Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

含义的翻译 章: 呼德   段:
فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا جَعَلۡنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهَا حِجَارَةٗ مِّن سِجِّيلٖ مَّنضُودٖ
82. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ከተማይቱን ላይዋን ከታችዋ አድርገን ገለበጥናት:: ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በእርሷ ላይ አዘነብንባት::
阿拉伯语经注:
مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَۖ وَمَا هِيَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ بِبَعِيدٖ
83. ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም (መንደሯ) ከበደለኞቹ ህዝቦች ሩቅ አይደለችም::
阿拉伯语经注:
۞ وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ وَلَا تَنقُصُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَۖ إِنِّيٓ أَرَىٰكُم بِخَيۡرٖ وَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ مُّحِيطٖ
84. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን:: አላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: ስፍርንና ሚዛንን አታጉሉ:: እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ:: እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ أَوۡفُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
85. «ህዝቦቼ ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: ሰዎችን መብቶቻቸውን አታጓድሉባቸው:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።
阿拉伯语经注:
بَقِيَّتُ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ
86. «አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ትክክለኛ አማኞች እንደ ሆናችሁ አላህ በሰጣችሁ ውደዱ። እኔም መካሪ እንጂ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።»
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ أَصَلَوٰتُكَ تَأۡمُرُكَ أَن نَّتۡرُكَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَآ أَوۡ أَن نَّفۡعَلَ فِيٓ أَمۡوَٰلِنَا مَا نَشَٰٓؤُاْۖ إِنَّكَ لَأَنتَ ٱلۡحَلِيمُ ٱلرَّشِيدُ
87. «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣኦታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን እንድንተው ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑው አንተ ነህና።» አሉት።
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَرَزَقَنِي مِنۡهُ رِزۡقًا حَسَنٗاۚ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أُخَالِفَكُمۡ إِلَىٰ مَآ أَنۡهَىٰكُمۡ عَنۡهُۚ إِنۡ أُرِيدُ إِلَّا ٱلۡإِصۡلَٰحَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُۚ وَمَا تَوۡفِيقِيٓ إِلَّا بِٱللَّهِۚ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُ وَإِلَيۡهِ أُنِيبُ
88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ።
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 呼德
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭