Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

含义的翻译 章: 呼德   段:
فَلَا تَكُ فِي مِرۡيَةٖ مِّمَّا يَعۡبُدُ هَٰٓؤُلَآءِۚ مَا يَعۡبُدُونَ إِلَّا كَمَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُهُم مِّن قَبۡلُۚ وَإِنَّا لَمُوَفُّوهُمۡ نَصِيبَهُمۡ غَيۡرَ مَنقُوصٖ
109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከሓዲያን ከሚገዙት ጣኦት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚገዙት እንጂ አይገዙም:: እኛም እነዚህን ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ
110. ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው አሁን ይፈረድ ነበር:: እነርሱም ከእርሱ ከቁርኣን አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ كُلّٗا لَّمَّا لَيُوَفِّيَنَّهُمۡ رَبُّكَ أَعۡمَٰلَهُمۡۚ إِنَّهُۥ بِمَا يَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
111. ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን ምንዳቸውን በእርግጥ ይሞላላቸዋል:: እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَقِمۡ كَمَآ أُمِرۡتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطۡغَوۡاْۚ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል። ካንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ። ወሰንንም አትለፉ። እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
阿拉伯语经注:
وَلَا تَرۡكَنُوٓاْ إِلَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ فَتَمَسَّكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنۡ أَوۡلِيَآءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ
113. ወደ እነዚያም ወደ በደሉት ህዝቦች አትዘንበሉ:: እሳት ትነካችኋለችና:: ከአላህ ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም ከዚያ አትረዱም::
阿拉伯语经注:
وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ طَرَفَيِ ٱلنَّهَارِ وَزُلَفٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِۚ إِنَّ ٱلۡحَسَنَٰتِ يُذۡهِبۡنَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ ذَٰلِكَ ذِكۡرَىٰ لِلذَّٰكِرِينَ
114. ሶላትንም በቀን ጫፍና ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም:: መልካም ሥራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና:: ይህ ለተገሳጮች ሁሉ ግሳጼ ነው::
阿拉伯语经注:
وَٱصۡبِرۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
115. ታገስ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::
阿拉伯语经注:
فَلَوۡلَا كَانَ مِنَ ٱلۡقُرُونِ مِن قَبۡلِكُمۡ أُوْلُواْ بَقِيَّةٖ يَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡفَسَادِ فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّنۡ أَنجَيۡنَا مِنۡهُمۡۗ وَٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَآ أُتۡرِفُواْ فِيهِ وَكَانُواْ مُجۡرِمِينَ
116. ከናንተ በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት (ሰዎች) ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ሥራዎች ቅሪት ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነርሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ ከለከሉና ዳኑ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች አልከለከሉም። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ አመጠኞችም ነበሩ::
阿拉伯语经注:
وَمَا كَانَ رَبُّكَ لِيُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ بِظُلۡمٖ وَأَهۡلُهَا مُصۡلِحُونَ
117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 呼德
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭