Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 高壁章   節:
قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسۡجُدَ إِذۡ أَمَرۡتُكَۖ قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ
12. አላህም «ዲያብሎስ ሆይ! ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው:: ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ:: እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው።» አለ።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ فَٱهۡبِطۡ مِنۡهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخۡرُجۡ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّٰغِرِينَ
13. (አላህም) «ከእርሷ ውረድ:: በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና:: ውጣም:: አንተ ከወራዶቹ ነህና።» አለው::
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ أَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
14. (ኢብሊስም): «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ::
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ إِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ
15. አላህ «አንተ ከሚቆዩት ነህ።» አለው።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ فَبِمَآ أَغۡوَيۡتَنِي لَأَقۡعُدَنَّ لَهُمۡ صِرَٰطَكَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
16. (ኢብሊስም) አለ: «ስላጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ።
アラビア語 クルアーン注釈:
ثُمَّ لَأٓتِيَنَّهُم مِّنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ وَعَنۡ أَيۡمَٰنِهِمۡ وَعَن شَمَآئِلِهِمۡۖ وَلَا تَجِدُ أَكۡثَرَهُمۡ شَٰكِرِينَ
17. «ከዚያም ከበስተፊቶቻቸው፤ ከየኋላቸዉም፤ ከየቀኞቻቸውና ከየግራዎቻቸዉም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ:: አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸዉም።» አለ።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ ٱخۡرُجۡ مِنۡهَا مَذۡءُومٗا مَّدۡحُورٗاۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمۡ أَجۡمَعِينَ
18. «የተጠላህ ብራሪ ስትሆን ከእርሷ ውጣ:: ከእነርሱ መካከልም አንተን ከተከተሉህ እና አንተንም ሁላችሁንም ገሀነምን በእርግጥ በእናንተ እሞላታለሁ።» አለው።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسۡكُنۡ أَنتَ وَزَوۡجُكَ ٱلۡجَنَّةَ فَكُلَا مِنۡ حَيۡثُ شِئۡتُمَا وَلَا تَقۡرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
19. ‹‹አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ እንደፈለጋችሁ ተመገቡ:: ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ:: ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና።» አላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
فَوَسۡوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيۡطَٰنُ لِيُبۡدِيَ لَهُمَا مَا وُۥرِيَ عَنۡهُمَا مِن سَوۡءَٰتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَىٰكُمَا رَبُّكُمَا عَنۡ هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةِ إِلَّآ أَن تَكُونَا مَلَكَيۡنِ أَوۡ تَكُونَا مِنَ ٱلۡخَٰلِدِينَ
20. ሰይጣንም ከሀፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁ እኮ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ኗዋሪዎቹ እንዳትሆኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም።» አላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
21. «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
فَدَلَّىٰهُمَا بِغُرُورٖۚ فَلَمَّا ذَاقَا ٱلشَّجَرَةَ بَدَتۡ لَهُمَا سَوۡءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخۡصِفَانِ عَلَيۡهِمَا مِن وَرَقِ ٱلۡجَنَّةِۖ وَنَادَىٰهُمَا رَبُّهُمَآ أَلَمۡ أَنۡهَكُمَا عَن تِلۡكُمَا ٱلشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَآ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لَكُمَا عَدُوّٞ مُّبِينٞ
22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 高壁章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる