Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ   አንቀጽ:
۞ وَإِذۡ نَتَقۡنَا ٱلۡجَبَلَ فَوۡقَهُمۡ كَأَنَّهُۥ ظُلَّةٞ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُۥ وَاقِعُۢ بِهِمۡ خُذُواْ مَآ ءَاتَيۡنَٰكُم بِقُوَّةٖ وَٱذۡكُرُواْ مَا فِيهِ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
171. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ሆኖ ባነሳነውና እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ መሆኑን ባረጋገጡ ጊዜ የሆነውን( አስታውስ):: «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ:: ትጠነቀቁም ዘንድ በዉስጡ ያለውን ተገንዘቡ።» አልን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذۡ أَخَذَ رَبُّكَ مِنۢ بَنِيٓ ءَادَمَ مِن ظُهُورِهِمۡ ذُرِّيَّتَهُمۡ وَأَشۡهَدَهُمۡ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَلَسۡتُ بِرَبِّكُمۡۖ قَالُواْ بَلَىٰ شَهِدۡنَآۚ أَن تَقُولُواْ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ إِنَّا كُنَّا عَنۡ هَٰذَا غَٰفِلِينَ
172. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ። በትንሳኤ ቀን «ከዚህ ቃል ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَوۡ تَقُولُوٓاْ إِنَّمَآ أَشۡرَكَ ءَابَآؤُنَا مِن قَبۡلُ وَكُنَّا ذُرِّيَّةٗ مِّنۢ بَعۡدِهِمۡۖ أَفَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلۡمُبۡطِلُونَ
173. ወይም «ጣኦታትን ያጋሩት ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው:: እኛም ከእነርሱ በኋላ የሆንን ዘሮች ነበርን አጥፊዎቹ በሠሩት ጥፋት እኛን ታጠፋናለህን?» እንዳትሉ አስመሰከርናችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
174. ልክ እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አናቅጽን እናብራራለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ ٱلَّذِيٓ ءَاتَيۡنَٰهُ ءَايَٰتِنَا فَٱنسَلَخَ مِنۡهَا فَأَتۡبَعَهُ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَكَانَ مِنَ ٱلۡغَاوِينَ
175. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከዚያ እርሱም ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን በዚህም ምክንያት ከጠማሞቹ የሆነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَوۡ شِئۡنَا لَرَفَعۡنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخۡلَدَ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُۚ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلۡكَلۡبِ إِن تَحۡمِلۡ عَلَيۡهِ يَلۡهَثۡ أَوۡ تَتۡرُكۡهُ يَلۡهَثۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۚ فَٱقۡصُصِ ٱلۡقَصَصَ لَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ
176. ብንፈልግ ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር:: እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ:: ፍላጎቱንም ተከተለ:: ብጤዉም ብታባርረዉም ባታባርረዉም ምላሱን አውጥቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ነው:: ይህ የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
سَآءَ مَثَلًا ٱلۡقَوۡمُ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَأَنفُسَهُمۡ كَانُواْ يَظۡلِمُونَ
177. የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِيۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
178. አላህ የሚያቀናው ሰው ሁሉ ቅን ማለት እርሱው ነው:: የሚያጠማቸዉም ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ማለት እነርሱው ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ከአፍሪካ አካዳሚ የተገኘ ‐ ተርጓሚ መሐመድ ዘይን ዘህረዲን

መዝጋት