Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: El-Bekara   Ajet:
أَوَلَا يَعۡلَمُونَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَ
77. አላህ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ጌታ መሆኑን አያውቁምን?
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَمِنۡهُمۡ أُمِّيُّونَ لَا يَعۡلَمُونَ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّآ أَمَانِيَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَظُنُّونَ
78. ከእነርሱም መካከል መጽሐፍን የማያውቁ መሃይማን አሉ:: ግን ከንቱ ምኞቶችን ይመኛሉ:: እነርሱም መጠራጠርን እንጂ ትክክለኛ እውቀት የላቸዉም::
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ يَكۡتُبُونَ ٱلۡكِتَٰبَ بِأَيۡدِيهِمۡ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشۡتَرُواْ بِهِۦ ثَمَنٗا قَلِيلٗاۖ فَوَيۡلٞ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتۡ أَيۡدِيهِمۡ وَوَيۡلٞ لَّهُم مِّمَّا يَكۡسِبُونَ
79. እነዚያ መጽሐፍን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያ በእርሱ ጥቂት ዋጋን ሊገዙበት ብለው: «ይህ ከአላህ ዘንድ የወረደ ነው» ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው። እነርሱ ከዚያ እጆቻቸው ከፃፉት ወንጀል ወዮላቸው:: እነርሱ ከዚያ ከሚሰሩት ኃጢአት ወዮላቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَقَالُواْ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامٗا مَّعۡدُودَةٗۚ قُلۡ أَتَّخَذۡتُمۡ عِندَ ٱللَّهِ عَهۡدٗا فَلَن يُخۡلِفَ ٱللَّهُ عَهۡدَهُۥٓۖ أَمۡ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
80. (አይሁዶች) “የገሀነም እሳት ለተቆጠሩ ውስን ቀናት ብቻ እንጂ ፈጽሞ አትነካንም” አሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “በዚህ ጉዳይ ከአላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን? ይህ ከሆነ አላህም ኪዳኑን አያፈርስም:: ወይስ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?” በላቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
بَلَىٰۚ مَن كَسَبَ سَيِّئَةٗ وَأَحَٰطَتۡ بِهِۦ خَطِيٓـَٔتُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
81. እንዴታ እነዚያ መጥፎን ተግባር የሰሩና በኃጢአትም የተከበቡ ሁሉ በእርግጥ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
82. እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ የገነት ጓዶች ናቸው። እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ لَا تَعۡبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَانٗا وَذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَقُولُواْ لِلنَّاسِ حُسۡنٗا وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ ثُمَّ تَوَلَّيۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗا مِّنكُمۡ وَأَنتُم مُّعۡرِضُونَ
83. (የኢስራኢል-ልጆችን) “አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ:: ለወላጆችም በጎን ስራ ስሩ:: ለዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞችና ለሚስኪኖችም በጎን ዋሉ:: ለሰዎችም ሁሉ መልካምን ብቻ ተናገሩ :: ሶላትን ደንቡን ጠብቃች ስገዱ:: ዘካን ለተገቢው ስጡ” በማለት ጥብቅ ቃልኪዳን በያዝንባቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከዚያም ከእናንተ ጥቂቶቹ ሲቀሩ ሸሻችሁ:: እናንተ (ቃልኪዳንንም) የምትተው ናችሁ፡፡
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: El-Bekara
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje