَةٌ أَنَّهُمۡ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ رَٰجِعُونَ
60. እነዚያም የሚሰጡትን ነገር ሁሉ እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡ ናቸው::
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَهُمۡ لَهَا سَٰبِقُونَ
61. እነዚያ በመልካም ስራዎች ይጣደፋሉ:: እነርሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ وَلَدَيۡنَا كِتَٰبٞ يَنطِقُ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
62. ማንኛይቱንም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድዳትም:: እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አለ:: እነርሱም አይበደሉም::
阿拉伯语经注:
بَلۡ قُلُوبُهُمۡ فِي غَمۡرَةٖ مِّنۡ هَٰذَا وَلَهُمۡ أَعۡمَٰلٞ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمۡ لَهَا عَٰمِلُونَ
63. በእውነቱ ከሓዲያን ልቦቻቸው ከዚህ መጽሐፍ በዝንጋታ ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱም ከዚህ ሌላ እነርሱ ለእርሷ ሰሪዎችዋ የሆኑ መጥፎ ስራዎች አሏቸው::
阿拉伯语经注:
حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذۡنَا مُتۡرَفِيهِم بِٱلۡعَذَابِ إِذَا هُمۡ يَجۡـَٔرُونَ
64. ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ::
阿拉伯语经注:
لَا تَجۡـَٔرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ
65. (ይባላሉም) «ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱምና።
阿拉伯语经注:
قَدۡ كَانَتۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ تَنكِصُونَ
66. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር። እናንተ ግን በተረከዞቻችሁ ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበር።
阿拉伯语经注:
مُسۡتَكۡبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرٗا تَهۡجُرُونَ
67. «በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ሆናችሁ (ትመለሱ ነበር)።» ይባላሉ።
阿拉伯语经注:
أَفَلَمۡ يَدَّبَّرُواْ ٱلۡقَوۡلَ أَمۡ جَآءَهُم مَّا لَمۡ يَأۡتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
68. የቁርኣንን ንግግርን አያስተነትኑምን? ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?
阿拉伯语经注:
أَمۡ لَمۡ يَعۡرِفُواْ رَسُولَهُمۡ فَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ
69. ወይስ መልዕክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ በእርሱ ከሓዲያን ናቸውን?
阿拉伯语经注:
أَمۡ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةُۢۚ بَلۡ جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ وَأَكۡثَرُهُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ
70. ወይስ «በእርሱ ዕብደት አለበት» ይላሉን? እብድ አይደለም። እውነትን ይዞ መጣላቸው:: አብዛኞቻቸዉም ግን እውነትን ጠይዎች ናቸው።
阿拉伯语经注:
وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلۡحَقُّ أَهۡوَآءَهُمۡ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِذِكۡرِهِمۡ فَهُمۡ عَن ذِكۡرِهِم مُّعۡرِضُونَ
71. እውነታው (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸዉም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር:: ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው:: እነርሱም ክብራቸውን ዘንጊዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ خَرۡجٗا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيۡرٞۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
72. ወይስ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ ከሁሉም በላጭ ነው:: እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّكَ لَتَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
73.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ
74. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ግን ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው።
阿拉伯语经注:
۞ وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرّٖ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
75. ባዘንላቸውና በእነርሱ ያለውን ጉዳትም ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋዥቁ ሆነው ይዘወትሩ ነበር::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ
76. በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው:: ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም:: የሚዋደቁም አይደሉም።
阿拉伯语经注:
حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا ذَا عَذَابٖ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ
77. በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የሆነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ
78. እርሱም ያ መስሚያዎችን፤ ማያዎችንና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው:: ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም::
阿拉伯语经注:
وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ
79. እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው:: በመጨረሻም ጊዜ ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
80. እርሱም ያ ህያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው:: የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው :: አታውቁምን?
阿拉伯语经注:
بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ
81. ይልቁንም የመካ ከሓዲያን ልክ የፊተኞቹ ህዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ::
阿拉伯语经注:
قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
82. አሉም: «በሞትንና አፈርና አጥንቶች በሆንን ጊዜ እኛ እንደገና ተቀስቃሾች ነን?
阿拉伯语经注:
لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
83. «ይህንን ሁኔታ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ እስቲ ንገሩኝ።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ የአላህ ነው።» ይሉሃል። «ታዲያ አትገሠጹምን?» በላቸው።
阿拉伯语经注:
قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ
86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰባቱ ሰማያት ጌታ የታላቁም ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው።
阿拉伯语经注:
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ
87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።
阿拉伯语经注:
قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
88. «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ፤ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ (እስቲ መልሱልኝ)» በላቸው።
阿拉伯语经注:
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ
89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው።
阿拉伯语经注:
بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
90. ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው እነርሱም በመካዳቸው ውሸታሞች ናቸው::
阿拉伯语经注:
مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٖ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنۡ إِلَٰهٍۚ إِذٗا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهِۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
91. አላህ ምንም ልጅን አልያዘም አልወለደም:: ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም:: ሌላ አምላክ በነበረማ አምላኩ ሁሉ የፈጠረውን ነገር በማስተዳደር ከሌላው በተለየ ነበር:: ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በነገሰ ነበር:: አላህ ከሓዲያን እሱን ከሚመጥኑበት መግለጫ ሁሉ ጠራ::
阿拉伯语经注:
عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
92. ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ነው:: በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ::
阿拉伯语经注:
قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ
93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «ጌታዬ ሆይ! የሚስፈራሩበትን ቅጣት ብታሳየኝ፤
阿拉伯语经注:
رَبِّ فَلَا تَجۡعَلۡنِي فِي ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
94. «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ህዝቦች ውስጥ አታድርገኝ።» በል።
阿拉伯语经注:
وَإِنَّا عَلَىٰٓ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمۡ لَقَٰدِرُونَ
95. እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን::
阿拉伯语经注:
ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ ٱلسَّيِّئَةَۚ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَصِفُونَ
96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጠባይ መጥፎይቱን ነገር መልስ:: እኛ ከሓዲያን የሚሉትን ሁሉ አዋቂዎች ነንና::
阿拉伯语经注:
وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنۡ هَمَزَٰتِ ٱلشَّيَٰطِينِ
97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «ጌታዬ ሆይ ከሰይጣናት ጉትጎታዎች ባንተ እጠበቃለሁ።
阿拉伯语经注:
وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحۡضُرُونِ
98. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እኔ ከመጣዳቸው ከመቅረባቸውም ባንተው እጠበቃለሁ።» በል።
阿拉伯语经注:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ
99. አንዳቸውን ሞት በመጣበት ጊዜ ይላል: «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ።
阿拉伯语经注:
لَعَلِّيٓ أَعۡمَلُ صَٰلِحٗا فِيمَا تَرَكۡتُۚ كَلَّآۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَاۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
100. «ችላ ብዬ የተውኩትን በጎ ስራ ልሰራ እከጅላለሁና።» (ይላል)። (ይህን ከማለት ይከልከል):: እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የሆነች ቃል (ብቻ) ናት:: ከበስተፊታቸዉም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ::
阿拉伯语经注:
فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَلَآ أَنسَابَ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ وَلَا يَتَسَآءَلُونَ
101. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም። አይጠያየቁምም::
阿拉伯语经注:
فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
102.ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فِي جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ
103. እነዚያ ሚዛኖቻቸዉም የቀለሉባቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ በገሀነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
تَلۡفَحُ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ وَهُمۡ فِيهَا كَٰلِحُونَ
104. ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፋቸዋለች:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው::
阿拉伯语经注:
أَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
105. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» ይባላሉ።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ رَبَّنَا غَلَبَتۡ عَلَيۡنَا شِقۡوَتُنَا وَكُنَّا قَوۡمٗا ضَآلِّينَ
106. (እነርሱም) ይላሉ: «ታላቁ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችንና ጠማማ ህዝቦች ነበርን።
阿拉伯语经注:
رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا مِنۡهَا فَإِنۡ عُدۡنَا فَإِنَّا ظَٰلِمُونَ
107. «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣንና ወደ ዱንያ መልሰን:: ከዚህ በኋላ ወደ ክህደት ብንመለስ እኛ በዳዮች ነን።» ይላሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ ٱخۡسَـُٔواْ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ
108. አላህም ይላቸዋል: «ወራዶች ሆናችሁ በውስጧ አርፋችሁ ኑሩ እንጂ ፍጹም አታናግሩኝ።
阿拉伯语经注:
إِنَّهُۥ كَانَ فَرِيقٞ مِّنۡ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ
109. «እነሆ ከባሮቼ መካከል ‹ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን:: እዘንልንም:: አንተ ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ› የሚሉ ክፍሎች ነበሩ።
阿拉伯语经注:
فَٱتَّخَذۡتُمُوهُمۡ سِخۡرِيًّا حَتَّىٰٓ أَنسَوۡكُمۡ ذِكۡرِي وَكُنتُم مِّنۡهُمۡ تَضۡحَكُونَ
110. «እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው:: በእነርሱም ላይ ትስቁባቸው ነበር።
阿拉伯语经注:
إِنِّي جَزَيۡتُهُمُ ٱلۡيَوۡمَ بِمَا صَبَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ
111. «እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱን ብቻ በማድረግ መነዳኋቸው።» ይላቸዋል።
阿拉伯语经注:
قَٰلَ كَمۡ لَبِثۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ عَدَدَ سِنِينَ
112. «በምድር ውስጥ ስንትን አመታትን ቆያችሁ?» ይላቸዋል።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖ فَسۡـَٔلِ ٱلۡعَآدِّينَ
113. «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን:: ቆጣሪዎችንም ጠይቅ» ይላሉ።
阿拉伯语经注:
قَٰلَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗاۖ لَّوۡ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
114. ይላቸዋልም: «እናንተ የቆያችሁትን መጠን የምታውቁ ብትሆኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ ከምትቆዩት ጊዜ አንጻር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም።
阿拉伯语经注:
أَفَحَسِبۡتُمۡ أَنَّمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ عَبَثٗا وَأَنَّكُمۡ إِلَيۡنَا لَا تُرۡجَعُونَ
115. «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደ እኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን? (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)።» (ይባላሉ።)
阿拉伯语经注:
فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡحَقُّۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡكَرِيمِ
116. የእውነቱ ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: የዚያ የሚያምረው ዐርሽ ጌታም እሱ ብቻ ነው::
阿拉伯语经注:
وَمَن يَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرۡهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ
117. ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሁሉ ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው:: እነሆ ከሓዲያን አይድኑም።
阿拉伯语经注:
وَقُل رَّبِّ ٱغۡفِرۡ وَٱرۡحَمۡ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ
118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሆይ! ማር:: እዘንም:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል፡:
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 穆米尼奈
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭