Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ   អាយ៉ាត់:
وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ وَٱلنَّصَٰرَىٰ نَحۡنُ أَبۡنَٰٓؤُاْ ٱللَّهِ وَأَحِبَّٰٓؤُهُۥۚ قُلۡ فَلِمَ يُعَذِّبُكُم بِذُنُوبِكُمۖ بَلۡ أَنتُم بَشَرٞ مِّمَّنۡ خَلَقَۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ
18. አይሁድና ክርስቲያኖች «እኛ የአላህ ልጆችና ወዳጆቹ ነን።» አሉ። «ታዲያ በኃጢአቶቻችሁ ለምን ይቀጣችኋል? አይደላችሁም:: እናንተ ከፈጠራቸው መካከል የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ:: አላህ ለሚሻው ይምራል:: የሚሻውን ይቀጣል:: የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: መመለሻም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ قَدۡ جَآءَكُمۡ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمۡ عَلَىٰ فَتۡرَةٖ مِّنَ ٱلرُّسُلِ أَن تَقُولُواْ مَا جَآءَنَا مِنۢ بَشِيرٖ وَلَا نَذِيرٖۖ فَقَدۡ جَآءَكُم بَشِيرٞ وَنَذِيرٞۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
19. እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «አብሳሪና አስፈራሪ አልመጣልንም።» እንዳትሉ መልዕክተኞቻችን በተቋረጡበት ጊዜ መመሪያዎችን የሚያብራራ ሆኖ መልዕክተኛችን ሙሐመድ በእርግጥ መጣላችሁ:: አብሳሪና አስፈራሪም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ جَعَلَ فِيكُمۡ أَنۢبِيَآءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكٗا وَءَاتَىٰكُم مَّا لَمۡ يُؤۡتِ أَحَدٗا مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
20. ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ አስታውሱ፣ በውስጣችሁ ነብያትን ባደረገ፤ ነገስታትም ባደረጋችሁና ከአለማት ህዝብ ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰقَوۡمِ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡأَرۡضَ ٱلۡمُقَدَّسَةَ ٱلَّتِي كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمۡ وَلَا تَرۡتَدُّواْ عَلَىٰٓ أَدۡبَارِكُمۡ فَتَنقَلِبُواْ خَٰسِرِينَ
21. ‹‹ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ:: ወደ ኋላችሁም አትመለሱ:: ከሳሪዎች ሆናችሁ ትመለሳላችሁና›› (ባሉ ጊዜ የሆነዉን አስታውስ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ فِيهَا قَوۡمٗا جَبَّارِينَ وَإِنَّا لَن نَّدۡخُلَهَا حَتَّىٰ يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا فَإِن يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا فَإِنَّا دَٰخِلُونَ
22. «ሙሳ ሆይ! በእርሷ ውስጥ ሀያላን ህዝቦች ስላሉ ከእርሷ እስከሚወጡ ድረስ ፈጽሞ አንገባትም:: ከወጡ ግን ገቢዎች ነን።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ رَجُلَانِ مِنَ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمَا ٱدۡخُلُواْ عَلَيۡهِمُ ٱلۡبَابَ فَإِذَا دَخَلۡتُمُوهُ فَإِنَّكُمۡ غَٰلِبُونَۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓاْ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
23. ከእነዚያ አላህን ከሚፈሩትና አላህ ጸጋውን ከለገሰላቸው ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች «በእነርሱ በሀያሎቹ ላይ በሩን ግቡ:: በገባችሁ ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ:: ትክክለኛ አማኞችም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አሏቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ