《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 宰尼 * - 译解目录


含义的翻译 章: 宰哈柔福   段:

ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ

حمٓ
1. ሓ፤ሚም፤
阿拉伯语经注:
وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
2. ገላጭ በሆነው መጽሐፍ እምላለሁ::
阿拉伯语经注:
إِنَّا جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَٰنًا عَرَبِيّٗا لَّعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
3. እኛ ታውቁ ዘንድ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ አደረግነው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّهُۥ فِيٓ أُمِّ ٱلۡكِتَٰبِ لَدَيۡنَا لَعَلِيٌّ حَكِيمٌ
4. እርሱም እኛ ዘንድ በመጽሐፎቹ እናት (መሰረት) ውስጥ ያለ፤ እርግጥ ከፍተኛ ማዕረግ ያለውና በጥበብ የተሞላ ነው።
阿拉伯语经注:
أَفَنَضۡرِبُ عَنكُمُ ٱلذِّكۡرَ صَفۡحًا أَن كُنتُمۡ قَوۡمٗا مُّسۡرِفِينَ
5. ድንበር አላፊዎች ህዝቦች በመሆናችሁ ምክኒያት ቁርኣኑን ከማውረድ ከናንተ ማገድን እናግዳለንን? (አናግድም)::
阿拉伯语经注:
وَكَمۡ أَرۡسَلۡنَا مِن نَّبِيّٖ فِي ٱلۡأَوَّلِينَ
6. በፊተኞቹም ህዝቦች ውስጥ ከነብያት መካከል ብዙን ልከናል::
阿拉伯语经注:
وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن نَّبِيٍّ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
7. ከነብይም አንድንም የሚመጣላቸው አልነበረም በእርሱ ይቀልዱበት (ያፌዙበት) የነበሩ ቢሆን እንጂ::
阿拉伯语经注:
فَأَهۡلَكۡنَآ أَشَدَّ مِنۡهُم بَطۡشٗا وَمَضَىٰ مَثَلُ ٱلۡأَوَّلِينَ
8. ከእነርሱም በሀይል ይበልጥ የበረቱትን አጥፍተናል:: የፊተኞቹም አጠፋፍ ምሳሌ አልፏል።
阿拉伯语经注:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ማን ፈጠራቸው?» ብለህ ብትጠይቃቸው «ያ ሁሉን አሸናፊዉና ሁሉን አዋቂው ጌታ ነው የፈጠራቸው» ይላሉ::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ مَهۡدٗا وَجَعَلَ لَكُمۡ فِيهَا سُبُلٗا لَّعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ
10. አላህ ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው::
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِي نَزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَنشَرۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ
11. ያም ከሰማይ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም (በውሀው) የሞተችውን አገር ህያው አደረግን:: (ሰዎች ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከየመቃብሮቻችሁ ትወጣለችሁ::
阿拉伯语经注:
وَٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡفُلۡكِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مَا تَرۡكَبُونَ
12. ያም የፍጡር ዓይነቶችን ሁሉ (ጥንድ) አድርጎ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንሰሳዎች መካከል የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው::
阿拉伯语经注:
لِتَسۡتَوُۥاْ عَلَىٰ ظُهُورِهِۦ ثُمَّ تَذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ رَبِّكُمۡ إِذَا ٱسۡتَوَيۡتُمۡ عَلَيۡهِ وَتَقُولُواْ سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَٰذَا وَمَا كُنَّا لَهُۥ مُقۡرِنِينَ
13. በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም «ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ተገባው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا لَمُنقَلِبُونَ
14. እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን» እንድትሉ ነው::
阿拉伯语经注:
وَجَعَلُواْ لَهُۥ مِنۡ عِبَادِهِۦ جُزۡءًاۚ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَكَفُورٞ مُّبِينٌ
15. ከባሮቹም መካከል ለእርሱ ክፋይን (የተወሰነን) ብቻ አደረጉለት:: ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነውና::
阿拉伯语经注:
أَمِ ٱتَّخَذَ مِمَّا يَخۡلُقُ بَنَاتٖ وَأَصۡفَىٰكُم بِٱلۡبَنِينَ
16. አላህ ከሚፈጥረው ፍጡር መካከል ሴቶች ልጆችን ብቻ ለይቶ የራሱ ልጅ አድርጎ ያዘን? (ከዚያም) እናንተን በወንዶች ልጆች መረጣችሁን? (አይደለም)።
阿拉伯语经注:
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحۡمَٰنِ مَثَلٗا ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدّٗا وَهُوَ كَظِيمٌ
17. አንዳቸዉም ለአር-ረህማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ በቁጭት የተሞላ ሆኖ ፊቱ ጥቁር ይሆናል::
阿拉伯语经注:
أَوَمَن يُنَشَّؤُاْ فِي ٱلۡحِلۡيَةِ وَهُوَ فِي ٱلۡخِصَامِ غَيۡرُ مُبِينٖ
18. በጌጣጌጥ ተከልሶ እንዲያድግ የሚደረገውን ክፍል እርሱም ከደካማነቱ የተነሳ በክርክር የማያብራራውን ፍጡር ለይተው ለአላህ ያደርጋሉን?
阿拉伯语经注:
وَجَعَلُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ ٱلَّذِينَ هُمۡ عِبَٰدُ ٱلرَّحۡمَٰنِ إِنَٰثًاۚ أَشَهِدُواْ خَلۡقَهُمۡۚ سَتُكۡتَبُ شَهَٰدَتُهُمۡ وَيُسۡـَٔلُونَ
19. እነዚያን የአር-ረሕማን ቅን ባሮች የሆኑትን መላእክትንም ሴቶች አደረጓቸው። ለመሆኑ እነርሱ መላእክት ሲፈጠሩ አብረው ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትፃፋለች:: ስለ እርሷም ይጠየቃሉ::
阿拉伯语经注:
وَقَالُواْ لَوۡ شَآءَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مَا عَبَدۡنَٰهُمۗ مَّا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ
20. «አር-ረሕማንም በፈለገ ኖሮ ባልተገዛናቸው ነበር» አሉ። ለእነርሱም በዚህ ምንም እውቀት የላቸዉም፤ እነርሱ የሚዋሹ ህዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም።
阿拉伯语经注:
أَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ كِتَٰبٗا مِّن قَبۡلِهِۦ فَهُم بِهِۦ مُسۡتَمۡسِكُونَ
21. ከእርሱ (ቁርኣን) በፊት መጽሐፍን ሰጠናቸውና እሱን አጥብቀው የያዙ ናቸውን?
阿拉伯语经注:
بَلۡ قَالُوٓاْ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّهۡتَدُونَ
22. ከቶውንም «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘናቸው:: እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተመሪዎች ነን» አሉ እንጂ።
阿拉伯语经注:
وَكَذَٰلِكَ مَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتۡرَفُوهَآ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّقۡتَدُونَ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው:: ከበፊትም በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አላክንም ቅምጥሎቿ «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘን:: እኛም ፈለጎቻቸውን ተከታዩች ነን» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::
阿拉伯语经注:
۞ قَٰلَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكُم بِأَهۡدَىٰ مِمَّا وَجَدتُّمۡ عَلَيۡهِ ءَابَآءَكُمۡۖ قَالُوٓاْ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
24. አስፈራሪው «አባቶቻችሁን በእርሱ ላይ ካገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛው ሃይማኖት ባመጣላችሁም?» ቢላቸው «እኛ በተላካችሁበት ነገር (ሀይማኖት) ከሓዲያን ነን» አሉ።
阿拉伯语经注:
فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
25. ከእነርሱም ተበቀልን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደነበር ተመልከት::
阿拉伯语经注:
وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦٓ إِنَّنِي بَرَآءٞ مِّمَّا تَعۡبُدُونَ
26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ «እኔ ከምትገዙት ጣኦታት ሁሉ ንጹህ ነኝ::
阿拉伯语经注:
إِلَّا ٱلَّذِي فَطَرَنِي فَإِنَّهُۥ سَيَهۡدِينِ
27. «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ማንንም አልገዛም:: አላህንማ በእርግጥ ይመራኛልና ብቻውን አመልከዋለሁ» ባለ ጊዜ የነበረውን አስታውስ::
阿拉伯语经注:
وَجَعَلَهَا كَلِمَةَۢ بَاقِيَةٗ فِي عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
28. በዝርዮቹም ውስጥ ወደ አላህ ይመለሱ ዘንድ (በአንድ አምላክ) ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት::
阿拉伯语经注:
بَلۡ مَتَّعۡتُ هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ وَرَسُولٞ مُّبِينٞ
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁን እነዚህን ቁረይሾችንም አባቶቻቸውንም ቁርኣንንና ገላጭ መልዕክተኛ እስካመጣላቸው ድረስ አጣቀምኳቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ قَالُواْ هَٰذَا سِحۡرٞ وَإِنَّا بِهِۦ كَٰفِرُونَ
30. እውነት በመጣላቸው ጊዜም «ይህ ያመጣሀው ድግምት ነው። እኛም በእርሱ ከሓዲያን ነን።» አሉ::
阿拉伯语经注:
وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنَ ٱلۡقَرۡيَتَيۡنِ عَظِيمٍ
31. ይህም «ቁርኣን በሁለቱ ከተሞች በአንዱ በሚኖር ታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?» አሉ።
阿拉伯语经注:
أَهُمۡ يَقۡسِمُونَ رَحۡمَتَ رَبِّكَۚ نَحۡنُ قَسَمۡنَا بَيۡنَهُم مَّعِيشَتَهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَرَفَعۡنَا بَعۡضَهُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَتَّخِذَ بَعۡضُهُم بَعۡضٗا سُخۡرِيّٗاۗ وَرَحۡمَتُ رَبِّكَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ የጌታህን ስጦታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት እንኳን ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል:: ከፊላቸዉም ከፊሉን አገልጋይ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ (በሀብት) አበለጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው::
阿拉伯语经注:
وَلَوۡلَآ أَن يَكُونَ ٱلنَّاسُ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ لَّجَعَلۡنَا لِمَن يَكۡفُرُ بِٱلرَّحۡمَٰنِ لِبُيُوتِهِمۡ سُقُفٗا مِّن فِضَّةٖ وَمَعَارِجَ عَلَيۡهَا يَظۡهَرُونَ
33. ሰዎችም (በክህደት) ላይ አንድ ህዝብ የሚሆኑ ባልነበሩ ኖሮ በአል-ረህማን ለሚክዱ ሰዎች ሁሉ (በዚህች ዓለም) ለቤቶቻቸው የብር ጣራዎች፤ የሚወጣጡባቸውም የብር መሰላሎች፤ ባደረግንላቸው ነበር።
阿拉伯语经注:
وَلِبُيُوتِهِمۡ أَبۡوَٰبٗا وَسُرُرًا عَلَيۡهَا يَتَّكِـُٔونَ
34. ለቤቶቻቸው የብር በሮች፤ ለሚደገፉባቸዉም የብር አልጋዎች፤(ባደረግንላቸው ነበር)።
阿拉伯语经注:
وَزُخۡرُفٗاۚ وَإِن كُلُّ ذَٰلِكَ لَمَّا مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَٱلۡأٓخِرَةُ عِندَ رَبِّكَ لِلۡمُتَّقِينَ
35. የወርቅ ጌጥንም ባደረግንላቸው ነበር። ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም:: ጠፊ ነው:: መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆች ብቻ ናት::
阿拉伯语经注:
وَمَن يَعۡشُ عَن ذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ نُقَيِّضۡ لَهُۥ شَيۡطَٰنٗا فَهُوَ لَهُۥ قَرِينٞ
36. (በቁርኣን ከተወሳው) ከአል-ረሕማን ግሳጼ የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን። ስለዚህ እርሱ ለእርሱ የሁልግዜ ቁራኛው ነው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّهُمۡ لَيَصُدُّونَهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُم مُّهۡتَدُونَ
37. እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ሁሉ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል::
阿拉伯语经注:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَنَا قَالَ يَٰلَيۡتَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَ بُعۡدَ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرِينُ
38. (በትንሳኤ) ወደ እኛ በመጣ ጊዜ «(ቁራኛዬ ሆይ) በእኔና ባንተ መካከል የምስራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ዋ ምኞቴ! ምን የከፋ ቁራኛ ነህ።» ይላል::
阿拉伯语经注:
وَلَن يَنفَعَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ إِذ ظَّلَمۡتُمۡ أَنَّكُمۡ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ
39. (ከሓዲያን ሆይ!) ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም (ይባላሉ)።
阿拉伯语经注:
أَفَأَنتَ تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ أَوۡ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَمَن كَانَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ደንቆሮዎችን ታሰማለህን? ወይስ እውሮችንና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑ ሰዎችን ትመራለህን?
阿拉伯语经注:
فَإِمَّا نَذۡهَبَنَّ بِكَ فَإِنَّا مِنۡهُم مُّنتَقِمُونَ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቅጣታቸውን ሳታይ ብንወስድህ እኛ ከእነርሱ ተበቃዮች ነን።
阿拉伯语经注:
أَوۡ نُرِيَنَّكَ ٱلَّذِي وَعَدۡنَٰهُمۡ فَإِنَّا عَلَيۡهِم مُّقۡتَدِرُونَ
42. ወይም ያንን የቀጠርናቸውን ብናሳይህ እኛ በእነርሱ ቅጣት ላይ ቻይዎች ነን::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَمۡسِكۡ بِٱلَّذِيٓ أُوحِيَ إِلَيۡكَۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ:: አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّهُۥ لَذِكۡرٞ لَّكَ وَلِقَوۡمِكَۖ وَسَوۡفَ تُسۡـَٔلُونَ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ (ቁርኣን) ላንተም ሆነ ለህዝቦችህ ታላቅ ክብር ነው:: ወደፊተም ከርሱ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَسۡـَٔلۡ مَنۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رُّسُلِنَآ أَجَعَلۡنَا مِن دُونِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ءَالِهَةٗ يُعۡبَدُونَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞችም ካንተ በፊት የላክናቸው ከአር-ረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የሆነን አማልክት አድርገን እንደሆነ (ተከታዮቻቸውን) ጠይቃቸው።
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَقَالَ إِنِّي رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም በተዓምራታችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን:: «እኔ የዓለማቱ ጌታ መልዕክተኛ ነኝ» አላቸዉም::
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا جَآءَهُم بِـَٔايَٰتِنَآ إِذَا هُم مِّنۡهَا يَضۡحَكُونَ
47. በተዓምራታችን በመጣላቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ በእርሷ ይስቃሉ::
阿拉伯语经注:
وَمَا نُرِيهِم مِّنۡ ءَايَةٍ إِلَّا هِيَ أَكۡبَرُ مِنۡ أُخۡتِهَاۖ وَأَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
48. ከተዓምራት አንዲትንም እናሳያቸዉም እርሷ ከብጤዋ በጣም የበለጠች ብትሆን እንጅ። ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው::
阿拉伯语经注:
وَقَالُواْ يَٰٓأَيُّهَ ٱلسَّاحِرُ ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ إِنَّنَا لَمُهۡتَدُونَ
49. አንተ ድግምተኛ ሆይ! «ጌታህን አንተ ዘንድ ቃል በገባልህ ለእኛ ለምንልን እኛ (ቅጣቱን ቢያነሳልን) ተመሪዎች ነን» አሉም::
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابَ إِذَا هُمۡ يَنكُثُونَ
50. ስቃዩን ከእነርሱ ላይ በገለጥንም ጊዜ ወዲያውኑ ቃልኪዳናቸውን ያፈርሳሉ::
阿拉伯语经注:
وَنَادَىٰ فِرۡعَوۡنُ فِي قَوۡمِهِۦ قَالَ يَٰقَوۡمِ أَلَيۡسَ لِي مُلۡكُ مِصۡرَ وَهَٰذِهِ ٱلۡأَنۡهَٰرُ تَجۡرِي مِن تَحۡتِيٓۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ
51. ፈርዖንም በህዝቦቹ ውስጥ ተጣራ። (እንዲህ) አለም: «ህዝቦቼ ሆይ! የሚስር (ግብጽ) ግዛት የእኔ አይደለምን? እነዚህም ጅረቶች ከስሬ የሚፈሱ ሲሆኑ የእኔ አይደሉምን? አትመለከቱምን?
阿拉伯语经注:
أَمۡ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي هُوَ مَهِينٞ وَلَا يَكَادُ يُبِينُ
52. «በእውነት እኔ ከዚያ ያ እርሱ ወራዳ ጉዳዩንም በደንብ ሊገልጽ የማይችል ከሆነው ሰው በላጭ ነኝ።
阿拉伯语经注:
فَلَوۡلَآ أُلۡقِيَ عَلَيۡهِ أَسۡوِرَةٞ مِّن ذَهَبٍ أَوۡ جَآءَ مَعَهُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ مُقۡتَرِنِينَ
53. «እርሱ ላይ የወርቅ አንባሮች ለምን አልተጣሉበትም? ወይም መላዕክት ከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ለምን አልመጡም?» አለ።
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَخَفَّ قَوۡمَهُۥ فَأَطَاعُوهُۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ
54. ህዝቦቹንም አቄላቸው:: ታዘዙትም:: እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::
阿拉伯语经注:
فَلَمَّآ ءَاسَفُونَا ٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ أَجۡمَعِينَ
55. ባስቆጡንም ጊዜ ከእነርሱ ተበቀልን:: ሁሉንም አሰመጥናቸውም::
阿拉伯语经注:
فَجَعَلۡنَٰهُمۡ سَلَفٗا وَمَثَلٗا لِّلۡأٓخِرِينَ
56. በጥፋት ቀዳሚዎችና ለኋለኞች መቀጣጫ ምሳሌም አደረግናቸው::
阿拉伯语经注:
۞ وَلَمَّا ضُرِبَ ٱبۡنُ مَرۡيَمَ مَثَلًا إِذَا قَوۡمُكَ مِنۡهُ يَصِدُّونَ
57. የመርየም ልጅ ዒሳ ምሳሌ በተደረገ ጊዜ ህዝቦችህ (ከሀዲያኑ) ወዲያውኑ ከእርሱ ሌሎችን ያግዳሉ።
阿拉伯语经注:
وَقَالُوٓاْ ءَأَٰلِهَتُنَا خَيۡرٌ أَمۡ هُوَۚ مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلَۢاۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٌ خَصِمُونَ
58. «አማልክቶቻችን ይበልጣሉን? ወይስ እርሱ ይበልጣል?» አሉም:: ለክርክር እንጅ ላንተ (እርሱን) ምሳሌ አላደረጉትም:: በእውነት እነርሱ ክርክረ ብርቱ ህዝቦች ናቸው::
阿拉伯语经注:
إِنۡ هُوَ إِلَّا عَبۡدٌ أَنۡعَمۡنَا عَلَيۡهِ وَجَعَلۡنَٰهُ مَثَلٗا لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
59. እርሱ (ዒሳ) በእርሱ ላይ የለገስንለት ለኢስራኢል ልጆችም ተዐምር ያደረግነው አገልጋይ ባሪያችን እንጂ ሌላ አይደለም::
阿拉伯语经注:
وَلَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَا مِنكُم مَّلَٰٓئِكَةٗ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَخۡلُفُونَ
60. ብንፈልግም ኖሮ በምድር ላይ በእናንተ ምትክ መላዕክትን ባደረግን ነበር::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّهُۥ لَعِلۡمٞ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمۡتَرُنَّ بِهَا وَٱتَّبِعُونِۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም (ዒሳ) ለስዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው:: በእርሷም አትጠራጠሩ:: ተከተሉኝም:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَا يَصُدَّنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
62. ሰይጣንም አያግዳችሁ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا جَآءَ عِيسَىٰ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ قَالَ قَدۡ جِئۡتُكُم بِٱلۡحِكۡمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُم بَعۡضَ ٱلَّذِي تَخۡتَلِفُونَ فِيهِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
63. ዒሳ ግልፅ ተዓምራታችንን ይዞ በመጣ ጊዜ «በእርግጥ በጥበብ መጣሁላችሁ:: የዚያንም የምትለያዩበትን ጉዳይ ከፊሉን ለእናንተ ላብራራላችሁ መጣሁ:: እናም አላህን ፍሩ:: ታዘዙኝም::
阿拉伯语经注:
إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
64. «አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው::» አለ።
阿拉伯语经注:
فَٱخۡتَلَفَ ٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَيۡنِهِمۡۖ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ عَذَابِ يَوۡمٍ أَلِيمٍ
65. ከመካከላቸዉም አህዛቦቹ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለበደሉት ህዝቦች ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው::
阿拉伯语经注:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
66. ሰዓቲቱን እነርሱ የማያውቁ ሆነው በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ (ሌላ) ይጠባበቃሉን?::
阿拉伯语经注:
ٱلۡأَخِلَّآءُ يَوۡمَئِذِۭ بَعۡضُهُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوٌّ إِلَّا ٱلۡمُتَّقِينَ
67. አላህን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ሲቀሩ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው።
阿拉伯语经注:
يَٰعِبَادِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَآ أَنتُمۡ تَحۡزَنُونَ
68. (አላህም ለነርሱ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ምንም ፍርሀት የለባችሁም:: እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም።
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ مُسۡلِمِينَ
69. «እነዚያ በአናቅጻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ::
阿拉伯语经注:
ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ أَنتُمۡ وَأَزۡوَٰجُكُمۡ تُحۡبَرُونَ
70. (ባሮቼ ሆይ!) « እናንተም ሚስቶቻችሁም ገነትን ግቡ ትደሰታላችሁ (ትከበራላችሁ)።» ይባላሉ::
阿拉伯语经注:
يُطَافُ عَلَيۡهِم بِصِحَافٖ مِّن ذَهَبٖ وَأَكۡوَابٖۖ وَفِيهَا مَا تَشۡتَهِيهِ ٱلۡأَنفُسُ وَتَلَذُّ ٱلۡأَعۡيُنُۖ وَأَنتُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
71. ከወርቅ የሆኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳህኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ እንዲዞሩ ይደረጋሉ። በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት ዓይኖችም የሚደስቱበት ሁሉ አለ:: እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ::
阿拉伯语经注:
وَتِلۡكَ ٱلۡجَنَّةُ ٱلَّتِيٓ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
72. ይህም ያ ስትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ነው::
阿拉伯语经注:
لَكُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٞ كَثِيرَةٞ مِّنۡهَا تَأۡكُلُونَ
73. ለእናንተ በውስጧ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁና ከእርሷም እንደልባችሁ ትበላላችሁ ይባላሉ::
阿拉伯语经注:
إِنَّ ٱلۡمُجۡرِمِينَ فِي عَذَابِ جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ
74. አመጸኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘወታሪዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
لَا يُفَتَّرُ عَنۡهُمۡ وَهُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ
75. ከእነርሱም ቅጣት በፍጹም አይቀለልላቸዉም:: እነርሱም በእርሱ ውስጥ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن كَانُواْ هُمُ ٱلظَّٰلِمِينَ
76. አልበደልናቸዉም:: በዳዮቹ ግን እነርሱው ብቻ ነበሩ::
阿拉伯语经注:
وَنَادَوۡاْ يَٰمَٰلِكُ لِيَقۡضِ عَلَيۡنَا رَبُّكَۖ قَالَ إِنَّكُم مَّٰكِثُونَ
77. «ማሊክ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ (በሞት) ይፍረድ።» እያሉ ይጣራሉም:: ይላቸዋልም: «እናንተ (በቅጣት ውስጥ) ለዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ።
阿拉伯语经注:
لَقَدۡ جِئۡنَٰكُم بِٱلۡحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَكُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ
78. «እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ:: ግን አብዛኞቻችሁ እውነትን ጠይዎች ነበራችሁ» ይባላሉ::
阿拉伯语经注:
أَمۡ أَبۡرَمُوٓاْ أَمۡرٗا فَإِنَّا مُبۡرِمُونَ
79. ይልቁንም (በነብዩ ላይ) በማደም ነገርን አጠነከሩን? እኛም ተንኮላቸውን ወደ እነርሱ በመመለስ አጠንካሪዎች ነን::
阿拉伯语经注:
أَمۡ يَحۡسَبُونَ أَنَّا لَا نَسۡمَعُ سِرَّهُمۡ وَنَجۡوَىٰهُمۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيۡهِمۡ يَكۡتُبُونَ
80. ወይም እኛ ሚስጥራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መሆናችንን ያስባሉን? ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: መልዕክተኞቻችን እነርሱ ዘንድ ናቸው:: የሚሉትን ሁሉ ይጽፋሉ::
阿拉伯语经注:
قُلۡ إِن كَانَ لِلرَّحۡمَٰنِ وَلَدٞ فَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡعَٰبِدِينَ
81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለአር-ረሕማን ልጅ (የለዉም እንጂ) ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎች መጀመሪያ ነኝ» በላቸው::
阿拉伯语经注:
سُبۡحَٰنَ رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ رَبِّ ٱلۡعَرۡشِ عَمَّا يَصِفُونَ
82. የሰማያት፤ የምድርና የዙፋኑ ጌታ ከሓዲያን ስለ እሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ::
阿拉伯语经注:
فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ
83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን ይስፈራሩበት የነበሩትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ በስህተታቸው ውስጥ ይዋኙ ተዋቸው :: ይጫዎቱም::
阿拉伯语经注:
وَهُوَ ٱلَّذِي فِي ٱلسَّمَآءِ إِلَٰهٞ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَٰهٞۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡعَلِيمُ
84. እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባው በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባው ብቸኛ አምላክ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ሁሉን አዋቂው ነው::
阿拉伯语经注:
وَتَبَارَكَ ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
85. ያም የሰማያት፤ የምድርና በመካከላቸው ያለው ሁሉ ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነው አምላክ ላቀ:: የሰዓቲቱም የመምጫዋ ዘመን ዕውቀት በእርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ::
阿拉伯语经注:
وَلَا يَمۡلِكُ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِهِ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَن شَهِدَ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ
86. እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክት ሁሉ እነርሱ ትክክለኛውን የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት ክፍሎች በስተቀር ምልጃ አይችሉም::
阿拉伯语经注:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ
87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ:: ታዲያ (ከትክክለኛው እምነት) ወዴት ይዞራሉ::
阿拉伯语经注:
وَقِيلِهِۦ يَٰرَبِّ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ قَوۡمٞ لَّا يُؤۡمِنُونَ
88. (ነብዩ) ጌታዬ ሆይ! እነዚህ የማያምኑ ህዝቦች ናቸው የማለቱም እውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።
阿拉伯语经注:
فَٱصۡفَحۡ عَنۡهُمۡ وَقُلۡ سَلَٰمٞۚ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: «ነገሬ ስላም ነው» በልም:: ወደፊትም የሚመጣባቸውን ሲደርስ ያውቃሉ::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 宰哈柔福
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 宰尼 - 译解目录

阿姆哈拉语翻译

关闭