Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 阿里欧姆拉尼   段:
يَوۡمَ تَجِدُ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا عَمِلَتۡ مِنۡ خَيۡرٖ مُّحۡضَرٗا وَمَا عَمِلَتۡ مِن سُوٓءٖ تَوَدُّ لَوۡ أَنَّ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَهُۥٓ أَمَدَۢا بَعِيدٗاۗ وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفۡسَهُۥۗ وَٱللَّهُ رَءُوفُۢ بِٱلۡعِبَادِ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ):: ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች:: አላህ እራሱን ያስጠነቅቃችኋል:: አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና::
阿拉伯语经注:
قُلۡ إِن كُنتُمۡ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِي يُحۡبِبۡكُمُ ٱللَّهُ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
قُلۡ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَۖ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡكَٰفِرِينَ
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ። ብሸሹም አላህ ከሓዲያንን አይወድም» በላቸው።
阿拉伯语经注:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصۡطَفَىٰٓ ءَادَمَ وَنُوحٗا وَءَالَ إِبۡرَٰهِيمَ وَءَالَ عِمۡرَٰنَ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
33. አላህ (ነብዩ) አደምን፣(ነብዩ) ኑህን፣(የነብዩ) ኢብራሂምን ቤተሰብ እና የዒምራንን ቤተሰብ ከአለማት አበለጣቸው (መረጣቸው)።
阿拉伯语经注:
ذُرِّيَّةَۢ بَعۡضُهَا مِنۢ بَعۡضٖۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
34. እኒህን ቤተሰቦች ከፊሉ ከከፊሉ የሆነ ዝርያ አድርጎ መረጣቸው። አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው።
阿拉伯语经注:
إِذۡ قَالَتِ ٱمۡرَأَتُ عِمۡرَٰنَ رَبِّ إِنِّي نَذَرۡتُ لَكَ مَا فِي بَطۡنِي مُحَرَّرٗا فَتَقَبَّلۡ مِنِّيٓۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዒምራን ባለቤት (ሀና) «ጌታዬ ሆይ! በሆዴ ውስጥ ያለውን ጽንስ ከሥራ ነፃ የተደረገ ሲሆን ላንተ አገልግሎት ይውል ዘንድ ተሳልኩ:: እናም ተቀበለኝ:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።» ባለች ጊዜ የሆነውን አስታውሱ በላቸው።
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا وَضَعَتۡهَا قَالَتۡ رَبِّ إِنِّي وَضَعۡتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا وَضَعَتۡ وَلَيۡسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلۡأُنثَىٰۖ وَإِنِّي سَمَّيۡتُهَا مَرۡيَمَ وَإِنِّيٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ
36. በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው:: የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም:: «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት:: እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች።
阿拉伯语经注:
فَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٖ وَأَنۢبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنٗا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّاۖ كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيۡهَا زَكَرِيَّا ٱلۡمِحۡرَابَ وَجَدَ عِندَهَا رِزۡقٗاۖ قَالَ يَٰمَرۡيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَاۖ قَالَتۡ هُوَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۖ إِنَّ ٱللَّهَ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٍ
37. ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት:: በመልካም አስተዳደግም አፋፋት:: ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት:: ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ:: «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው:: አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው።
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 阿里欧姆拉尼
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭