Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: بقرہ   آیت:
وَإِذۡ يَرۡفَعُ إِبۡرَٰهِـۧمُ ٱلۡقَوَاعِدَ مِنَ ٱلۡبَيۡتِ وَإِسۡمَٰعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلۡ مِنَّآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
127. ኢብራሂምና ኢስማዒልም (እንደሚከተለው) በማለት እየለመኑ የካዕባን ህንፃ (መሰረቶች ግንባታ) ባሳደጉ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ): «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበለን:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።
عربی تفاسیر:
رَبَّنَا وَٱجۡعَلۡنَا مُسۡلِمَيۡنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَآ أُمَّةٗ مُّسۡلِمَةٗ لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبۡ عَلَيۡنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
128. «ጌታችን ሆይ! ላንተው ፍጹም ታዛዦችም አድርገን:: ከዘሮቻችንም ላንተ ፍጹም ታዛዦች ሕዝቦችን አስነሳ:: አምልኳዊ ክንውኖቻችንንም አሳውቀን:: ንሰሀችንን ተቀበለን:: ጸጸትን ተቀባይና ሩህሩህ አንተ ብቻ ነህና::
عربی تفاسیر:
رَبَّنَا وَٱبۡعَثۡ فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَيُزَكِّيهِمۡۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
129. «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸው ከእነርሱ የሆነን መልዕክተኛ፤ በእነርሱ ላይ አናቅጽህን የሚያነብላቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውንም ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክላቸው:: አሸናፊዉና ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና።» የሚሉም ሲሆኑ (ከዕባን ገነቡ)።
عربی تفاسیر:
وَمَن يَرۡغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبۡرَٰهِـۧمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفۡسَهُۥۚ وَلَقَدِ ٱصۡطَفَيۡنَٰهُ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَإِنَّهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
130. ከኢብራሂምም እምነት ሞኝ ካልሆነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማን ነው? በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ (ለተልዕኳችን) መረጥነው:: በመጨረሻይቱ ዓለምም እርሱ ከመልካሞቹ ነው።
عربی تفاسیر:
إِذۡ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسۡلِمۡۖ قَالَ أَسۡلَمۡتُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
131. ጌታው ለእርሱ «ፍጹም ታዛዥ ሁን።» ባለው ጊዜ «ለዓለማቱ ጌታ ታዛዥ ሆኛለሁ።» አለ።
عربی تفاسیر:
وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبۡرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعۡقُوبُ يَٰبَنِيَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصۡطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسۡلِمُونَ
132. ኢብራሂምም ልጆቹን በተመሳሳይ አዘዘ:: የዕቁብም እንደዚሁ በዚሁ ጉዳይ ልጆቹን አዘዘ:: (እንዲህም አለ) «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሀይማኖትን መረጠ:: ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ እንዳትሞቱ።» አላቸው።
عربی تفاسیر:
أَمۡ كُنتُمۡ شُهَدَآءَ إِذۡ حَضَرَ يَعۡقُوبَ ٱلۡمَوۡتُ إِذۡ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعۡبُدُونَ مِنۢ بَعۡدِيۖ قَالُواْ نَعۡبُدُ إِلَٰهَكَ وَإِلَٰهَ ءَابَآئِكَ إِبۡرَٰهِـۧمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ إِلَٰهٗا وَٰحِدٗا وَنَحۡنُ لَهُۥ مُسۡلِمُونَ
133. የዕቆብም ለጣዕረ ሞት በተዳረገበት ጊዜና ለልጆቹ «ከእኔ በኋላ ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ ነበራችሁን? እነርሱም «አንድ የሆነውን አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን፤ የኢስማዒልንና የኢስሃቅንም አምላክ እንገዛለን:: እኛም ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች ሆነን እናመልከዋለን።» አሉ።
عربی تفاسیر:
تِلۡكَ أُمَّةٞ قَدۡ خَلَتۡۖ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَلَكُم مَّا كَسَبۡتُمۡۖ وَلَا تُسۡـَٔلُونَ عَمَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
134. እነኝህ (ከላይ የተወሱት ህዝቦች) በእርግጥ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱም የስራቸው ምንዳ አላቸው:: ለእናንተም የስራችሁ (ምንዳ) አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት በነበረው ፈጽሞ አትጠየቁም::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: بقرہ
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں