Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录


含义的翻译 章: 安法里   段:
فَلَمۡ تَقۡتُلُوهُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمۡۚ وَمَا رَمَيۡتَ إِذۡ رَمَيۡتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ وَلِيُبۡلِيَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ مِنۡهُ بَلَآءً حَسَنًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
17. እናንተ አልገደላችኋቸዉም:: ግን አላህ ገደላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጭብጥን አፈር በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም:: ግን አላህ ወረወረ። አማኞችን ሁሉ ከእርሱ የሆነን መልካም ፈተናን ለመፈተን ይህንን አደረገ። አላህም ሁሉን ሰሚ፤ ሁሉንም አዋቂ ነውና::
阿拉伯语经注:
ذَٰلِكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُوهِنُ كَيۡدِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
18. ይህ ከአላህ የተቸረ ዕውነት ነው:: አላህ የከሓዲያንን ሁሉ ተንኮል አድካሚ ነውና::
阿拉伯语经注:
إِن تَسۡتَفۡتِحُواْ فَقَدۡ جَآءَكُمُ ٱلۡفَتۡحُۖ وَإِن تَنتَهُواْ فَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۖ وَإِن تَعُودُواْ نَعُدۡ وَلَن تُغۡنِيَ عَنكُمۡ فِئَتُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَوۡ كَثُرَتۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
19. (ከሓዲያን ሆይ!) ፍትሕን ብትጠይቁ ፍትሁ በእርግጥ መጥቶላችኋል:: ክሕደትና መዋጋታችሁን ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ወደ መጋደል ብትመለሱም እንመለሳለን:: ሰራዊታችሁ ብትበዛም እንኳ ለእናንተ ምንም አትጠቅማችሁም:: አላህ ሁልጊዜም ከትክክለኛ አማኞች ጋር ነውና::
阿拉伯语经注:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ وَأَنتُمۡ تَسۡمَعُونَ
20. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ:: እናንተም እየሰማችሁ ከእርሱ አትሽሹ::
阿拉伯语经注:
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ
21. እንደነዚያም የማይሰሙ ሲሆኑ ሰማን እንዳሉትም አትሁኑ::
阿拉伯语经注:
۞ إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلصُّمُّ ٱلۡبُكۡمُ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡقِلُونَ
22. ከተንቀሳቃሾች ፍጡራን ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎዎች ማለት እነዚያ ሐቅን የማይሰሙ ደንቆሮዎቹ፣ እውነትን የማይናገሩና እውነታን የማያስተውሉት ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَوۡ عَلِمَ ٱللَّهُ فِيهِمۡ خَيۡرٗا لَّأَسۡمَعَهُمۡۖ وَلَوۡ أَسۡمَعَهُمۡ لَتَوَلَّواْ وَّهُم مُّعۡرِضُونَ
23. በውስጣቸው ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ የመረዳትን መስማት ያሰማቸው ነበር:: ደግ የሌለባቸው መሆኑን እያወቀ ባሰማቸዉም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተዉ ሆነው በሸሹ ነበር።
阿拉伯语经注:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱسۡتَجِيبُواْ لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمۡ لِمَا يُحۡيِيكُمۡۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَحُولُ بَيۡنَ ٱلۡمَرۡءِ وَقَلۡبِهِۦ وَأَنَّهُۥٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ
24. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልዕክተኛው) ህያው ወደ የሚያደርጋችሁ (እምነት) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልዕክተኛው ታዘዙ:: አላህ በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መሆኑንና ወደ እርሱም የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::
阿拉伯语经注:
وَٱتَّقُواْ فِتۡنَةٗ لَّا تُصِيبَنَّ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنكُمۡ خَآصَّةٗۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
25. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትጎዳን ፈተና ተጠንቀቁ:: አላህ ቅጣቱ ብርቱ መሆኑንም እወቁ::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 安法里
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭