Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-नूर   आयत:

አልን ኑር

سُورَةٌ أَنزَلۡنَٰهَا وَفَرَضۡنَٰهَا وَأَنزَلۡنَا فِيهَآ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لَّعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
1.(ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ) ያወረድነውና በእናንተ ላይ (እንድትሰሩበት) የደነገግነው ምዕራፍ ነው:: እርሱ በርሷም ውስጥ ትገሰጹ ዘንድ ግልጽ አናቅጽን አውርደናል::
अरबी तफ़सीरें:
ٱلزَّانِيَةُ وَٱلزَّانِي فَٱجۡلِدُواْ كُلَّ وَٰحِدٖ مِّنۡهُمَا مِاْئَةَ جَلۡدَةٖۖ وَلَا تَأۡخُذۡكُم بِهِمَا رَأۡفَةٞ فِي دِينِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۖ وَلۡيَشۡهَدۡ عَذَابَهُمَا طَآئِفَةٞ مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
2. ዝሙተኛይቱ ሴትና ዝሙተኛው ወንድ ከሁለቱ እያንዳንዳቸው (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፏቸው:: በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ በእነርሱ ላይ በደነገገው በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ። ሙስሊሞች ሆይ! ቅጣታቸውንም በምትፈጽሙበት ጊዜ ከአማኞች የተወሰኑ ቡድኖች ይገኙበት::
अरबी तफ़सीरें:
ٱلزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوۡ مُشۡرِكَةٗ وَٱلزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَآ إِلَّا زَانٍ أَوۡ مُشۡرِكٞۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
3. ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛን ሴት ወይም በአላህ አጋሪን ሴት እንጂ ሌላን አያገባም (አይፈልግም) :: ዝሙተኛይቱም ሴት ዝሙተኛ ወይም በአላህ አጋሪ ወንድ እንጂ ሌላ አያገባትም (አይፈልጋትም):: ይህም በአማኞች ላይ ተከልክሏል::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَأۡتُواْ بِأَرۡبَعَةِ شُهَدَآءَ فَٱجۡلِدُوهُمۡ ثَمَٰنِينَ جَلۡدَةٗ وَلَا تَقۡبَلُواْ لَهُمۡ شَهَٰدَةً أَبَدٗاۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ
4. እነዚያ ጥብቆችን ሴቶች በዝሙት የሚሰድቡ ከዚያ በሰደቡበት አራት ምስክሮች ያላመጡ ሰማንያ ግርፋት ግረፏቸው:: ከእነርሱም ምስክርነትን ለሁልጊዜ አትቀበሉ:: እነዚያም እነርሱ አመጸኞች ናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
5. እነዚያ ከዚህ በኋላ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ:: አላህ በጣም መሓሪና አዛኝ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ أَزۡوَٰجَهُمۡ وَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ شُهَدَآءُ إِلَّآ أَنفُسُهُمۡ فَشَهَٰدَةُ أَحَدِهِمۡ أَرۡبَعُ شَهَٰدَٰتِۭ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
6. እነዚያ ሚስቶቻቻውን (በዝሙት) የሚሰድቡ ለነሱም ከነፍሶቻቸው በስተቀር ምስክሮች የሌሏቸው የሆኑ የአንዳቸው ምስክርነት ከእውነተኞች ለመሆናቸው በአላህ ስም አራት ጊዜ ምሎ መመስከር ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلۡخَٰمِسَةُ أَنَّ لَعۡنَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
7. አምስተኛይቱም ከውሸታሞች ቢሆን በእርሱ ላይ የአላህ እርግማን እንዲሰፍንበት (ምሎ መመስከር ነው)።
अरबी तफ़सीरें:
وَيَدۡرَؤُاْ عَنۡهَا ٱلۡعَذَابَ أَن تَشۡهَدَ أَرۡبَعَ شَهَٰدَٰتِۭ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
8. «እርሱም ከውሸታሞች ነው።» ብላ አራት ጊዜ በአላህ ስም መመስከሯ ከእርሷ ላይ ቅጣትን ይከላከልላታል::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلۡخَٰمِسَةَ أَنَّ غَضَبَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَآ إِن كَانَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
9. አምስተኛይቱም እርሱ ከእውነተኞች ቢሆን በርሷ ላይ የአላህ ቁጣ ይኑርባት ብላ መመስከሯ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ وَأَنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٌ حَكِيمٌ
10. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረና አላህ ጸጸትን ተቀባይና ጥበበኛ ባልሆነ ኖሮ (ውሸታሙን ሁሉ በዚሁ አለም ላይ ይገልጸው ነበር)::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-नूर
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें