Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូសុហ្វ   អាយ៉ាត់:
وَٱتَّبَعۡتُ مِلَّةَ ءَابَآءِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَۚ مَا كَانَ لَنَآ أَن نُّشۡرِكَ بِٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۚ ذَٰلِكَ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ عَلَيۡنَا وَعَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ
38. «የአባቶቼንም የኢብራሂምን፤ የኢስሐቅንና የያዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ:: ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም:: ያ አለማጋራት በእኛ ላይና በሰዎች ላይ የአላህ ችሮታ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰصَٰحِبَيِ ٱلسِّجۡنِ ءَأَرۡبَابٞ مُّتَفَرِّقُونَ خَيۡرٌ أَمِ ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ
39. «የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊውና አንዱ አላህ?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ أَسۡمَآءٗ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِ أَمَرَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلۡقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
40. «ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ የጠራችኋቸውን ስሞች እንጂ አትገዙም። አላህ በእርሷ ምንም አስረጂ አላወረደም። ፍርዱ የአላህ እንጂ ሌላ አይደለም:: እርሱን እንጂ ሌላን እንዳትገዙም አዟል:: ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰصَٰحِبَيِ ٱلسِّجۡنِ أَمَّآ أَحَدُكُمَا فَيَسۡقِي رَبَّهُۥ خَمۡرٗاۖ وَأَمَّا ٱلۡأٓخَرُ فَيُصۡلَبُ فَتَأۡكُلُ ٱلطَّيۡرُ مِن رَّأۡسِهِۦۚ قُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ٱلَّذِي فِيهِ تَسۡتَفۡتِيَانِ
41. «የአስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ንጉሡን ጠጅ ያጠጣል። ሌላውም ይሰቀላል:: ከራሱም በራሪ አሞራ ትበላለች:: ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ لِلَّذِي ظَنَّ أَنَّهُۥ نَاجٖ مِّنۡهُمَا ٱذۡكُرۡنِي عِندَ رَبِّكَ فَأَنسَىٰهُ ٱلشَّيۡطَٰنُ ذِكۡرَ رَبِّهِۦ فَلَبِثَ فِي ٱلسِّجۡنِ بِضۡعَ سِنِينَ
42. ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ አለው፡፡ ጌታውንም ከማስታወስ ሰይጣን አስረሳው፡፡ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ ቆየ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ إِنِّيٓ أَرَىٰ سَبۡعَ بَقَرَٰتٖ سِمَانٖ يَأۡكُلُهُنَّ سَبۡعٌ عِجَافٞ وَسَبۡعَ سُنۢبُلَٰتٍ خُضۡرٖ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٖۖ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَأُ أَفۡتُونِي فِي رُءۡيَٰيَ إِن كُنتُمۡ لِلرُّءۡيَا تَعۡبُرُونَ
43. ንጉሡም «እኔ ሰባት የሰቡ ላሞችን ሰባት የከሱ ላሞች ሲበሉዋቸው፤ ሰባት ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆችን ስብርብር ሲያደርጉ በሕልሜ አየሁ:: እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልም መፍታት የምታውቁ ከሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូសុហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ