Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: El-Bekara   Ajet:
وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمُ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِ وَتَثۡبِيتٗا مِّنۡ أَنفُسِهِمۡ كَمَثَلِ جَنَّةِۭ بِرَبۡوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٞ فَـَٔاتَتۡ أُكُلَهَا ضِعۡفَيۡنِ فَإِن لَّمۡ يُصِبۡهَا وَابِلٞ فَطَلّٞۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ
265. የእነዚያ የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ከነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ብለው ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱት ምሳሌያቸው በተስተካከለች ከፍተኛ ቦታ ላይ እንዳለች አትክልት ሲሆን ይህች አትክልት ከፍተኛ ዝናብ አግኝታ እጥፍ ድርብ ምርት እንደሰጠች ከፍተኛ ዝናብ ባታገኝ እንኳን ካፊያ ብቻ እንደሚበቃት የአትክልት አይነት ይመስላል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
أَيَوَدُّ أَحَدُكُمۡ أَن تَكُونَ لَهُۥ جَنَّةٞ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَابٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ لَهُۥ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَأَصَابَهُ ٱلۡكِبَرُ وَلَهُۥ ذُرِّيَّةٞ ضُعَفَآءُ فَأَصَابَهَآ إِعۡصَارٞ فِيهِ نَارٞ فَٱحۡتَرَقَتۡۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَتَفَكَّرُونَ
266. ከናንተ አንዳችሁ ሁሉን ዓይነት ምርት የምትሰጥ ከስሯ ወንዞች የምፈሱባት የዘንባባዎችና የወይኖች የአትክልት ቦታ ልትኖረው እርጅናም ሊነካውና በእነርሱም ደካሞች ረዳት የለሽ ህፃናት ያሉት ሲሆኑ በውስጡ እሳት ያለበት ውርጭ ምርቱ ላይ አደጋ ሊያደርስበት እና ልትቃጠልበት ይወዳልን? ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል:: ልታስተነትኑ ይከጀላልና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنفِقُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا كَسَبۡتُمۡ وَمِمَّآ أَخۡرَجۡنَا لَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِۖ وَلَا تَيَمَّمُواْ ٱلۡخَبِيثَ مِنۡهُ تُنفِقُونَ وَلَسۡتُم بِـَٔاخِذِيهِ إِلَّآ أَن تُغۡمِضُواْ فِيهِۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٌ
267. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያ ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ:: መጥፎውንም ለመስጠት አታስቡ:: እርሱን ለራሳችሁ አይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትሆኑ ከእርሱ (ከመጥፎ) ትሰጣላችሁን? አላህ ተብቃቂና ምስጉን መሆኑን እወቁ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
ٱلشَّيۡطَٰنُ يَعِدُكُمُ ٱلۡفَقۡرَ وَيَأۡمُرُكُم بِٱلۡفَحۡشَآءِۖ وَٱللَّهُ يَعِدُكُم مَّغۡفِرَةٗ مِّنۡهُ وَفَضۡلٗاۗ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٞ
268. ሰይጣን እንዳትለግሱ በድህነት ያስፈራራችኋል:: በመጥፎም ያዛችኋል:: አላህ ከእርሱ የሆነን ምህረትና ችሮታን ሊያጎናጽፋችሁ ተስፋ ሰጥቷችኋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው::
Tefsiri na arapskom jeziku:
يُؤۡتِي ٱلۡحِكۡمَةَ مَن يَشَآءُۚ وَمَن يُؤۡتَ ٱلۡحِكۡمَةَ فَقَدۡ أُوتِيَ خَيۡرٗا كَثِيرٗاۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
269. አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል:: ጥበብንም የሚስ-ሰጥ ሰው ሁሉ ብዙ መልካም ነገርን በእርግጥ ተሰጥቷል:: የአዕምሮ ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም::
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: El-Bekara
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje