Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-नूर   आयत:
وَإِذَا بَلَغَ ٱلۡأَطۡفَٰلُ مِنكُمُ ٱلۡحُلُمَ فَلۡيَسۡتَـٔۡذِنُواْ كَمَا ٱسۡتَـٔۡذَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
59. ከናንተም መካከል ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ታላላቆች እንዳስፈቀዷችሁ ያስፈቅዱ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀፆቹን ያብራራል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلۡقَوَٰعِدُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ ٱلَّٰتِي لَا يَرۡجُونَ نِكَاحٗا فَلَيۡسَ عَلَيۡهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعۡنَ ثِيَابَهُنَّ غَيۡرَ مُتَبَرِّجَٰتِۭ بِزِينَةٖۖ وَأَن يَسۡتَعۡفِفۡنَ خَيۡرٞ لَّهُنَّۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
60. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ባልቴቶች በጌጥ የተገለጹ ሳይሆኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእርሱ ኃጢአት የለባቸዉም:: ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው:: አላህም ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሁሉም አዋቂ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
لَّيۡسَ عَلَى ٱلۡأَعۡمَىٰ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡأَعۡرَجِ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرِيضِ حَرَجٞ وَلَا عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۡ أَن تَأۡكُلُواْ مِنۢ بُيُوتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ ءَابَآئِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أُمَّهَٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ إِخۡوَٰنِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَخَوَٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَعۡمَٰمِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ عَمَّٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَخۡوَٰلِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ خَٰلَٰتِكُمۡ أَوۡ مَا مَلَكۡتُم مَّفَاتِحَهُۥٓ أَوۡ صَدِيقِكُمۡۚ لَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٌ أَن تَأۡكُلُواْ جَمِيعًا أَوۡ أَشۡتَاتٗاۚ فَإِذَا دَخَلۡتُم بُيُوتٗا فَسَلِّمُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۡ تَحِيَّةٗ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ مُبَٰرَكَةٗ طَيِّبَةٗۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
61. (ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር (አይነስውር) ላይ ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከውድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእህቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት ወንድሞች አጎቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት እህቶች አክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናት ወንድሞች የሹሞቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከእናት እህቶች የሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎችን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት ብትበሉ ኃጢአት የለባችሁም:: ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የሆነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ:: ልክ እንደዚህ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል፤ ልታውቁ ይከጅላልና::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-नूर
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें