Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ   આયત:
إِنَّ وَلِـِّۧيَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي نَزَّلَ ٱلۡكِتَٰبَۖ وَهُوَ يَتَوَلَّى ٱلصَّٰلِحِينَ
196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ በላቸው) «የእኔ ረዳቴ ያ ቁርኣንን ያወረደልኝ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ ይረዳልና።
અરબી તફસીરો:
وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَكُمۡ وَلَآ أَنفُسَهُمۡ يَنصُرُونَ
197. (አጋሪዎች ሆይ! ) «እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦታት ሁሉ ሊረዷችሁ ፍጽሞ አይችሉም:: ነፍሶቻቸውንም እንኳን አይረዱም።»
અરબી તફસીરો:
وَإِن تَدۡعُوهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ لَا يَسۡمَعُواْۖ وَتَرَىٰهُمۡ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ وَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ
198. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ቀናው መንገድ እንዲመሩ ብትጠሯቸው አይሰሙም። እነርሱንም የማያዩ ሲሆኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ::
અરબી તફસીરો:
خُذِ ٱلۡعَفۡوَ وَأۡمُرۡ بِٱلۡعُرۡفِ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡجَٰهِلِينَ
199. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይቅርባይነትን ያዝ:: በመልካምም እዘዝ:: ባለጌዎቹንም ተዋቸው::
અરબી તફસીરો:
وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ نَزۡغٞ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
200. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሰይጣን የተንኮል ጉትጎታ ቢያጋጥምህ በአላህ ብቻ ተጠበቅ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ إِذَا مَسَّهُمۡ طَٰٓئِفٞ مِّنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ تَذَكَّرُواْ فَإِذَا هُم مُّبۡصِرُونَ
201.እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ:: ወዲያዉም እነርሱ ተመልካቾች ይሆናሉ:
અરબી તફસીરો:
وَإِخۡوَٰنُهُمۡ يَمُدُّونَهُمۡ فِي ٱلۡغَيِّ ثُمَّ لَا يُقۡصِرُونَ
202. ወንድሞቻቸዉም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል:: ከዚያም እነርሱ አይገቱም::
અરબી તફસીરો:
وَإِذَا لَمۡ تَأۡتِهِم بِـَٔايَةٖ قَالُواْ لَوۡلَا ٱجۡتَبَيۡتَهَاۚ قُلۡ إِنَّمَآ أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ مِن رَّبِّيۚ هَٰذَا بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::
અરબી તફસીરો:
وَإِذَا قُرِئَ ٱلۡقُرۡءَانُ فَٱسۡتَمِعُواْ لَهُۥ وَأَنصِتُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
204. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ እርሱን በጥሞና አድምጡ:: ጸጥም በሉ። ይታዘንላችኋልና።
અરબી તફસીરો:
وَٱذۡكُر رَّبَّكَ فِي نَفۡسِكَ تَضَرُّعٗا وَخِيفَةٗ وَدُونَ ٱلۡجَهۡرِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡأٓصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡغَٰفِلِينَ
205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህን በሚስጥር ተናንሰህና ፈርተህ ከጩኸት በታች በሆነ ድምጽ በጥዋትና በማታ አውሳው:: ከዘንጊዎቹም አትሁን::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ ٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِهِۦ وَيُسَبِّحُونَهُۥ وَلَهُۥ يَسۡجُدُونَۤ۩
206. እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት እንኳን እርሱን ከመገዛት ፈጽሞ አይኮሩም:: ሁል ጊዜም ያወድሱታል:: ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો