Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ   អាយ៉ាត់:
يُرِيدُونَ أَن يَخۡرُجُواْ مِنَ ٱلنَّارِ وَمَا هُم بِخَٰرِجِينَ مِنۡهَاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّقِيمٞ
37. ከእሳት ሊወጡ ይፈልጋሉ:: እነርሱ ግን ሁልጊዜም ከእርሷ ወጪዎች አይደሉም:: ለእነርሱ ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلسَّارِقُ وَٱلسَّارِقَةُ فَٱقۡطَعُوٓاْ أَيۡدِيَهُمَا جَزَآءَۢ بِمَا كَسَبَا نَكَٰلٗا مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
38. የወንድ ሌባንና የሴት ሌባን ለሰሩት ወንጀል ከአላህ የሆነ መቀጫ ሲሆን እጆቻቸውን ቁረጡ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَمَن تَابَ مِنۢ بَعۡدِ ظُلۡمِهِۦ وَأَصۡلَحَ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَتُوبُ عَلَيۡهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ
39. ከበደለ በኋላ የተጸጸተና ስራውን ያሳመረ ሁሉ አላህ ጸጸቱን ይቀበለዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእሱ ብቻ መሆኑን አላወክምን? የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ لَا يَحۡزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡكُفۡرِ مِنَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِأَفۡوَٰهِهِمۡ وَلَمۡ تُؤۡمِن قُلُوبُهُمۡۛ وَمِنَ ٱلَّذِينَ هَادُواْۛ سَمَّٰعُونَ لِلۡكَذِبِ سَمَّٰعُونَ لِقَوۡمٍ ءَاخَرِينَ لَمۡ يَأۡتُوكَۖ يُحَرِّفُونَ ٱلۡكَلِمَ مِنۢ بَعۡدِ مَوَاضِعِهِۦۖ يَقُولُونَ إِنۡ أُوتِيتُمۡ هَٰذَا فَخُذُوهُ وَإِن لَّمۡ تُؤۡتَوۡهُ فَٱحۡذَرُواْۚ وَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ فِتۡنَتَهُۥ فَلَن تَمۡلِكَ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔاۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَمۡ يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يُطَهِّرَ قُلُوبَهُمۡۚ لَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا خِزۡيٞۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٞ
41. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሆነው ልቦቻቸው ሳያምኑ በአፎቻቸው ብቻ «አመንን» ካሉት አስመሳዮችና ከእነዚያም አይሁዶቹ አያሳዝኑህ:: እነርሱ ውሸትን ብቻ አድማጮች ናቸውና:: ገና ወደ አንተ ላልመጡ ለሌሎች ሕዝቦች አድማጮች ናቸው:: ንግግሮችንም ከስፍሮቻቸው ወደ ሌላ በመቀየር መልዕክት ያጣምማሉ። «ይህንን የተጣመመውን ከተሰጣችሁ ያዙት:: ካልተሰጣችሁም ተጠንቀቁ።» ይላሉ:: አላህ መፈተንን የሚሻበትን ሰው ሁሉ ለእርሱ ከአላህ ለመከላከል ፍጹም አትችልም:: እነዚያ ማለት አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ሰዎች ናቸው:: ለእነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: ለእነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለምም ሌላ ከባድ ቅጣት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ