Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: លុកម៉ាន   អាយ៉ាត់:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا لُقۡمَٰنَ ٱلۡحِكۡمَةَ أَنِ ٱشۡكُرۡ لِلَّهِۚ وَمَن يَشۡكُرۡ فَإِنَّمَا يَشۡكُرُ لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٞ
12. ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው:: አላህን አመስግን አልነዉም:: ያመሰገነም ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው:: የካደም ሰውም (በራሱ ላይ ነው::) አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قَالَ لُقۡمَٰنُ لِٱبۡنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَيَّ لَا تُشۡرِكۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّ ٱلشِّرۡكَ لَظُلۡمٌ عَظِيمٞ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን «ልጄ ሆይ! በአላህ አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።» ያለውን አስታውስ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ حَمَلَتۡهُ أُمُّهُۥ وَهۡنًا عَلَىٰ وَهۡنٖ وَفِصَٰلُهُۥ فِي عَامَيۡنِ أَنِ ٱشۡكُرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيۡكَ إِلَيَّ ٱلۡمَصِيرُ
14. ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው:: ጡት መጣያዉም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው:: «ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን" በማለትም አዘዝነው። መመለሻው ወደ እኔ ብቻ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشۡرِكَ بِي مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٞ فَلَا تُطِعۡهُمَاۖ وَصَاحِبۡهُمَا فِي ٱلدُّنۡيَا مَعۡرُوفٗاۖ وَٱتَّبِعۡ سَبِيلَ مَنۡ أَنَابَ إِلَيَّۚ ثُمَّ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
15. ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው:: ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ (አልነው)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰبُنَيَّ إِنَّهَآ إِن تَكُ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٖ فَتَكُن فِي صَخۡرَةٍ أَوۡ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَوۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَأۡتِ بِهَا ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٞ
16. (ሉቅማንም አለ:) «ልጄ ሆይ! የእርሷ (መጥፎም ይሁን በጎ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል እንኳን ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል:: አላህ ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰبُنَيَّ أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ وَأۡمُرۡ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَٱنۡهَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَآ أَصَابَكَۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ
17. «ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚያዙ ወሳኝ ነገሮች ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا تُصَعِّرۡ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخۡتَالٖ فَخُورٖ
18. «ጉንጭህንም በኩራት ከሰዎች አታዙር:: በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ:: አላህ ተንበጥራሪን (ኮራተኛ) ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱقۡصِدۡ فِي مَشۡيِكَ وَٱغۡضُضۡ مِن صَوۡتِكَۚ إِنَّ أَنكَرَ ٱلۡأَصۡوَٰتِ لَصَوۡتُ ٱلۡحَمِيرِ
19. «በአካሄድህም መካከለኛ ሁን:: ከድምጽህም ዝቅ አድርግ:: ከድምፆች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: លុកម៉ាន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ