Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ   አንቀጽ:
وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَخۡرِجُوهُم مِّن قَرۡيَتِكُمۡۖ إِنَّهُمۡ أُنَاسٞ يَتَطَهَّرُونَ
82. የሕዝቦቹም መልስ «ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸው።» ከማለት ውጭ ሌላ አልነበረም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ
83. ከዚያም እርሱንና ቤተሰቦቹን አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ ለጥፋት ከቀሩት ሰዎች ሆነች::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
84. በእነርሱ ላይ የእሳት ዝናብን አዘነብንባቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኃጢአተኞች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ قَدۡ جَآءَتۡكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡۖ فَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بَعۡدَ إِصۡلَٰحِهَاۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
85. ወደ መድየን ሕዝብም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። አላቸዉም: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ በስተቀር ምንም አምላክ የላችሁም:: ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ መጥቶላችኋል:: ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: የሰዎችንም ገንዘቦቻቸውን አታጉድሉባቸው:: ምድርንም ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። አማኞች ከሆናችሁ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَقۡعُدُواْ بِكُلِّ صِرَٰطٖ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ بِهِۦ وَتَبۡغُونَهَا عِوَجٗاۚ وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ كُنتُمۡ قَلِيلٗا فَكَثَّرَكُمۡۖ وَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
86. «ሰዎችን የምታስፈራሩ፤ ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱና የአላህን መንገድ መጥመሟንም የምትፈልጉ ሆናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ:: ጥቂቶች በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የአጥፊ ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረም ተመልከቱ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِن كَانَ طَآئِفَةٞ مِّنكُمۡ ءَامَنُواْ بِٱلَّذِيٓ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦ وَطَآئِفَةٞ لَّمۡ يُؤۡمِنُواْ فَٱصۡبِرُواْ حَتَّىٰ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ بَيۡنَنَاۚ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ
87. «ከናንተም መካከል እኔ በተላኩበት ያመኑ ቡድኖችና ያላመኑ ቡድኖች ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሡ:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ እጅግ በላጭ ነው።»
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ከአፍሪካ አካዳሚ የተገኘ ‐ ተርጓሚ መሐመድ ዘይን ዘህረዲን

መዝጋት