Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Học viện Châu Phi * - Mục lục các bản dịch

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Ý nghĩa nội dung Chương: Taha   Câu:

ጣሃ

طه
1. ጧሃ፤
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
مَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لِتَشۡقَىٰٓ
2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን አንድትቸገር ባንተ ላይ አላወረድንም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِلَّا تَذۡكِرَةٗ لِّمَن يَخۡشَىٰ
3. አላህን ለሚፈራ ሁሉ መገሠጫ ይሆን ዘንድ እንጂ
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
تَنزِيلٗا مِّمَّنۡ خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ وَٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلۡعُلَى
4. ቁርኣን ምድርንና የላይኛዎቹን (የተከበሩ) ሰማያትን ከፈጠረ አምላክ ተወረደ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ
5.እርሱ አዛኙ ጌታ (አር-ረህማን) በዐርሹ ላይ ከፍ አለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَمَا تَحۡتَ ٱلثَّرَىٰ
6. በሰማያት፤በምድርና በመካከላቸዉም ያለው ከአፈር በታችም ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَإِن تَجۡهَرۡ بِٱلۡقَوۡلِ فَإِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلسِّرَّ وَأَخۡفَى
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው።) እርሱ ምስጢርን ከዚያም በጣም የተደበቀንም ያውቃልና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ
8.አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ለእርሱ መልካሞች የሆኑ አያሌ ስሞች አሉት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَهَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ
9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ (ታሪክ) መጥቶሃልን (ደርሶሃልን)?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِذۡ رَءَا نَارٗا فَقَالَ لِأَهۡلِهِ ٱمۡكُثُوٓاْ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا لَّعَلِّيٓ ءَاتِيكُم مِّنۡهَا بِقَبَسٍ أَوۡ أَجِدُ عَلَى ٱلنَّارِ هُدٗى
10. እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ «(እዚህ) ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ፤ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِيَ يَٰمُوسَىٰٓ
11. እናም ወደ እርሷ በመጣ ጊዜ (እንዲህ) በማለት ተጠራ: «ሙሳ ሆይ!
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنِّيٓ أَنَا۠ رَبُّكَ فَٱخۡلَعۡ نَعۡلَيۡكَ إِنَّكَ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوٗى
12. «እኔ ጌታህ ነኝ። ጫማዎችህን አውልቅ፤ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَنَا ٱخۡتَرۡتُكَ فَٱسۡتَمِعۡ لِمَا يُوحَىٰٓ
13. «እኔም መረጥኩህ ስለ ሆነም የሚወረድልህን ነገር በደንብ አዳምጥ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّنِيٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعۡبُدۡنِي وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكۡرِيٓ
14. «እኔ አላህ ነኝ። ያለ እኔ ትክክለኛ አምላክ የለምና እኔን ብቻ ተገዛኝ:: ሶላትንም እኔን ለማውሳት በአግባቡ ስገድ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّ ٱلسَّاعَةَ ءَاتِيَةٌ أَكَادُ أُخۡفِيهَا لِتُجۡزَىٰ كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا تَسۡعَىٰ
15. «ነፍስ ሁሉ በምትሰራው ነገር ትመነዳ ዘንድ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት። የትንሳኤውን ወሬ ልደብቃት እቀርባለሁ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَلَا يَصُدَّنَّكَ عَنۡهَا مَن لَّا يُؤۡمِنُ بِهَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَتَرۡدَىٰ
16. (ሙሳ ሆይ!) «በእርሷ የማያምንና ዝንባሌውን የሚከተል ሰው ሁሉ ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَا تِلۡكَ بِيَمِينِكَ يَٰمُوسَىٰ
17. (ሙሳ ሆይ!) «ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት?» (ተባለ)።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ هِيَ عَصَايَ أَتَوَكَّؤُاْ عَلَيۡهَا وَأَهُشُّ بِهَا عَلَىٰ غَنَمِي وَلِيَ فِيهَا مَـَٔارِبُ أُخۡرَىٰ
18. «እርሷ በትሬ ናት:: በእርሷም እደገፍባታለሁ:: በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ:: በእርሷ ሌሎች ጉዳዮችም አሉኝ።» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ أَلۡقِهَا يَٰمُوسَىٰ
19. አላህም «ሙሳ ሆይ! እስቲ ጣላት።» አለው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَلۡقَىٰهَا فَإِذَا هِيَ حَيَّةٞ تَسۡعَىٰ
20.ሙሳም ጣላትና፤ ወዲያዉም እርሷ የምትሮጥ እባብ ሆነች::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ خُذۡهَا وَلَا تَخَفۡۖ سَنُعِيدُهَا سِيرَتَهَا ٱلۡأُولَىٰ
21.አላህም አለው: «ሙሳ ሆይ! ያዛት አትፍራም ወደ መጀመሪያ ጠባይዋ እንመልሳታለን።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱضۡمُمۡ يَدَكَ إِلَىٰ جَنَاحِكَ تَخۡرُجۡ بَيۡضَآءَ مِنۡ غَيۡرِ سُوٓءٍ ءَايَةً أُخۡرَىٰ
22. «እጅህንም ወደ ብብትህ አስገባ:: ሌላ ተዓምር ስትሆን ያለ ምንም ችግር ነጭ ሆና ትወጣለችና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لِنُرِيَكَ مِنۡ ءَايَٰتِنَا ٱلۡكُبۡرَى
23. (ሙሳ ሆይ!) «ከተዓምራቶቻችን ታላቋን እናሳይህ ዘንድ ይህን ፈጸምን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱذۡهَبۡ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
24. (ሙሳ ሆይ!) «ወደ ፈርዖን ሂድ:: እርሱ ወሰን (ድንበር) አልፏልና።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ رَبِّ ٱشۡرَحۡ لِي صَدۡرِي
25. ሙሳም አለ: «ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَيَسِّرۡ لِيٓ أَمۡرِي
26. «ጉዳዬንም አግራልኝ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱحۡلُلۡ عُقۡدَةٗ مِّن لِّسَانِي
27. «የምላሴን መኮላተፍም አስወግድልኝ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَفۡقَهُواْ قَوۡلِي
28. «ንግግሬን ይረዱ ዘንድ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱجۡعَل لِّي وَزِيرٗا مِّنۡ أَهۡلِي
29. «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
هَٰرُونَ أَخِي
30. «ወንድሜን ሃሩንን
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱشۡدُدۡ بِهِۦٓ أَزۡرِي
31. «ኃይሌንም በእርሱ አበርታልኝ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَشۡرِكۡهُ فِيٓ أَمۡرِي
32. «በነገሬም አጋራው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
كَيۡ نُسَبِّحَكَ كَثِيرٗا
33. «በብዛት እንድናጠራህና
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَنَذۡكُرَكَ كَثِيرًا
34. «በብዛት እንድናወሳህ
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّكَ كُنتَ بِنَا بَصِيرٗا
35. «አንተ በእኛ ነገር አዋቂ ነህና።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ قَدۡ أُوتِيتَ سُؤۡلَكَ يَٰمُوسَىٰ
36. አላህም አለ: «ሙሳ ሆይ! ልመናህ በእርግጥ ተቀባይነትን አገኝቷል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَيۡكَ مَرَّةً أُخۡرَىٰٓ
37. «ሙሳ ሆይ! በሌላም ጊዜ ባንተ ላይ በእርግጥ ውለታን ውለናል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِذۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ أُمِّكَ مَا يُوحَىٰٓ
38. «ለእናትህ በራእይ ባሳወቅን ጊዜ ነው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَنِ ٱقۡذِفِيهِ فِي ٱلتَّابُوتِ فَٱقۡذِفِيهِ فِي ٱلۡيَمِّ فَلۡيُلۡقِهِ ٱلۡيَمُّ بِٱلسَّاحِلِ يَأۡخُذۡهُ عَدُوّٞ لِّي وَعَدُوّٞ لَّهُۥۚ وَأَلۡقَيۡتُ عَلَيۡكَ مَحَبَّةٗ مِّنِّي وَلِتُصۡنَعَ عَلَىٰ عَيۡنِيٓ
39. «‹ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገቢው እርሱንም (ሳጥኑን) በባህር ላይ ጣይው፤ ባህሩም በዳርቻው ይጥለዋል (ይተፋዋል):: ለእኔም ለእርሱም ጠላት የሆነ ሰው ይይዘዋልና› በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)። ልትወደድና በዐይኔ እይታ (በእኔም ጥበቃ) ታድግ ዘንድ ባንተ ላይም ከእኔ የሆነ መወደድን ጣልኩብህ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِذۡ تَمۡشِيٓ أُخۡتُكَ فَتَقُولُ هَلۡ أَدُلُّكُمۡ عَلَىٰ مَن يَكۡفُلُهُۥۖ فَرَجَعۡنَٰكَ إِلَىٰٓ أُمِّكَ كَيۡ تَقَرَّ عَيۡنُهَا وَلَا تَحۡزَنَۚ وَقَتَلۡتَ نَفۡسٗا فَنَجَّيۡنَٰكَ مِنَ ٱلۡغَمِّ وَفَتَنَّٰكَ فُتُونٗاۚ فَلَبِثۡتَ سِنِينَ فِيٓ أَهۡلِ مَدۡيَنَ ثُمَّ جِئۡتَ عَلَىٰ قَدَرٖ يَٰمُوسَىٰ
40. «እህትህ በምትሄድና ‹የሚያሳድገውን ሰው ላመላክታችሁን?› ባለች ጊዜ (መወደድን ጣልኩብህ):: ወደ እናትህም ዓይኗ እንዲረጋና እርሷ እንዳታዝንም መለስንህ:: ነፍስንም ገደልክ ከጭንቅም አዳንንህ:: ፈተናዎችንም ፈተንህ:: በመድየን ቤተሰቦችም ውስጥ ብዙ ዓመታትን ተቀመጥክ:: ከዚያ ሙሳ ሆይ! በተወሰነ ጊዜ ላይ መጣህ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱصۡطَنَعۡتُكَ لِنَفۡسِي
41. «ለራሴም ለመልዕክተኝነት መረጥኩህ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱذۡهَبۡ أَنتَ وَأَخُوكَ بِـَٔايَٰتِي وَلَا تَنِيَا فِي ذِكۡرِي
42. «አንተና ወንድምህ በተዓምራቴ ሆናችሁ ሂዱ:: እኔንም ከማውሳትም አትቦዝኑ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱذۡهَبَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
43. «ወደ ፈርዖን ሂዱ:: እርሱ ወሰን አልፏልና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَقُولَا لَهُۥ قَوۡلٗا لَّيِّنٗا لَّعَلَّهُۥ يَتَذَكَّرُ أَوۡ يَخۡشَىٰ
44. «እርሱ ምን አልባትም ይገሰጥ ወይም ይፈራ ዘንድ:: ለእርሱ ለስላሳን ቃል ተናገሩት።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَا رَبَّنَآ إِنَّنَا نَخَافُ أَن يَفۡرُطَ عَلَيۡنَآ أَوۡ أَن يَطۡغَىٰ
45. «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ክፋት በመስራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን።» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ لَا تَخَافَآۖ إِنَّنِي مَعَكُمَآ أَسۡمَعُ وَأَرَىٰ
46. አላህም አለ: «እኔ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ:: የሚለውንም ሁሉ እሰማለሁ። የሚፈጸመዉንም አያለሁም።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأۡتِيَاهُ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرۡسِلۡ مَعَنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَلَا تُعَذِّبۡهُمۡۖ قَدۡ جِئۡنَٰكَ بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّكَۖ وَٱلسَّلَٰمُ عَلَىٰ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلۡهُدَىٰٓ
47. እናም ወደ እርሱም ሂዱና (እንዲህ) በሉት: ‹እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነንና የኢስራኢልን ልጆች ሁሉ ከእኛ ጋር ልቀቅ። አታሰቃያቸዉም:: ከጌታህ በሆነው ተዓምር በእርግጥ መጥተንሃልና:: ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّا قَدۡ أُوحِيَ إِلَيۡنَآ أَنَّ ٱلۡعَذَابَ عَلَىٰ مَن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
48. «‹እነሆ የአላህ ቅጣት እውነትን ባስተባበለና እምቢ ባለ ሰው ላይ እንደሆነ በእርግጥ አያሌ መልዕክት ተወረደልን።› በሉት።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ فَمَن رَّبُّكُمَا يَٰمُوسَىٰ
49. ፈርዖንም «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው?» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ رَبُّنَا ٱلَّذِيٓ أَعۡطَىٰ كُلَّ شَيۡءٍ خَلۡقَهُۥ ثُمَّ هَدَىٰ
50. «ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚያስፈልገውን ቅርጹንና ባህሪውን የሰጠው ከዚያም ሁሉንም ለተፈጠረለት የመራው ነው።» አለው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ فَمَا بَالُ ٱلۡقُرُونِ ٱلۡأُولَىٰ
51. ፈርዖንም «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ህዝቦች ሁኔታስ ምንድን ነው?» አለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ عِلۡمُهَا عِندَ رَبِّي فِي كِتَٰبٖۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنسَى
52. ሙሳም «የዚህ ዕውቀት እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው:: ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም።» አለው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ مَهۡدٗا وَسَلَكَ لَكُمۡ فِيهَا سُبُلٗا وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦٓ أَزۡوَٰجٗا مِّن نَّبَاتٖ شَتَّىٰ
53. ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ ውሃንም ከሰማይ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም ከተለያየ በቃይ ዓይነቶችን አወጣንላችሁ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
كُلُواْ وَٱرۡعَوۡاْ أَنۡعَٰمَكُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّأُوْلِي ٱلنُّهَىٰ
54. ለራሳችሁ ብሉ:: እንስሳዎቻችሁንም አግጡ:: (ባዮች ሆነን አወጣንላችሁ።) በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ ተዐምራት አለበት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ مِنۡهَا خَلَقۡنَٰكُمۡ وَفِيهَا نُعِيدُكُمۡ وَمِنۡهَا نُخۡرِجُكُمۡ تَارَةً أُخۡرَىٰ
55. (ሰዎች ሆይ!) ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ:: ወደ እርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን:: ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ أَرَيۡنَٰهُ ءَايَٰتِنَا كُلَّهَا فَكَذَّبَ وَأَبَىٰ
56.ተዓምራቶቻችንንም ሁሏንም ለፈርዖን በእርግጥ አሳየነው:: አስተባበለም:: እምቢም አለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ أَجِئۡتَنَا لِتُخۡرِجَنَا مِنۡ أَرۡضِنَا بِسِحۡرِكَ يَٰمُوسَىٰ
57. አለም: «ሙሳ ሆይ! ከምድራችን በድግምትህ ልታወጣን መጣህብን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَلَنَأۡتِيَنَّكَ بِسِحۡرٖ مِّثۡلِهِۦ فَٱجۡعَلۡ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكَ مَوۡعِدٗا لَّا نُخۡلِفُهُۥ نَحۡنُ وَلَآ أَنتَ مَكَانٗا سُوٗى
58. «መሰሉንም ድግምት እናመጣብሃለን:: በእኛና ባንተም መካከል እኛም አንተም የማንጥሰው የሆነ ቀጠሮን በመካከለኛ ስፍራ አድርግልን።» አለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ مَوۡعِدُكُمۡ يَوۡمُ ٱلزِّينَةِ وَأَن يُحۡشَرَ ٱلنَّاسُ ضُحٗى
59.ሙሳም: «ቀጠሯችሁ ያ የማጌጫው የበአሉ ቀን ነው። ሰዎችም ረፋድ ላይ እንዲሰበሰቡ ይሁን።» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَتَوَلَّىٰ فِرۡعَوۡنُ فَجَمَعَ كَيۡدَهُۥ ثُمَّ أَتَىٰ
60. ፈርዖንም ዞረ:: ተንኮሉን ሰበሰበ:: ከዚያ መጣ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ وَيۡلَكُمۡ لَا تَفۡتَرُواْ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا فَيُسۡحِتَكُم بِعَذَابٖۖ وَقَدۡ خَابَ مَنِ ٱفۡتَرَىٰ
61.ሙሳም ለእነርሱ: «ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ:: በቅጣት ያጠፋችኋልና:: የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ።» አላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَتَنَٰزَعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّجۡوَىٰ
62. (ድግምተኞቹ) በመካከላቸውም ነገራቸውን ተጨቃጨቁ፡፡ ውይይትንም ደበቁ፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَٰنِ لَسَٰحِرَٰنِ يُرِيدَانِ أَن يُخۡرِجَاكُم مِّنۡ أَرۡضِكُم بِسِحۡرِهِمَا وَيَذۡهَبَا بِطَرِيقَتِكُمُ ٱلۡمُثۡلَىٰ
63. አሉም: «እነዚህ በእርግጥ ደጋሚዎች ናቸው:: ከምድራችሁ በድግምታቸው ሊያወጧችሁ በላጪቱንም መንገዳችሁን ሊያስወግዱባችሁ ይሻሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَجۡمِعُواْ كَيۡدَكُمۡ ثُمَّ ٱئۡتُواْ صَفّٗاۚ وَقَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡيَوۡمَ مَنِ ٱسۡتَعۡلَىٰ
64. «ተንኮላችሁንም አጠንክሩ:: ከዚያም ተሰልፋችሁ ኑ:: ዛሬ ያሸነፈም ሰው ምኞቱን አገኘ።» ተባባሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلۡقِيَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَلۡقَىٰ
65. «ሙሳ ሆይ! በመጀመሪያ ትጥላለህ ወይስ እኛ እንጣል? (ምረጥ)» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ بَلۡ أَلۡقُواْۖ فَإِذَا حِبَالُهُمۡ وَعِصِيُّهُمۡ يُخَيَّلُ إِلَيۡهِ مِن سِحۡرِهِمۡ أَنَّهَا تَسۡعَىٰ
66. ሙሳም «እናንተ በመጀመሪያ ጣሉ።» አላቸው። ጣሉም:: ወዲያዉም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ የሚሮጡ እባቦች ሆነው (መስለው) ወደ እርሱ ተመሰሉበት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَوۡجَسَ فِي نَفۡسِهِۦ خِيفَةٗ مُّوسَىٰ
67.ሙሳም በውስጡ ፍርሃት አደረበት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡنَا لَا تَخَفۡ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡأَعۡلَىٰ
68. አልነውም: «አትፍራ። የበላዩ አንተ ነህና።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَلۡقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلۡقَفۡ مَا صَنَعُوٓاْۖ إِنَّمَا صَنَعُواْ كَيۡدُ سَٰحِرٖۖ وَلَا يُفۡلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيۡثُ أَتَىٰ
69. «በቀኝ እጅህ ያለችውን ብትር ጣል:: ያንን የሰሩትን ሁሉ ትውጣለችና። ያ የሰሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ብቻ ነውና:: ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናዉም::»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سُجَّدٗا قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ هَٰرُونَ وَمُوسَىٰ
70. ድግምተኞቹም ሱጁድ ወረዱ: «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን።» አሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ ءَامَنتُمۡ لَهُۥ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِي عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحۡرَۖ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمۡ فِي جُذُوعِ ٱلنَّخۡلِ وَلَتَعۡلَمُنَّ أَيُّنَآ أَشَدُّ عَذَابٗا وَأَبۡقَىٰ
71. (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁለትን! እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ መሪያችሁ ነው:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (በማናጋት) ግራንና ቀኝን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ:: የማንኛችን ቅጣት በጣም ብርቱና የሚቆይ መሆኑን በዚያ ጊዜ ታውቃላችሁ።» አላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ لَن نُّؤۡثِرَكَ عَلَىٰ مَا جَآءَنَا مِنَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلَّذِي فَطَرَنَاۖ فَٱقۡضِ مَآ أَنتَ قَاضٍۖ إِنَّمَا تَقۡضِي هَٰذِهِ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَآ
72. አሉትም: «ከመጡልን ተዓምራትና ከዚያ ከፈጠረን አምላክ ፈጽሞ አናስበልጥህም:: እናም የምትፈርደውን ፍረድ:: የምትፈርደው በዚህች በአነስተኛይቱ ህይወት ብቻ ላይ ነውና።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّآ ءَامَنَّا بِرَبِّنَا لِيَغۡفِرَ لَنَا خَطَٰيَٰنَا وَمَآ أَكۡرَهۡتَنَا عَلَيۡهِ مِنَ ٱلسِّحۡرِۗ وَٱللَّهُ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓ
73. «ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም እንድንፈጽመው ያስገደድከንን ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል:: አላህ በጣም በላጭ ነው:: ቅጣቱም ሆነ ምንዳው በጣም የሚዘወትር ነው።» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّهُۥ مَن يَأۡتِ رَبَّهُۥ مُجۡرِمٗا فَإِنَّ لَهُۥ جَهَنَّمَ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ
74. ከሃዲ ሆኖ ወደ ጌታው የሚመጣ (የሚሞት) ሰው ሁሉ ለእርሱ ገሀነም አለችለት:: በውስጧም አይሞትም ህያዉም አይሆንም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَن يَأۡتِهِۦ مُؤۡمِنٗا قَدۡ عَمِلَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلدَّرَجَٰتُ ٱلۡعُلَىٰ
75.እነዚያ በጎ ስራዎችን የሰሩና አማኝ ሆነው ወደ ጌታቸው የመጡ ሰዎች ደግሞ እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
جَنَّٰتُ عَدۡنٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ وَذَٰلِكَ جَزَآءُ مَن تَزَكَّىٰ
76.ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አሏቸው:: ይህም አይነቱ ክፍያ ለተጥራራ ሁሉ ምንዳው ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِي فَٱضۡرِبۡ لَهُمۡ طَرِيقٗا فِي ٱلۡبَحۡرِ يَبَسٗا لَّا تَخَٰفُ دَرَكٗا وَلَا تَخۡشَىٰ
77. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ሂድ:: ለእነርሱም በባህር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው:: ፈርዖን ያገኘኛል ብለህ አትፍራ:: ከመስመጥም አትጨነቅ።» ስንል በእርግጥ ላክንበት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَتۡبَعَهُمۡ فِرۡعَوۡنُ بِجُنُودِهِۦ فَغَشِيَهُم مِّنَ ٱلۡيَمِّ مَا غَشِيَهُمۡ
78. ፈርዖን ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ ተከተላቸው:: ከባህሩም የሚሸፍን ነገር ሸፈናቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَضَلَّ فِرۡعَوۡنُ قَوۡمَهُۥ وَمَا هَدَىٰ
79.ፈርዖንም ህዝቦቹን አሳሳታቸው:: ቅኑንም መንገድ አልመራቸዉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ قَدۡ أَنجَيۡنَٰكُم مِّنۡ عَدُوِّكُمۡ وَوَٰعَدۡنَٰكُمۡ جَانِبَ ٱلطُّورِ ٱلۡأَيۡمَنَ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰ
80. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ:: በጡር ተራራም ቀኝ ጎን ላይ ቀጠሮ አደረግንላችሁ። በእናንተም ላይ መናንና ሰልዋን (ድርጭት) አወረድንላችሁ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ وَلَا تَطۡغَوۡاْ فِيهِ فَيَحِلَّ عَلَيۡكُمۡ غَضَبِيۖ وَمَن يَحۡلِلۡ عَلَيۡهِ غَضَبِي فَقَدۡ هَوَىٰ
81. ከሰጠናችሁ ሲሳይ ከመልካሙ ብሉ:: በእርሱም ወሰንን አትለፉ:: ቁጣዬ በእናንተ ላይ ይወርድባችኋልና:: ቁጣዬ የሚወርድበት ሁሉ በእርግጥ ይጠፋል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَإِنِّي لَغَفَّارٞ لِّمَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا ثُمَّ ٱهۡتَدَىٰ
82.እኔም ለተጸጸተ ላመነም መልካምንም ለሰራ ከዚያ ለተመራ ሁሉ በእርግጥ መሓሪ ነኝ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ وَمَآ أَعۡجَلَكَ عَن قَوۡمِكَ يَٰمُوسَىٰ
83. «ሙሳ ሆይ! ከህዝቦችህ ምን አስቸኮለህ?» ተባለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ هُمۡ أُوْلَآءِ عَلَىٰٓ أَثَرِي وَعَجِلۡتُ إِلَيۡكَ رَبِّ لِتَرۡضَىٰ
84. «እነርሱ እነዚህ በዱካዬ ላይ ያሉ ናቸው:: ጌታዬ ሆይ! ትወድልኝ ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ።» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ فَإِنَّا قَدۡ فَتَنَّا قَوۡمَكَ مِنۢ بَعۡدِكَ وَأَضَلَّهُمُ ٱلسَّامِرِيُّ
85.(አላህም) «እኛም ካንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈተንን:: ሳምራዊዉም አሳሳታቸው።» አለው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَرَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ غَضۡبَٰنَ أَسِفٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ أَلَمۡ يَعِدۡكُمۡ رَبُّكُمۡ وَعۡدًا حَسَنًاۚ أَفَطَالَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡعَهۡدُ أَمۡ أَرَدتُّمۡ أَن يَحِلَّ عَلَيۡكُمۡ غَضَبٞ مِّن رَّبِّكُمۡ فَأَخۡلَفۡتُم مَّوۡعِدِي
86. ሙሳም ወደ ሰዎች የተቆጣና ያዘነ ሆኖ ተመለሰ:: «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁ መልካም ተስፋን አልቀጠራችሁምን? ቀጠሮው በእናንተ ላይ ረዘመባችሁን? ወይስ በእናንተ ላይ ከጌታችሁ ቅጣት ሊወርድባችሁ ፈለጋችሁና ቃል ኪዳኔን አፈረሳችሁ?» አላቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ مَآ أَخۡلَفۡنَا مَوۡعِدَكَ بِمَلۡكِنَا وَلَٰكِنَّا حُمِّلۡنَآ أَوۡزَارٗا مِّن زِينَةِ ٱلۡقَوۡمِ فَقَذَفۡنَٰهَا فَكَذَٰلِكَ أَلۡقَى ٱلسَّامِرِيُّ
87. «ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም:: ግን እኛ ከህዝቦች ጌጥ ሸክሞችን ተጫን:: በእሳት ላይ ጣልናትም:: ሳምራዊዉም እንደዚሁ አብሮን ጣለ።» አሉት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَخۡرَجَ لَهُمۡ عِجۡلٗا جَسَدٗا لَّهُۥ خُوَارٞ فَقَالُواْ هَٰذَآ إِلَٰهُكُمۡ وَإِلَٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ
88. ለእነርሱም የመጓጎር ባህሪ ያለውን ጥጃን (መሰል) አካልን አወጣላቸው። «ተከታዮቹ ሆይ! ይህ የእናንተም ሆነ የሙሳ አምላክ ነው:: ግን ረሳው እንጂ።» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَفَلَا يَرَوۡنَ أَلَّا يَرۡجِعُ إِلَيۡهِمۡ قَوۡلٗا وَلَا يَمۡلِكُ لَهُمۡ ضَرّٗا وَلَا نَفۡعٗا
89.ወደ እነርሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም ጉዳትንና ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ قَالَ لَهُمۡ هَٰرُونُ مِن قَبۡلُ يَٰقَوۡمِ إِنَّمَا فُتِنتُم بِهِۦۖ وَإِنَّ رَبَّكُمُ ٱلرَّحۡمَٰنُ فَٱتَّبِعُونِي وَأَطِيعُوٓاْ أَمۡرِي
90-.ከዚያ በፊት ሀሩንም በእርግጥ አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! ይህ በእርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው:: ጌታችሁም አር-ረህማን ነው:: ተከተሉኝም፤ ትእዛዜንም ስሙ።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ لَن نَّبۡرَحَ عَلَيۡهِ عَٰكِفِينَ حَتَّىٰ يَرۡجِعَ إِلَيۡنَا مُوسَىٰ
91. «ሙሳ ወደ እኛ እስከሚመለስ በእርሱ መገዛት ላይ ከመቆየት ፈጽሞ አንወገድም።» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ يَٰهَٰرُونُ مَا مَنَعَكَ إِذۡ رَأَيۡتَهُمۡ ضَلُّوٓاْ
92- ሙሳም አለ፡- «ሃሩን ሆይ! ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከለህ?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَلَّا تَتَّبِعَنِۖ أَفَعَصَيۡتَ أَمۡرِي
93. «እኔን ከመከተል? ትእዛዜን ጣስክን?» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ يَبۡنَؤُمَّ لَا تَأۡخُذۡ بِلِحۡيَتِي وَلَا بِرَأۡسِيٓۖ إِنِّي خَشِيتُ أَن تَقُولَ فَرَّقۡتَ بَيۡنَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَلَمۡ تَرۡقُبۡ قَوۡلِي
94. «ሃሩን የእናቴ ልጅ ሆይ! ፂሜንም ሆነ ራሴን አትያዝ:: እኔ ‹በኢስራኢል ልጆች መካከል ለያየህ ቃሌንም አልጠበክም› ማለትህን ፈራሁና ነው።» አለው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ فَمَا خَطۡبُكَ يَٰسَٰمِرِيُّ
95. ሙሳም «ሳምራዊው ሆይ! ነገርህ ምንድን ነው?» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ بَصُرۡتُ بِمَا لَمۡ يَبۡصُرُواْ بِهِۦ فَقَبَضۡتُ قَبۡضَةٗ مِّنۡ أَثَرِ ٱلرَّسُولِ فَنَبَذۡتُهَا وَكَذَٰلِكَ سَوَّلَتۡ لِي نَفۡسِي
96. ሳምራዊውም: «እነርሱ ያላዩትን ነገር አየሁ:: ከመልዕክተኛው ፈረስ ኮቴ ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ:: በቅርጹ ላይ ጣልኳትም:: ልክ እንደዚሁ ነፍሴ ሸለመችልኝ።» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ فَٱذۡهَبۡ فَإِنَّ لَكَ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ أَن تَقُولَ لَا مِسَاسَۖ وَإِنَّ لَكَ مَوۡعِدٗا لَّن تُخۡلَفَهُۥۖ وَٱنظُرۡ إِلَىٰٓ إِلَٰهِكَ ٱلَّذِي ظَلۡتَ عَلَيۡهِ عَاكِفٗاۖ لَّنُحَرِّقَنَّهُۥ ثُمَّ لَنَنسِفَنَّهُۥ فِي ٱلۡيَمِّ نَسۡفًا
97. ሙሳም ለሳምራዊው አለው: «ሂድ። በህይወትህ ላየኸው ሰው ሁሉ ‹መነካካት የለም› እያልክ ኑር:: ላንተም ፈጽሞ የማትቀር ቀጠሮ አለህ:: ወደ እዚያዉም በእርሱ ላይ ተገዢው ሆነህ ወደ ቆየህበት አምላክህ ተመልከት:: በእርግጥ እናቃጥለዋለን:: ከዚያም በባህሩ ውስጥ እንበትነዋለን::»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّمَآ إِلَٰهُكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ وَسِعَ كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمٗا
98.(ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ያ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነው አላህ ብቻ ነው:: እውቀቱ ሁሉን ነገር አዳረሰ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ مَا قَدۡ سَبَقَۚ وَقَدۡ ءَاتَيۡنَٰكَ مِن لَّدُنَّا ذِكۡرٗا
99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፤ ከእኛም ዘንድ ቁርኣንን በእርግጥ ሰጠንህ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
مَّنۡ أَعۡرَضَ عَنۡهُ فَإِنَّهُۥ يَحۡمِلُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وِزۡرًا
100.ከእርሱ ያፈገፈገ ሰው እርሱ በትንሳኤ ቀን ከባድን ቅጣት ይሸከማል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
خَٰلِدِينَ فِيهِۖ وَسَآءَ لَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ حِمۡلٗا
101.በእርሱ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው ይሸከማሉ:: በትንሳኤ ቀን ለእነርሱ እጣ ፈንታ የሆነው ሸክም ከፋ!
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِۚ وَنَحۡشُرُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ يَوۡمَئِذٖ زُرۡقٗا
102. በቀንዱ በሚነፋ ቀን ሸክማቸው ከፋ:: ከሓዲያን በዚያ ቀን ዓይኖቻቸው ሰማያዊዎች ሆነው እንሰበስባቸዋለን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَتَخَٰفَتُونَ بَيۡنَهُمۡ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا عَشۡرٗا
103. «አስርን (ቀን) እንጂ አልቆያችሁም።» በመባባል በመካከላቸው ይንሾካሾካሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
نَّحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَقُولُونَ إِذۡ يَقُولُ أَمۡثَلُهُمۡ طَرِيقَةً إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا يَوۡمٗا
104. በሃሳብ ቀጥተኛቸው «አንድን ቀን እንጂ አልቆያችሁም።» በሚል ጊዜ የሚሉትን ነገር እኛ አዋቂዎች ነን።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡجِبَالِ فَقُلۡ يَنسِفُهَا رَبِّي نَسۡفٗا
105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጋራዎች ይጠይቁሃልና (እንዲህ) በላቸው: «ጌታዬ መበተንን ይበትናቸዋል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَيَذَرُهَا قَاعٗا صَفۡصَفٗا
106. «ትክክል ሜዳም ሆና ይተዋታል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَّا تَرَىٰ فِيهَا عِوَجٗا وَلَآ أَمۡتٗا
107. «በእርሷ ዝቅታና ከፍታን ፈጽሞ አታይም።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَوۡمَئِذٖ يَتَّبِعُونَ ٱلدَّاعِيَ لَا عِوَجَ لَهُۥۖ وَخَشَعَتِ ٱلۡأَصۡوَاتُ لِلرَّحۡمَٰنِ فَلَا تَسۡمَعُ إِلَّا هَمۡسٗا
108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ ቀን ለመሰብሰብ ጠሪውን ምንም እንከን የሌለውን ተጣሪ ይከተላሉ:: ድምፆችም ሁሉ ለአር-ረህማን ጸጥ ይላሉ:: ስለዚህ (የኮቴ) ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَوۡمَئِذٖ لَّا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَرَضِيَ لَهُۥ قَوۡلٗا
109.በዚያ ቀን ለእርሱ አር-ረህማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ብቻ ቢሆን እንጂ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِۦ عِلۡمٗا
110. በስተፊታቸው ያለውንም ሆነ በስተኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል:: በእርሱ ላይ ግን ማንም በእውቀቱ አያካብብም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ وَعَنَتِ ٱلۡوُجُوهُ لِلۡحَيِّ ٱلۡقَيُّومِۖ وَقَدۡ خَابَ مَنۡ حَمَلَ ظُلۡمٗا
111. ፊቶችም ሁሉ ህያውና የሁሉ አስተናባሪ ለሆነው አላህ ተዋረዱ:: በደልንም የተሸከመ በእርግጥ ከሰረ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَن يَعۡمَلۡ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَا يَخَافُ ظُلۡمٗا وَلَا هَضۡمٗا
112. አማኝ ሆኖ መልካም ስራዎችን የሰራ በደልንም ሆነ መጉደልን አይፈራም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلۡنَٰهُ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا وَصَرَّفۡنَا فِيهِ مِنَ ٱلۡوَعِيدِ لَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ أَوۡ يُحۡدِثُ لَهُمۡ ذِكۡرٗا
113.ልክ እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ሆኖ አወረድነው:: አላህን ይፈሩ ዘንድ ወይም ለእነርሱ ግሣጼን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡحَقُّۗ وَلَا تَعۡجَلۡ بِٱلۡقُرۡءَانِ مِن قَبۡلِ أَن يُقۡضَىٰٓ إِلَيۡكَ وَحۡيُهُۥۖ وَقُل رَّبِّ زِدۡنِي عِلۡمٗا
114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኛው ንጉስ አላህ ከሓዲያን ከሚሉት ነገር ሁሉ ላቀ:: ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት ቁርኣንን በማንበብ አትቸኩል:: «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ።» በልም።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ عَهِدۡنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبۡلُ فَنَسِيَ وَلَمۡ نَجِدۡ لَهُۥ عَزۡمٗا
115. ወደ አደምም ከዚህ በፊት ቃል ኪዳንን በእርግጥ አወረድንና ረሳ:: ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ أَبَىٰ
116.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ።» ባልን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እነርሱም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሰገዱ:: እሱማ እምቢ አለ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَقُلۡنَا يَٰٓـَٔادَمُ إِنَّ هَٰذَا عَدُوّٞ لَّكَ وَلِزَوۡجِكَ فَلَا يُخۡرِجَنَّكُمَا مِنَ ٱلۡجَنَّةِ فَتَشۡقَىٰٓ
117.ከዚያም አልን: «አደም ሆይ! ይህ ላንተም ለሚስትህም በእርግጥ ጠላት ነው:: ስለዚህ ከገነት አያውጣችሁ፤ ትለፋለህና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّ لَكَ أَلَّا تَجُوعَ فِيهَا وَلَا تَعۡرَىٰ
118.(አደም ሆይ!) «ላንተ በእርሷ ውስጥ አለመራብና አለመታረዝ አለህ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَنَّكَ لَا تَظۡمَؤُاْ فِيهَا وَلَا تَضۡحَىٰ
119. «አንተም ከእርሷ ውስጥ አትጠማም:: በጸሐይም አትተኮስም።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَوَسۡوَسَ إِلَيۡهِ ٱلشَّيۡطَٰنُ قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ هَلۡ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ ٱلۡخُلۡدِ وَمُلۡكٖ لَّا يَبۡلَىٰ
120. ሰይጣን ወደ እርሱ (አደም) « አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግስናም ላይ ላመላክትህን?» በማለት ጎተጎተ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَكَلَا مِنۡهَا فَبَدَتۡ لَهُمَا سَوۡءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخۡصِفَانِ عَلَيۡهِمَا مِن وَرَقِ ٱلۡجَنَّةِۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ
121.ከእርሷም በሉ:: ለእነርሱም ሀፍረተ ገላቸው ተገለጸች:: ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር:: አደምም የጌታውን ትእዛዝ ረስቶ ጣሰ:: ተሳሳተም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ثُمَّ ٱجۡتَبَٰهُ رَبُّهُۥ فَتَابَ عَلَيۡهِ وَهَدَىٰ
122. ከዚያም ጌታው መረጠው:: ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው:: መራዉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ ٱهۡبِطَا مِنۡهَا جَمِيعَۢاۖ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوّٞۖ فَإِمَّا يَأۡتِيَنَّكُم مِّنِّي هُدٗى فَمَنِ ٱتَّبَعَ هُدَايَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشۡقَىٰ
123.አላህም አላቸው፡- «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን (አደምና ሐዋ) ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ:: ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያየን የተከተለ ሁሉ አይሳሳትም:: አይቸገርምም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَنۡ أَعۡرَضَ عَن ذِكۡرِي فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةٗ ضَنكٗا وَنَحۡشُرُهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَعۡمَىٰ
124. «ከግሳጼዬ የዞረ ግን በዚህች ዓለም ጠባብ ኑሮ አለው:: በትንሳኤ ቀንም ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን::»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ رَبِّ لِمَ حَشَرۡتَنِيٓ أَعۡمَىٰ وَقَدۡ كُنتُ بَصِيرٗا
125. «ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ:: በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስሆን» አለ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتۡكَ ءَايَٰتُنَا فَنَسِيتَهَاۖ وَكَذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمَ تُنسَىٰ
126. «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: ተዓምራቶቻችን መጡልህና ተውካቸውም:: ልክ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ።» ይለዋል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي مَنۡ أَسۡرَفَ وَلَمۡ يُؤۡمِنۢ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦۚ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَشَدُّ وَأَبۡقَىٰٓ
127.እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አናቅጽ ያላመነን እንቀጣዋለን:: የመጨረሻይቱ ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱና ለሁልጊዜም ዘውታሪ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَفَلَمۡ يَهۡدِ لَهُمۡ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ يَمۡشُونَ فِي مَسَٰكِنِهِمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّأُوْلِي ٱلنُّهَىٰ
128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ቁረይሾች) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሆነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልዕክቶች አሉበት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَكَانَ لِزَامٗا وَأَجَلٞ مُّسَمّٗى
129.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ አሁኑኑ የሚይዛቸው ይሆን ነበር::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ قَبۡلَ طُلُوعِ ٱلشَّمۡسِ وَقَبۡلَ غُرُوبِهَاۖ وَمِنۡ ءَانَآيِٕ ٱلَّيۡلِ فَسَبِّحۡ وَأَطۡرَافَ ٱلنَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرۡضَىٰ
130. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) በሚሉትም ሁሉ ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመግባቷም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው:: ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው:: በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَا تَمُدَّنَّ عَيۡنَيۡكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعۡنَا بِهِۦٓ أَزۡوَٰجٗا مِّنۡهُمۡ زَهۡرَةَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا لِنَفۡتِنَهُمۡ فِيهِۚ وَرِزۡقُ رَبِّكَ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰ
131.ዐይኖችህን ከሰዎች የተወሰኑ ክፍሎችን ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት ወደ ቅርቢቱ ህይወት ጌጦች አትዘርጋ:: የጌታህ ሲሳይ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأۡمُرۡ أَهۡلَكَ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱصۡطَبِرۡ عَلَيۡهَاۖ لَا نَسۡـَٔلُكَ رِزۡقٗاۖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُكَۗ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلتَّقۡوَىٰ
132.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤተሰብህንም በሶላት ላይ እዘዝ:: አንተም በእርሷ ላይ ዘውትር:: ሲሳይን አንጠይቅህም:: እኛ እንሰጥሃለን:: መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَقَالُواْ لَوۡلَا يَأۡتِينَا بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّهِۦٓۚ أَوَلَمۡ تَأۡتِهِم بَيِّنَةُ مَا فِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ
133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተከራካሪዎችህ «ከጌታው በሆነ ተዓምር አይመጣምን?» አሉ:: በመጀመሪያዎቹ ጹሁፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸዉምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَوۡ أَنَّآ أَهۡلَكۡنَٰهُم بِعَذَابٖ مِّن قَبۡلِهِۦ لَقَالُواْ رَبَّنَا لَوۡلَآ أَرۡسَلۡتَ إِلَيۡنَا رَسُولٗا فَنَتَّبِعَ ءَايَٰتِكَ مِن قَبۡلِ أَن نَّذِلَّ وَنَخۡزَىٰ
134. እኛም (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አናቅጽህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልዕክተኛን አትልክልንም ነበርን?» ባሉ ነበር::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ كُلّٞ مُّتَرَبِّصٞ فَتَرَبَّصُواْۖ فَسَتَعۡلَمُونَ مَنۡ أَصۡحَٰبُ ٱلصِّرَٰطِ ٱلسَّوِيِّ وَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ
135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም ተጠባባቂ ነው:: ተጠባበቁም የቀጥታዉም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደ ሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደፊት ታውቃላችሁ።» በላቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Taha
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Học viện Châu Phi - Mục lục các bản dịch

Người dịch Muhammad Zain Zuher Al-Din, do Học viện Châu Phi phát hành.

Đóng lại