Check out the new design

Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique * - Lexique des traductions


Traduction des sens Sourate: Al Baqarah   Verset:
قَالُواْ ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِيَ إِنَّ ٱلۡبَقَرَ تَشَٰبَهَ عَلَيۡنَا وَإِنَّآ إِن شَآءَ ٱللَّهُ لَمُهۡتَدُونَ
70. ጌታህን ጠይቅልን :: እርሷ ምን እንደሆነች ይግለጽልን:: ምክንያቱም ላሞቹ በሙሉ በእኛ ላይ ተመሳሰሉብን:: እኛም አላህ የሻ እንደሆነ በእርግጥ (ትክክለኛውን አቅጣጫ የምንይዝ) ተመሪዎች ነን” አሉ፡፡
Les exégèses en arabe:
قَالَ إِنَّهُۥ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٞ لَّا ذَلُولٞ تُثِيرُ ٱلۡأَرۡضَ وَلَا تَسۡقِي ٱلۡحَرۡثَ مُسَلَّمَةٞ لَّا شِيَةَ فِيهَاۚ قَالُواْ ٱلۡـَٰٔنَ جِئۡتَ بِٱلۡحَقِّۚ فَذَبَحُوهَا وَمَا كَادُواْ يَفۡعَلُونَ
71. እርሱም: «‹እርሷ ያልተገራች ምድርን በማረስ የማታስነሳ፤ እርሻንም የማታጠጣ፤ ከነውር ሁሉ ነፃ የሆነች፤ ጸያፍ ምልክት የሌለባት ናት።› ይላችኋል አላቸው።» እነርሱም «አሁን ገና በትክክል መጣህ።» አሉ:: ከዚያ ትዕዛዙን ላለመፈጸም የቀረቡ ሆነው ላሟን አረዷት።
Les exégèses en arabe:
وَإِذۡ قَتَلۡتُمۡ نَفۡسٗا فَٱدَّٰرَٰءۡتُمۡ فِيهَاۖ وَٱللَّهُ مُخۡرِجٞ مَّا كُنتُمۡ تَكۡتُمُونَ
72. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ነፍስ በገደላችሁና በእርሷም ጉዳይ በተከራከራችሁ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: አላህ ያን በውስጣችሁ ትደብቁት የነበራችሁትን ሚስጢር ሁሉ ገላጭ ነው፡፡
Les exégèses en arabe:
فَقُلۡنَا ٱضۡرِبُوهُ بِبَعۡضِهَاۚ كَذَٰلِكَ يُحۡيِ ٱللَّهُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَيُرِيكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
73. (የሙቱን በድን) «በታረደችው ላም ከፊል አካል ምቱት አልን »:: (እናም መቱትና ተነሳ:: የገደለው ማን እንደሆነ ነገራቸውና እንደገና ሞተ::) ሰዎች ሆይ! ልክ እንደዚሁ ትገነዘቡና ታውቁ ዘንድ ሙታንን ህያው በማድረግ ተዓምራቶቹን ያሳያችኋል፡፡
Les exégèses en arabe:
ثُمَّ قَسَتۡ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ فَهِيَ كَٱلۡحِجَارَةِ أَوۡ أَشَدُّ قَسۡوَةٗۚ وَإِنَّ مِنَ ٱلۡحِجَارَةِ لَمَا يَتَفَجَّرُ مِنۡهُ ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا يَشَّقَّقُ فَيَخۡرُجُ مِنۡهُ ٱلۡمَآءُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا يَهۡبِطُ مِنۡ خَشۡيَةِ ٱللَّهِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
74. ከዚያም ልቦቻቸው ከዚህ (ትዕይንት) በኋላ ደረቁ:: እርሷም በድርቅና እንደ አለት ድንጋዩች ወይም ከእርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው:: ምክንያቱም ከድንጋዩች መካከል ጅረቶች (ወንዞች) የሚፈሱበት፤ ከእነርሱም የሚሰነጥቅና ከእርሱ ውሃ ምንጭ የሚወጣው፤ ከእነርሱም አላህን ከመፍራቱ የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አለና:: አላህ ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ከአንዱም ዘንጊ አይደለም፡፡
Les exégèses en arabe:
۞ أَفَتَطۡمَعُونَ أَن يُؤۡمِنُواْ لَكُمۡ وَقَدۡ كَانَ فَرِيقٞ مِّنۡهُمۡ يَسۡمَعُونَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُۥ مِنۢ بَعۡدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ
75. ከ(አይሁድ) መካከል የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም እውነቱን ከተረዱ በኋላ ሆን ብለው እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ቡድኖች እያሉ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
Les exégèses en arabe:
وَإِذَا لَقُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَا بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٖ قَالُوٓاْ أَتُحَدِّثُونَهُم بِمَا فَتَحَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمۡ لِيُحَآجُّوكُم بِهِۦ عِندَ رَبِّكُمۡۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
76. እነዚያም ያመኑትን ሙስሊሞችን ባገኙ ጊዜ “እኛም እንደናንተው አምነናል” ይላሉ:: እርስ በርሳቸው ብቻ በተገናኙ ጊዜ ግን “አላህ በእናንተ ላይ የገለጸላችሁን ነገር በጌታችሁ ዘንድ እርሱን መረጃ እንዲያቀርቡባችሁ ትነግሯቸዋላችሁን? አታስተውሉምን?” ይባባላሉ::
Les exégèses en arabe:
 
Traduction des sens Sourate: Al Baqarah
Lexique des sourates Numéro de la page
 
Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique - Lexique des traductions

La traduction par Muhammad Zayn Zahr Al-Dîn. Publiée par l'Académie d'Afrique.

Fermeture