Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ   આયત:
۞ يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ خُذُواْ زِينَتَكُمۡ عِندَ كُلِّ مَسۡجِدٖ وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
31. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን ጌጦቻችሁን በየመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ:: ብሉም ጠጡም:: ግን አታባክኑ:: እርሱ (አላህ) አባካኞችን አይወድምና::
અરબી તફસીરો:
قُلۡ مَنۡ حَرَّمَ زِينَةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِيٓ أَخۡرَجَ لِعِبَادِهِۦ وَٱلطَّيِّبَٰتِ مِنَ ٱلرِّزۡقِۚ قُلۡ هِيَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا خَالِصَةٗ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያችን ለባሮች የፈጠራትን የአላህን ጌጥ ከሲሳይ ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው። «እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ በትክክል ላመኑት ብቻ ስትሆን በቅርቢቱ ህይወትም ተገቢያቸው ናት።» በላቸው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::
અરબી તફસીરો:
قُلۡ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَ وَٱلۡإِثۡمَ وَٱلۡبَغۡيَ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَأَن تُشۡرِكُواْ بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗا وَأَن تَقُولُواْ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እርም ያደረገው የተገለጸም ሆነ የተደበቀን መጥፎ ስራን፣ ኃጢአትን፤ ያለ አግባብ መበደልንም፣ በእርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣኦት በአላህ ማጋራታችሁንና በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٞۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ لَا يَسۡتَأۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ
34. ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። እናም ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትንም ሰዓት አይዘገዩም። ከጊዜያቱም አይቀድሙም::
અરબી તફસીરો:
يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ إِمَّا يَأۡتِيَنَّكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَقُصُّونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِي فَمَنِ ٱتَّقَىٰ وَأَصۡلَحَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
35. (የአደም ልጆች ሆይ!) ከናንተ መካከል አንቀፆቼን የሚያነቡላችሁ መልዕክተኞች ቢመጡላችሁ ከናንተ ክህደትን የተጠነቀቁና በጎንም ተግባር የሠሩ ሁሉ ምንም ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም አያዝኑምም::
અરબી તફસીરો:
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
36. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉና ከእርሷ የኮሩ ሁሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
અરબી તફસીરો:
فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ يَنَالُهُمۡ نَصِيبُهُم مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوۡنَهُمۡ قَالُوٓاْ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالُواْ ضَلُّواْ عَنَّا وَشَهِدُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰفِرِينَ
37. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአናቅጹ ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያ ከተጻፈላቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ሲሆን ድርሻቸው ያገኛቸዋል:: የሞት መልዕክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ሆነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል:: «ከእኛ ተሰወሩብን» ይላሉ:: እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અઅરાફ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો