للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: النجم   آية:

سورة النجم - አን ነጅም

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ
1. በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤
التفاسير العربية:
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ
2. (እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ)፤ ባልደረባችሁ ሙሐመድ ከሐቅ አልተሳሳተም። አላፈነገጠም።
التفاسير العربية:
وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ
3. ከልብ ወለድ ስሜቱም አይናገርም::
التفاسير العربية:
إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ
4. እርሱ (ንግግሩ) ከአላህ የተወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።
التفاسير العربية:
عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ
5. ሀይለ ብርቱ የሆነው አስተማረው::
التفاسير العربية:
ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ
6. የእውቀት ባለቤት የሆነው:: ከዚያም ላይ ሆኖ ተመቻቸ።
التفاسير العربية:
وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ
7. በላይኛው አድማስ ላይ ሆኖ፤
التفاسير العربية:
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ
8. ከዚያም (ነቢዩን) ቀረበው፤ በጣም ተጠጋውም።
التفاسير العربية:
فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ
9. ከዚያም የሁለት ደጋን ጫፎች ያህል ወይም ከዚያም ባነሰ ርቀት ላይ ሆነም::
التفاسير العربية:
فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ
10. እናም (አላህ) ለአገልጋዩ (ለሙሐመድ) ማውረድ የሻውን አወረደ::
التفاسير العربية:
مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ
11. ያየውን ነገር ሁሉ ልቦናው አላስተባበለዉም::
التفاسير العربية:
أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ
12. ታዲያ (ከሓዲያን ሆይ!) በሚያየው ጉዳይ ላይ ትከራከሩታላችሁን?
التفاسير العربية:
وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ
13. እርግጥ በሌላይቱም መውረድ (ነቢዩ ሙሐመድ መልዐኩ ጂብሪልን) አይቶታል::
التفاسير العربية:
عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ
14. ይኸዉም ሲድረቱ አል-ሙንተሃ (የመጨረሻቱ ቁርቁራ) በተባለው ዓለም ላይ ነው::
التفاسير العربية:
عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ
15. እርሷ ዘንድ መኖርያ የሆነችው ገነት አለች::
التفاسير العربية:
إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ
16. (ቁርቁራይቱን) ሸፋኝ ነገር በሸፈናት ጊዜ (አየው)።
التفاسير العربية:
مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ
17. አይኑ አልተዘነበለም:: ወሰንም አላለፈም።
التفاسير العربية:
لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ
18. ከጌታው ታላላቅ ተዐምራት በእርግጥ ተመለከተ።
التفاسير العربية:
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ
19. (ቁርይሾች ሆይ!) ላትንና ዑዛን አያችሁን?
التفاسير العربية:
وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ
20. ስለ ሶስተኛዋ መናትም የምታውቁትን እስቲ ንገሩኝ::
التفاسير العربية:
أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ
21. ለእናንተ ወንድ ወንድ ለእሱ ግን ሴት ሴት ታደርጋላችሁን::
التفاسير العربية:
تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ
22. ይህ ተግባር አድሏዊ ክፍፍል ነው::
التفاسير العربية:
إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ
23. እነዚያ ጣዖታት እናንተና አባቶቻችሁ የሰየማችኋቸው ስሞች ብቻ እንጂ ሌላ አይደሉም::አላህ በእርሷ (መገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ጣኡት አምላኪዎች ሁሉ ከጌታቸው የተላከላቸው ቅኑ መመሪያ እያለ የሚከተሉት ግን ጥርጣሬንና ስሜትን ብቻ ነው::
التفاسير العربية:
أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ
24. የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ ያገኛልን?
التفاسير العربية:
فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ
25. መጪውን ዓለምም ሆነ የመጀመሪያው ዓለም የአላህ ብቻ ነው::
التفاسير العربية:
۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ
26. በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት አላህ የሚሻውንና የሚወደውን ለሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: النجم
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق