《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 宰尼 * - 译解目录


含义的翻译 章: 隋法提   段:

ሱረቱ አስ ሷፋት

وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفّٗا
1. መሰለፍን በሚሰለፉት፤
阿拉伯语经注:
فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرٗا
2. (ደመና) መንዳትን በሚነዱት፤
阿拉伯语经注:
فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا
3. ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ::
阿拉伯语经注:
إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٞ
4. አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ብቻ ነው::
阿拉伯语经注:
رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ
5. እርሱ ያ በሰማያትና በምድር በመካካለቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው:: የምስራቆችም ጌታ ነው::
阿拉伯语经注:
إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ
6. እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት (አስዋብናት)::
阿拉伯语经注:
وَحِفۡظٗا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ مَّارِدٖ
7. አመጸኛ ከሆነ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት::
阿拉伯语经注:
لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٖ
8. ወደ ላይኛው ሰራዊት አያደምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፤ (ይቀጠቀጣሉ)።
阿拉伯语经注:
دُحُورٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ وَاصِبٌ
9. የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፤ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::
阿拉伯语经注:
إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ ثَاقِبٞ
10. ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውኑም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር (እርሱ ይሰማዋል)::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٖ لَّازِبِۭ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ ከእነርሱ በፊት የፈጠረነው ፍጡር? እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው::
阿拉伯语经注:
بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ
12. ይልቁንም ማስተባበላቸው አስደነቀህ፤ በመደነቅህም ይሳለቃሉ::
阿拉伯语经注:
وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ
13. በተገሰጹም ጊዜ አይገሰጹም::
阿拉伯语经注:
وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةٗ يَسۡتَسۡخِرُونَ
14. ተዓምርንም ባዩ ጊዜ ለመሳለቅ ይጣጣራሉ።
阿拉伯语经注:
وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٌ
15. አሉም: «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
阿拉伯语经注:
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
16. «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆን ጊዜ የምንቀስቀስ ነን?
阿拉伯语经注:
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ
17. «የቀድሞዎቹ አባቶቻችንም እንደዚሁ ይቀሰቀሳሉን?» (ይላሉ።)
阿拉伯语经注:
قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ
18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አዎን! እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ
19. እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት:: እነርሱም ወዲያውኑ ምን እንደሚፈጸምባቸው ያያሉ::
阿拉伯语经注:
وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
20. «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው።» (ይላሉም)
阿拉伯语经注:
هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
21. «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉት የነበራችት መለያው ቀን ነው።» ይባላሉ።
阿拉伯语经注:
۞ ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ
22. (ለመላዕክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ከአላህ ሌላ ይገዟቸው የነበሩትንም ጣዖታት በአንድ ሰብስቡ።
阿拉伯语经注:
مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ
23. ከአላህ ውጭ (ይገዟቸው የነበሩትን ሰብስቡ)። ከዚያም ወደ ገሀነም መንገድ ምሯቸው።
阿拉伯语经注:
وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ
24. «እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና አቁሟቸዉም።» (ይባላል።)
阿拉伯语经注:
مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ
25. ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ።
阿拉伯语经注:
بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ
26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
27. እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ።
阿拉伯语经注:
قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ
28. (ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
29. (አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም።
阿拉伯语经注:
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ
30. «ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ።
阿拉伯语经注:
فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ
31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል የተረጋገጠብንና ሁላችንም ቅጣቱን ቀማሽ ነን።
阿拉伯语经注:
فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ
32. «እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ።
阿拉伯语经注:
فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ
33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ
34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን።
阿拉伯语经注:
إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ
35. እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።
阿拉伯语经注:
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ
36. «እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።
阿拉伯语经注:
بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
37. አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ።
阿拉伯语经注:
إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ
38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ::
阿拉伯语经注:
وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
39. ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም::
阿拉伯语经注:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም::
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ
41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው::
阿拉伯语经注:
فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ
42. ፍራፋሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው::
阿拉伯语经注:
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
43. በድሎት ገነቶች ውስጥ::
阿拉伯语经注:
عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
44. ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ::
阿拉伯语经注:
يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ
45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል::
阿拉伯语经注:
بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ
46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤
阿拉伯语经注:
لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ
47. በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም:: እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም::
阿拉伯语经注:
وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ
48. እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ::
阿拉伯语经注:
كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ
49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ::
阿拉伯语经注:
فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
50. የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ::
阿拉伯语经注:
قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ
51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ።
阿拉伯语经注:
يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُصَدِّقِينَ
52. (እንዲህ) የሚል: ‹በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?
阿拉伯语经注:
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ
53. ‹በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆነ ጊዜ እኛ በእርግጥ እኛ እንመረመራለን?› የሚልም።
阿拉伯语经注:
قَالَ هَلۡ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ
54. እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል::
阿拉伯语经注:
فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِي سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ
55. ይመለከታልም በገሀነም መካከልም ጓደኛውን ያየዋል::
阿拉伯语经注:
قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرۡدِينِ
56. ይላል «በአላህ እምላለሁ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር።
阿拉伯语经注:
وَلَوۡلَا نِعۡمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ
57. «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።» (ይላል)
阿拉伯语经注:
أَفَمَا نَحۡنُ بِمَيِّتِينَ
58. (የገነት ሰዎች ይላሉ)፡ «እኛ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን?»
阿拉伯语经注:
إِلَّا مَوۡتَتَنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ
59. «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር እኛም የምንቀጣ አይደለንም» ይላሉ።
阿拉伯语经注:
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
60.ይህ ለገነት ሰዎች የተወሳው እርሱ በእርግጥ ታላቅ እድል ነው::
阿拉伯语经注:
لِمِثۡلِ هَٰذَا فَلۡيَعۡمَلِ ٱلۡعَٰمِلُونَ
61. ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ሁሉ ይስሩ::
阿拉伯语经注:
أَذَٰلِكَ خَيۡرٞ نُّزُلًا أَمۡ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ
62. በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
阿拉伯语经注:
إِنَّا جَعَلۡنَٰهَا فِتۡنَةٗ لِّلظَّٰلِمِينَ
63. እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።
阿拉伯语经注:
إِنَّهَا شَجَرَةٞ تَخۡرُجُ فِيٓ أَصۡلِ ٱلۡجَحِيمِ
64. እርሷ ከገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፤
阿拉伯语经注:
طَلۡعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ
65. እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል::
阿拉伯语经注:
فَإِنَّهُمۡ لَأٓكِلُونَ مِنۡهَا فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ
66. እነርሱ ከእርሷ በይዎች ናቸው:: ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ إِنَّ لَهُمۡ عَلَيۡهَا لَشَوۡبٗا مِّنۡ حَمِيمٖ
67. ከዚያ ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅልን መጠጥ አላቸው።
阿拉伯语经注:
ثُمَّ إِنَّ مَرۡجِعَهُمۡ لَإِلَى ٱلۡجَحِيمِ
68. ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُمۡ أَلۡفَوۡاْ ءَابَآءَهُمۡ ضَآلِّينَ
69. እነርሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋል።
阿拉伯语经注:
فَهُمۡ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ يُهۡرَعُونَ
70. እነርሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና።
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ ضَلَّ قَبۡلَهُمۡ أَكۡثَرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
71. ከእነርሱም በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ህዝቦች አብዛሀኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ
72. በውስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል::
阿拉伯语经注:
فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ
73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት!
阿拉伯语经注:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
74. ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ نَادَىٰنَا نُوحٞ فَلَنِعۡمَ ٱلۡمُجِيبُونَ
75. ኑህም በእርግጥ ጠራን:: ምንኛ ያማርን ምላሽ ሰጪ ነን?
阿拉伯语经注:
وَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ
76. እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን::
阿拉伯语经注:
وَجَعَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُۥ هُمُ ٱلۡبَاقِينَ
77. ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን::
阿拉伯语经注:
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
78. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝና ተውን::
阿拉伯语经注:
سَلَٰمٌ عَلَىٰ نُوحٖ فِي ٱلۡعَٰلَمِينَ
79. «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑህ ላይ ይሁን።»
阿拉伯语经注:
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
80. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
81. እርሱ ከአማኞች ባሮቻችን ነውና::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
82. ከዚያም ሌሎችን አሰመጥን::
阿拉伯语经注:
۞ وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبۡرَٰهِيمَ
83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ኢብራሂምም በእርግጥ ከወገኖቹ አንዱ ነው።
阿拉伯语经注:
إِذۡ جَآءَ رَبَّهُۥ بِقَلۡبٖ سَلِيمٍ
84. ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)::
阿拉伯语经注:
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَاذَا تَعۡبُدُونَ
85. ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ: «ምንን ትገዛላችሁ?
阿拉伯语经注:
أَئِفۡكًا ءَالِهَةٗ دُونَ ٱللَّهِ تُرِيدُونَ
86. «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
阿拉伯语经注:
فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
87. «በዓለማቱ ጌታስ ሀሳባችሁ ምንድ ነው?።»
阿拉伯语经注:
فَنَظَرَ نَظۡرَةٗ فِي ٱلنُّجُومِ
88. በከዋክብት መመልከትን ተመለከተ::
阿拉伯语经注:
فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٞ
89. እኔ «በሽተኛ ነኝ» አለ።
阿拉伯语经注:
فَتَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ مُدۡبِرِينَ
90. እነርሱም ከእርሱ የሸሹ ሆነው ሄዱ።
阿拉伯语经注:
فَرَاغَ إِلَىٰٓ ءَالِهَتِهِمۡ فَقَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ
91. ከዚያ እሱ ወደ አማልዕክቶቻቸው ተዘነበለ፤ (እንዲህ) አለም፡- «አትበሉም እንዴ?
阿拉伯语经注:
مَا لَكُمۡ لَا تَنطِقُونَ
92. «ምንም የማትናገሩበትስ ምን ምክኒያት አላችሁ?»
阿拉伯语经注:
فَرَاغَ عَلَيۡهِمۡ ضَرۡبَۢا بِٱلۡيَمِينِ
93. በቀኝ (እጁ) የሚመታቸዉም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ::
阿拉伯语经注:
فَأَقۡبَلُوٓاْ إِلَيۡهِ يَزِفُّونَ
94. ወደ እርሱም ሰዎቹ እየሮጡ መጡ።
阿拉伯语经注:
قَالَ أَتَعۡبُدُونَ مَا تَنۡحِتُونَ
95. አለ: «የምትጠርቡትን ትገዛላችሁን?
阿拉伯语经注:
وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ وَمَا تَعۡمَلُونَ
96. «አላህ እናንተንም ሆነ የምትሰሩትን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን» አላቸው።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ ٱبۡنُواْ لَهُۥ بُنۡيَٰنٗا فَأَلۡقُوهُ فِي ٱلۡجَحِيمِ
97. «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም።» አሉ።
阿拉伯语经注:
فَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَسۡفَلِينَ
98. ለእርሱ ተንኮልን አስቡ ወራዶችም አደረግናቸው።
阿拉伯语经注:
وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهۡدِينِ
99. አለም፡- «እኔ ወደ ጌታየ ሂያጅ ነኝ፤ በእርግጥ ይመራኛልና።
阿拉伯语经注:
رَبِّ هَبۡ لِي مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
100. «ጌታየ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ።»
阿拉伯语经注:
فَبَشَّرۡنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٖ
101. ታጋሽም በሆነ ልጅም አበሰርነው።
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعۡيَ قَالَ يَٰبُنَيَّ إِنِّيٓ أَرَىٰ فِي ٱلۡمَنَامِ أَنِّيٓ أَذۡبَحُكَ فَٱنظُرۡ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفۡعَلۡ مَا تُؤۡمَرُۖ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
102. ከእርሱ ጋርም (ለስራ) በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በህልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ትላለህ?» አለው። «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለ።
阿拉伯语经注:
فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ
103. ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)::
阿拉伯语经注:
وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ
104. ጠራነዉም: «ኢብራሂም ሆይ!
阿拉伯语经注:
قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
105. «ራዕዩን በርግጥ እውን አደረግክ።» እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።
阿拉伯语经注:
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ
106. ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው::
阿拉伯语经注:
وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٖ
107. በታላቅ እርድም መስዕዋት ቤዛ አደረግንለት።
阿拉伯语经注:
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
108. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት::
阿拉伯语经注:
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ
109. ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን::
阿拉伯语经注:
كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
110. ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
111. እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው::
阿拉伯语经注:
وَبَشَّرۡنَٰهُ بِإِسۡحَٰقَ نَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
112. በኢስሐቅም አበሰርነው። ከመልካሞች የሆነ ነብይ ሲሆን::
阿拉伯语经注:
وَبَٰرَكۡنَا عَلَيۡهِ وَعَلَىٰٓ إِسۡحَٰقَۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحۡسِنٞ وَظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ مُبِينٞ
113. በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን። ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሰሪ አለ:: ነፍሱን በግልጽ በዳይም አለ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
114. በሙሳና በሀሩን ላይ በእርግጥ ለገስን::
阿拉伯语经注:
وَنَجَّيۡنَٰهُمَا وَقَوۡمَهُمَا مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ
115. እነርሱንም ሆነ ህዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን::
阿拉伯语经注:
وَنَصَرۡنَٰهُمۡ فَكَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
116. ረዳናቸውናም እነርሱ አሸናፊዎቹ ሆኑ::
阿拉伯语经注:
وَءَاتَيۡنَٰهُمَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلۡمُسۡتَبِينَ
117. በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው::
阿拉伯语经注:
وَهَدَيۡنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
118. ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው::
阿拉伯语经注:
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِمَا فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
119. በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝናን ተውንላቸው::
阿拉伯语经注:
سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
120. ሰላም በሙሳና በሀሩን ላይ ይሁን::
阿拉伯语经注:
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
121. እኛ ልክ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُمَا مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
122. ሁለቱም በትክክል በአላህ ካመኑት ባሮቻችን ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ إِلۡيَاسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
123. ኢልያስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
阿拉伯语经注:
إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ
124. ለህዝቦቹም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አላህን አትፈሩምን?
阿拉伯语经注:
أَتَدۡعُونَ بَعۡلٗا وَتَذَرُونَ أَحۡسَنَ ٱلۡخَٰلِقِينَ
125. «ስዕልን ትገዛላችሁ? ከስዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነዉም አምላክ ትተዋላችሁን?
阿拉伯语经注:
ٱللَّهَ رَبَّكُمۡ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
126. «አላህ ጌታችሁና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁንም ጌታ ትተዋላችሁን?»
阿拉伯语经注:
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ
127. አስተባበሉትም ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው::
阿拉伯语经注:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
128. ንጹህ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::
阿拉伯语经注:
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
129. በእነርሱ ላይም በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት::
阿拉伯语经注:
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلۡ يَاسِينَ
130. ሰላም በኢልያስ ላይ ይሁን፤
阿拉伯语经注:
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
131. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
132. እርሱ በእርግጥ ከምዕመናን ባሮቻችን ነው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ لُوطٗا لَّمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
133. ሉጥም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው::
阿拉伯语经注:
إِذۡ نَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
134. እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳናቸው ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::
阿拉伯语经注:
إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ
135. በቅጣቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር::
阿拉伯语经注:
ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
136. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّكُمۡ لَتَمُرُّونَ عَلَيۡهِم مُّصۡبِحِينَ
137. (መኮች ሆይ)፤ እናንተም በእነርሱ መኖሪያዎች ላይ ያነጋችሁ ስትሆኑ ታልፋላችሁ።
阿拉伯语经注:
وَبِٱلَّيۡلِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
138. በሌሊትም ታልፋላችሁ:: ልብ አታደርጉምን?
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
139. ዩኑስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
阿拉伯语经注:
إِذۡ أَبَقَ إِلَى ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
140. ወደ ተሞላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ አስታውስ::
阿拉伯语经注:
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُدۡحَضِينَ
141. እጣም ተጣጣለ፤ ከተሸነፉትም ሆነ::
阿拉伯语经注:
فَٱلۡتَقَمَهُ ٱلۡحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٞ
142. እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳ ነባሪው ዋጠው::
阿拉伯语经注:
فَلَوۡلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُسَبِّحِينَ
143. እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነ ኖሮ
阿拉伯语经注:
لَلَبِثَ فِي بَطۡنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
144. እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር::
阿拉伯语经注:
۞ فَنَبَذۡنَٰهُ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٞ
145. እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው ባህር ዳርቻ ላይ ጣልነዉም::
阿拉伯语经注:
وَأَنۢبَتۡنَا عَلَيۡهِ شَجَرَةٗ مِّن يَقۡطِينٖ
146. በእርሱም ላይ በአጠገቡ ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን::
阿拉伯语经注:
وَأَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ مِاْئَةِ أَلۡفٍ أَوۡ يَزِيدُونَ
147. ወደ መቶ ሺህ ሰዎችም ላክነው፤ ከቶውንም ይጨምራሉ::
阿拉伯语经注:
فَـَٔامَنُواْ فَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٖ
148. አመኑም። እስከ ጊዜው ድረስም አጣቀምናቸው::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَلِرَبِّكَ ٱلۡبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلۡبَنُونَ
149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመካን ሰዎች ጠይቃቸዉም: «ለጌታህ ሴት ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራሉን?
阿拉伯语经注:
أَمۡ خَلَقۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثٗا وَهُمۡ شَٰهِدُونَ
150. «ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላዕክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?»
阿拉伯语经注:
أَلَآ إِنَّهُم مِّنۡ إِفۡكِهِمۡ لَيَقُولُونَ
151. አስተውሉ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው የተነሳ ይላሉ:
阿拉伯语经注:
وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
152.፡- «አላህ መላዕክትን ወለደ።» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።
阿拉伯语经注:
أَصۡطَفَى ٱلۡبَنَاتِ عَلَى ٱلۡبَنِينَ
153. በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጠን?
阿拉伯语经注:
مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ
154. ለእናንተ ምን አስረጂ አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
阿拉伯语经注:
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
155. አትገነዘቡምን?
阿拉伯语经注:
أَمۡ لَكُمۡ سُلۡطَٰنٞ مُّبِينٞ
156. ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጂ አላችሁን?
阿拉伯语经注:
فَأۡتُواْ بِكِتَٰبِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
157. «እውነተኞች እንደሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» በላቸው።
阿拉伯语经注:
وَجَعَلُواْ بَيۡنَهُۥ وَبَيۡنَ ٱلۡجِنَّةِ نَسَبٗاۚ وَلَقَدۡ عَلِمَتِ ٱلۡجِنَّةُ إِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ
158. በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ:: አጋንንትም ሆኑ ይህን ባዩች በእሳት የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ አውቀዋል::
阿拉伯语经注:
سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
159. አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ::
阿拉伯语经注:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
160. ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች በአላህ ላይ አይዋሹም::
阿拉伯语经注:
فَإِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ
161. (ካሐዲያን ሆይ!) እናንተም የምትገዟቸዉም ሁሉ፤
阿拉伯语经注:
مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ بِفَٰتِنِينَ
162. በእርሱ በአላህ ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም
阿拉伯语经注:
إِلَّا مَنۡ هُوَ صَالِ ٱلۡجَحِيمِ
163. ያንን እርሱ ገሀነም ገቢ የሆነውን ቢሆን እንጂ (አጥማሚዎች አይደላችሁም)።
阿拉伯语经注:
وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٞ مَّعۡلُومٞ
164. (መላእክቶችም አሉ)? «ከእኛ አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ።
阿拉伯语经注:
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلصَّآفُّونَ
165. «እኛም ጌታን ለመገዛት ተሰላፊዎቹ እኛ ነን።
阿拉伯语经注:
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡمُسَبِّحُونَ
166. «እኛም አላህን አጥሪዎቹ እኛው ነን።»
阿拉伯语经注:
وَإِن كَانُواْ لَيَقُولُونَ
167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ (ከሓዲያን) በእርግጥ ይሉ ነበር:
阿拉伯语经注:
لَوۡ أَنَّ عِندَنَا ذِكۡرٗا مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
168. «ከቀድሞዎቹ መጽሐፍ ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረ ኖሮ
阿拉伯语经注:
لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
169. «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር።»
阿拉伯语经注:
فَكَفَرُواْ بِهِۦۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
170. ግን ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ላይ ካዱ። ወደ ፊትም በእርግጥ ያውቃሉ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِينَ
171. የእርዳታ ቃላችንም መልዕክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች::
阿拉伯语经注:
إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ
172. እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
173. ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው::
阿拉伯语经注:
فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
174. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከመካ ከሓዲያን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር ተዋቸው::
阿拉伯语经注:
وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
175. ተመልከታቸዉም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ያያሉ::
阿拉伯语经注:
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
176. በቅጣታችንም ያቻኩሉናልን?
阿拉伯语经注:
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِينَ
177. በቀያቸዉም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
阿拉伯语经注:
وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
178. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ተዋቸው::
阿拉伯语经注:
وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
179. ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ::
阿拉伯语经注:
سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
180. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ::
阿拉伯语经注:
وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ
181. በመልዕክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን::
阿拉伯语经注:
وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
182. ምስጋና ሁሉም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 隋法提
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 宰尼 - 译解目录

阿姆哈拉语翻译

关闭