Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ   አንቀጽ:
وَقَطَّعۡنَٰهُمُ ٱثۡنَتَيۡ عَشۡرَةَ أَسۡبَاطًا أُمَمٗاۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسۡتَسۡقَىٰهُ قَوۡمُهُۥٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡحَجَرَۖ فَٱنۢبَجَسَتۡ مِنۡهُ ٱثۡنَتَا عَشۡرَةَ عَيۡنٗاۖ قَدۡ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٖ مَّشۡرَبَهُمۡۚ وَظَلَّلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡغَمَٰمَ وَأَنزَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰۖ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
160. የሙሳን ህዝቦች አስራ ሁለት ነገዶች አድርገን ከፋፈልናቸው:: ወደ ሙሳም ወገኖቹ ውሃን በፈለጉበት ጊዜ ድንጋዩን በበትርህ ምታው ስንል ላክን:: (መታዉም) አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ:: ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ:: በእነርሱም ላይ ዳመናን አጠለልን:: በእነርሱም ላይ "መንን" እና ድርጭትን አወረድን:: «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ።» አልን:: ጸጋዎቻችንን በመካዳቸው አልበደሉንም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ህዝቦች ነበሩ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذۡ قِيلَ لَهُمُ ٱسۡكُنُواْ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةَ وَكُلُواْ مِنۡهَا حَيۡثُ شِئۡتُمۡ وَقُولُواْ حِطَّةٞ وَٱدۡخُلُواْ ٱلۡبَابَ سُجَّدٗا نَّغۡفِرۡ لَكُمۡ خَطِيٓـَٰٔتِكُمۡۚ سَنَزِيدُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለነርሱም «በዚች ከተማ ተቀመጡ:: ከእርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ ብሉ:: ‹የምንፈልገው የኃጢታችንን መርገፍ ብቻ ነው።› በሉም:: የከተማይቱን በር አጎንብሳችሁ ግቡ ኃጢአቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና:: በጎ ለሠሩት ሰዎች በእርግጥ እንጨምራለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَبَدَّلَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡ قَوۡلًا غَيۡرَ ٱلَّذِي قِيلَ لَهُمۡ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِجۡزٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُواْ يَظۡلِمُونَ
162. ከእነርሱም ውስጥ እነዚያ ራሳቸውን የበደሉ ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የሆነን ቃል ለወጡ:: በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል ምክንያት መአትን ከሰማይ ላክንባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَسۡـَٔلۡهُمۡ عَنِ ٱلۡقَرۡيَةِ ٱلَّتِي كَانَتۡ حَاضِرَةَ ٱلۡبَحۡرِ إِذۡ يَعۡدُونَ فِي ٱلسَّبۡتِ إِذۡ تَأۡتِيهِمۡ حِيتَانُهُمۡ يَوۡمَ سَبۡتِهِمۡ شُرَّعٗا وَيَوۡمَ لَا يَسۡبِتُونَ لَا تَأۡتِيهِمۡۚ كَذَٰلِكَ نَبۡلُوهُم بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ
163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን አሳዎቻቸው የተከማቹ ሆነው በሚመጡላቸው ጊዜ የሆነውን ጠይቃቸው:: ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ በአመፃቸው ምክንያት እንሞክራቸዋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት