Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 高壁章   節:
قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي نَفۡعٗا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ وَلَوۡ كُنتُ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ لَٱسۡتَكۡثَرۡتُ مِنَ ٱلۡخَيۡرِ وَمَا مَسَّنِيَ ٱلسُّوٓءُۚ إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
188. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የፈለገዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ وَجَعَلَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا لِيَسۡكُنَ إِلَيۡهَاۖ فَلَمَّا تَغَشَّىٰهَا حَمَلَتۡ حَمۡلًا خَفِيفٗا فَمَرَّتۡ بِهِۦۖ فَلَمَّآ أَثۡقَلَت دَّعَوَا ٱللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنۡ ءَاتَيۡتَنَا صَٰلِحٗا لَّنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
189. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁና ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ የፈጠረ ነው:: በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች:: ጽንሱን ይዛው ሄደች:: ባረገዘችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَلَمَّآ ءَاتَىٰهُمَا صَٰلِحٗا جَعَلَا لَهُۥ شُرَكَآءَ فِيمَآ ءَاتَىٰهُمَاۚ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
190. መልካምን ልጅ በሰጣቸዉም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَيُشۡرِكُونَ مَا لَا يَخۡلُقُ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ
191. ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩትን ፍጡሮች በአላህ ያጋራሉን?
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ لَهُمۡ نَصۡرٗا وَلَآ أَنفُسَهُمۡ يَنصُرُونَ
192. ለነርሱም መርዳትንም የማይችሉትን፤ ነፍሶቻቸውንም እንኳን የማይረዱትን ያጋራሉን?
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِن تَدۡعُوهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ لَا يَتَّبِعُوكُمۡۚ سَوَآءٌ عَلَيۡكُمۡ أَدَعَوۡتُمُوهُمۡ أَمۡ أَنتُمۡ صَٰمِتُونَ
193. ወደ ቅን መንገድ ብትጠሯቸዉም አይከተሏችሁም:: ብትጠሯቸው ወይም ዝምተኞች ብትሆኑም በእናንተ ላይ እኩል ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمۡثَالُكُمۡۖ فَٱدۡعُوهُمۡ فَلۡيَسۡتَجِيبُواْ لَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
194. (ከሀዲያን ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦቶች ብጤዎቻችሁ የአላህ ባሮች ናቸው:: እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ጥሯቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ:: (መመለስ አይችሉም።)
アラビア語 クルアーン注釈:
أَلَهُمۡ أَرۡجُلٞ يَمۡشُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ أَيۡدٖ يَبۡطِشُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ أَعۡيُنٞ يُبۡصِرُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ ءَاذَانٞ يَسۡمَعُونَ بِهَاۗ قُلِ ٱدۡعُواْ شُرَكَآءَكُمۡ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ
195. ለእነርሱ የሚሄዱባቸው እግሮች አሏቸውን? ወይስ የሚጨብጡባቸው እጆች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸዉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያጋራችኃቸውን ጥሩና ከዚያም አሲሩብኝ:: ጊዜም አትስጡኝ።» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 高壁章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる