Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: بقرہ   آیت:
وَٱتَّبَعُواْ مَا تَتۡلُواْ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلۡكِ سُلَيۡمَٰنَۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيۡمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُواْ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحۡرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلۡمَلَكَيۡنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنۡ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحۡنُ فِتۡنَةٞ فَلَا تَكۡفُرۡۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنۡهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيۡنَ ٱلۡمَرۡءِ وَزَوۡجِهِۦۚ وَمَا هُم بِضَآرِّينَ بِهِۦ مِنۡ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡۚ وَلَقَدۡ عَلِمُواْ لَمَنِ ٱشۡتَرَىٰهُ مَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنۡ خَلَٰقٖۚ وَلَبِئۡسَ مَا شَرَوۡاْ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمۡۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
102. (የአላህን መጽሐፍ አንቀበልም ያሉ አይሁዶች) ሰይጣናት በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ:: ሱለይማን ጌታውን አልካደም::( ድግምተኛ አልነበረም::) ሰይጣናት ግን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲሆኑ በጌታቸው ካዱ:: በባቢሎን (በባቢል) በሁለቱ መላዕክት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደውን ተከተሉ:: (ሀሩትና ማሩት) ግን «እኛ ለእናንተ መፍፈተኛዎች ነንና በጌታህ አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም ነበር:: ከእነርሱም በባልና በሚስቱ መካከል የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ:: እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድንም በርሱ አይጎዱም:: (ድግምት የሚማሩ ሁሉ) የሚጎዳቸውንና ቅንጣት የማይጠቅማቸውን ትምህርት ይማራሉ:: የገዛው በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ ተገንዝበዋል:: ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ምንኛ ከፋ:: የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልተገበሩት ነበር::)
عربی تفاسیر:
وَلَوۡ أَنَّهُمۡ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَمَثُوبَةٞ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ خَيۡرٞۚ لَّوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
103. በአላህ ባመኑና የከለከለውን በተጠነቀቁ ኖሮ (መልካምን በተመነዱ ነበር):: የሚያውቁ ቢሆኑ ከአላህ ዘንድ የሚገኘው ምንዳ (ነፍሶቻቸውን ከሚሸጡበት) በላጭ ነው::
عربی تفاسیر:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَقُولُواْ رَٰعِنَا وَقُولُواْ ٱنظُرۡنَا وَٱسۡمَعُواْۗ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٞ
104. (እናንተያመናችሁ ሆይ!) ለነብዩ "ራዒና" አትበሉ:: “ኡንዙርና” (ተመልከተን) በሉ:: የምትባሉትንም ስሙ:: ለካሃዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ተዘጋጅቶላቸዋል::
عربی تفاسیر:
مَّا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ وَلَا ٱلۡمُشۡرِكِينَ أَن يُنَزَّلَ عَلَيۡكُم مِّنۡ خَيۡرٖ مِّن رَّبِّكُمۡۚ وَٱللَّهُ يَخۡتَصُّ بِرَحۡمَتِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ
105. እነዚያ ከመጽሐፍ ባለቤቶችም ሆነ ከአጋሪዎች በአላህ የካዱት በእናንተ ላይ ከጌታችሁ የሆነ መልካም ነገር መውረዱን አይወዱም:: አላህም በችሮታው (በነብይነት) የሚፈልገውን ሰው ይመርጣል:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: بقرہ
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں