Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 安法里   段:

አል-አንፋል

يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡأَنفَالِۖ قُلِ ٱلۡأَنفَالُ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَصۡلِحُواْ ذَاتَ بَيۡنِكُمۡۖ وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦርነት ከተማረኩ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «በጦርነት የተዘረፉ ገንዘቦች የአላህና የመልዕክተኛው ናቸው:: ስለዚህ አላህን ፍሩ:: በመካከላችሁ ያለውንም ሁኔታ አሳምሩ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَإِذَا تُلِيَتۡ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُهُۥ زَادَتۡهُمۡ إِيمَٰنٗا وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ
2. ፍጹም ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩ፤ በእነርሱም ላይ የቁርኣን አናቅጽ በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸውና በጌታቸው ላይ ብቻም የሚመኩት ብቻ ናቸው::
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
3. እነዚያ ሰላትንም (ወቅቱን ጠብቀውና ደንቡን አሟልተው) የሚሰግዱና ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው::
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ حَقّٗاۚ لَّهُمۡ دَرَجَٰتٌ عِندَ رَبِّهِمۡ وَمَغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ
4. እነዚያ ትክክለኛ አማኞች ማለት እነርሱው ናቸው:: ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ብዙ ደረጃዎች፤ የአላህ ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::
阿拉伯语经注:
كَمَآ أَخۡرَجَكَ رَبُّكَ مِنۢ بَيۡتِكَ بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّ فَرِيقٗا مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لَكَٰرِهُونَ
5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ይህ በምርኮ ክፍያ ሂደት ላይ የታየው የከፊሉ ሰው መጥላት ምሳሌው) ከአማኞች ከፊሉ እየጠሉ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ሆነህ እንዳወጣህ ምሳሌ ነው::
阿拉伯语经注:
يُجَٰدِلُونَكَ فِي ٱلۡحَقِّ بَعۡدَ مَا تَبَيَّنَ كَأَنَّمَا يُسَاقُونَ إِلَى ٱلۡمَوۡتِ وَهُمۡ يَنظُرُونَ
6.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ እያዩ ወደ ሞት እንደሚነዱ ሆነው በእውነቱ ነገር ላይ በመጋደል ግዴታነት ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል::
阿拉伯语经注:
وَإِذۡ يَعِدُكُمُ ٱللَّهُ إِحۡدَى ٱلطَّآئِفَتَيۡنِ أَنَّهَا لَكُمۡ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيۡرَ ذَاتِ ٱلشَّوۡكَةِ تَكُونُ لَكُمۡ وَيُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُحِقَّ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَيَقۡطَعَ دَابِرَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
7. (እናንተ ተከራካሪዎች ሆይ!)፤ አላህ ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛዋን ለእናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁና የኃይል ባለቤት ያልሆነችውን የነጋዴይቱን ቡድን ለእናንተ ልትሆን በወደዳችሁ ጊዜ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነቱን ማረጋገጡን ሊገልጽና የካሓዲያንንም መጨረሻ ሊቆርጥ በፈለገ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)::
阿拉伯语经注:
لِيُحِقَّ ٱلۡحَقَّ وَيُبۡطِلَ ٱلۡبَٰطِلَ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
8. ይህንንም ያደረገው አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥና ክህደትን ሊያጠፋ ነው::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 安法里
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭