Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 隋法提   段:

አስ ሷፋት

وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفّٗا
1. መሰለፍን በሚሰለፉት፤
阿拉伯语经注:
فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرٗا
2. (ደመና) መንዳትን በሚነዱት፤
阿拉伯语经注:
فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا
3. ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ::
阿拉伯语经注:
إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٞ
4. አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ብቻ ነው::
阿拉伯语经注:
رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ
5. እርሱ ያ በሰማያትና በምድር በመካካለቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው:: የምስራቆችም ጌታ ነው::
阿拉伯语经注:
إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ
6. እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት (አስዋብናት)::
阿拉伯语经注:
وَحِفۡظٗا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ مَّارِدٖ
7. አመጸኛ ከሆነ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት::
阿拉伯语经注:
لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٖ
8. ወደ ላይኛው ሰራዊት አያደምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፤ (ይቀጠቀጣሉ)።
阿拉伯语经注:
دُحُورٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ وَاصِبٌ
9. የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፤ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::
阿拉伯语经注:
إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ ثَاقِبٞ
10. ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውኑም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር (እርሱ ይሰማዋል)::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٖ لَّازِبِۭ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ ከእነርሱ በፊት የፈጠረነው ፍጡር? እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው::
阿拉伯语经注:
بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ
12. ይልቁንም ማስተባበላቸው አስደነቀህ፤ በመደነቅህም ይሳለቃሉ::
阿拉伯语经注:
وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ
13. በተገሰጹም ጊዜ አይገሰጹም::
阿拉伯语经注:
وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةٗ يَسۡتَسۡخِرُونَ
14. ተዓምርንም ባዩ ጊዜ ለመሳለቅ ይጣጣራሉ።
阿拉伯语经注:
وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٌ
15. አሉም: «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
阿拉伯语经注:
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
16. «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆን ጊዜ የምንቀስቀስ ነን?
阿拉伯语经注:
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ
17. «የቀድሞዎቹ አባቶቻችንም እንደዚሁ ይቀሰቀሳሉን?» (ይላሉ።)
阿拉伯语经注:
قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ
18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አዎን! እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ
19. እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት:: እነርሱም ወዲያውኑ ምን እንደሚፈጸምባቸው ያያሉ::
阿拉伯语经注:
وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
20. «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው።» (ይላሉም)
阿拉伯语经注:
هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
21. «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉት የነበራችት መለያው ቀን ነው።» ይባላሉ።
阿拉伯语经注:
۞ ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ
22. (ለመላዕክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ከአላህ ሌላ ይገዟቸው የነበሩትንም ጣዖታት በአንድ ሰብስቡ።
阿拉伯语经注:
مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ
23. ከአላህ ውጭ (ይገዟቸው የነበሩትን ሰብስቡ)። ከዚያም ወደ ገሀነም መንገድ ምሯቸው።
阿拉伯语经注:
وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ
24. «እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና አቁሟቸዉም።» (ይባላል።)
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 隋法提
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭