Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ   આયત:
وَلَقَدۡ ذَرَأۡنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِۖ لَهُمۡ قُلُوبٞ لَّا يَفۡقَهُونَ بِهَا وَلَهُمۡ أَعۡيُنٞ لَّا يُبۡصِرُونَ بِهَا وَلَهُمۡ ءَاذَانٞ لَّا يَسۡمَعُونَ بِهَآۚ أُوْلَٰٓئِكَ كَٱلۡأَنۡعَٰمِ بَلۡ هُمۡ أَضَلُّۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡغَٰفِلُونَ
179. ከአጋንንትም ሆነ ከሰዎች መካከል ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን:: ለእነርሱ የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው:: ለእነርሱም የማያዩባቸው ዓይኖች አሏቸው:: ለእነርሱም የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው:: እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው:: ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው:: እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱው ናቸው::
અરબી તફસીરો:
وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
180. ለአላህ መልካም ስሞች አሉት:: (ዱዓ ስታደርጉ) በእርሷ ጥሩት:: እነዚያን ስሞቹን የሚያጣምሙትን ክፍሎች ተዋቸው:: ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ::
અરબી તફસીરો:
وَمِمَّنۡ خَلَقۡنَآ أُمَّةٞ يَهۡدُونَ بِٱلۡحَقِّ وَبِهِۦ يَعۡدِلُونَ
181. ከፈጠርናቸዉም መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካክሉ ህዝቦችም አሉ::
અરબી તફસીરો:
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا سَنَسۡتَدۡرِجُهُم مِّنۡ حَيۡثُ لَا يَعۡلَمُونَ
182. እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ሰዎች ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ እናዘናጋቸዋለን::
અરબી તફસીરો:
وَأُمۡلِي لَهُمۡۚ إِنَّ كَيۡدِي مَتِينٌ
183. ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ:: ጥበቤ ብርቱ ነውና::
અરબી તફસીરો:
أَوَلَمۡ يَتَفَكَّرُواْۗ مَا بِصَاحِبِهِم مِّن جِنَّةٍۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٌ
184. በነብያቸው በሙሐመድ ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን አያስተውሉምን? እርሱ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለም::
અરબી તફસીરો:
أَوَلَمۡ يَنظُرُواْ فِي مَلَكُوتِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٖ وَأَنۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَدِ ٱقۡتَرَبَ أَجَلُهُمۡۖ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَهُۥ يُؤۡمِنُونَ
185. በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛዉም ነገር አላህ በፈጠራቸው ሁሉ የሞት ጊዜያቸዉም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መሆኑን አያስተውሉምን? ለመሆኑ እነርሱ ከቁርኣን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ::
અરબી તફસીરો:
مَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَا هَادِيَ لَهُۥۚ وَيَذَرُهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
186. አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ይተዋቸዋል::
અરબી તફસીરો:
يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرۡسَىٰهَاۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ رَبِّيۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقۡتِهَآ إِلَّا هُوَۚ ثَقُلَتۡ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا تَأۡتِيكُمۡ إِلَّا بَغۡتَةٗۗ يَسۡـَٔلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنۡهَاۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው:: በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም:: በሰማያትና በምድርም ከበደች:: በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው:: ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳ አድርገው ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો