Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ


ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូសុហ្វ   អាយ៉ាត់:
قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأۡخُذَ إِلَّا مَن وَجَدۡنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّظَٰلِمُونَ
79. «ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን:: እኛ ያን ባደረግን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን።» አለ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَمَّا ٱسۡتَيۡـَٔسُواْ مِنۡهُ خَلَصُواْ نَجِيّٗاۖ قَالَ كَبِيرُهُمۡ أَلَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ أَبَاكُمۡ قَدۡ أَخَذَ عَلَيۡكُم مَّوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبۡلُ مَا فَرَّطتُمۡ فِي يُوسُفَۖ فَلَنۡ أَبۡرَحَ ٱلۡأَرۡضَ حَتَّىٰ يَأۡذَنَ لِيٓ أَبِيٓ أَوۡ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ لِيۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ
80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيكُمۡ فَقُولُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبۡنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدۡنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمۡنَا وَمَا كُنَّا لِلۡغَيۡبِ حَٰفِظِينَ
81. «ወደ አባታችሁ ተመለሱ:: በሉትም: ‹አባታችን ሆይ ልጅህ ሰረቀ፤ ባወቅነዉም ነገር እንጂ አልመሰከርንም:: ሩቁንም ነገር ምስጢሩን አዋቂዎች አልነበርንም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَسۡـَٔلِ ٱلۡقَرۡيَةَ ٱلَّتِي كُنَّا فِيهَا وَٱلۡعِيرَ ٱلَّتِيٓ أَقۡبَلۡنَا فِيهَاۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ
82. «‹ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።›»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٌۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَنِي بِهِمۡ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ
83. ያዕቁብም፡- «አይደለም። ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላቸሁና ሠራችሁት እንጂ:: እናም መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: እነርሱን ሁሉንም የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል:: እነሆ እርሱ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبۡيَضَّتۡ عَيۡنَاهُ مِنَ ٱلۡحُزۡنِ فَهُوَ كَظِيمٞ
84. ከነርሱም ዞር አለና፡- «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ:: ዓይኖቹም ከሐዘን የተነሳ ነጡ:: እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُواْ تَٱللَّهِ تَفۡتَؤُاْ تَذۡكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوۡ تَكُونَ مِنَ ٱلۡهَٰلِكِينَ
85. እነርሱም፡- «በአላህ እንምላለን! ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ إِنَّمَآ أَشۡكُواْ بَثِّي وَحُزۡنِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
86. «ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ በኩል የማታውቁትን ነገር እኔ አውቃለሁና።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូសុហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ