Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ   አንቀጽ:
وَإِذۡ قَالَتۡ أُمَّةٞ مِّنۡهُمۡ لِمَ تَعِظُونَ قَوۡمًا ٱللَّهُ مُهۡلِكُهُمۡ أَوۡ مُعَذِّبُهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدٗاۖ قَالُواْ مَعۡذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከፊሎቹ ህዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጫቸው የሆኑትን ህዝቦች ለምን ትገስጻላችሁ?» ባሉ ጊዜ ገሳጮቹም «በጌታችሁ ዘንድ በቂ ምክንያት እንዲሆንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው።» ባሉበት ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَمَّا نَسُواْ مَا ذُكِّرُواْ بِهِۦٓ أَنجَيۡنَا ٱلَّذِينَ يَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلسُّوٓءِ وَأَخَذۡنَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ بِعَذَابِۭ بَـِٔيسِۭ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ
165. የተገሰጹበትንም ነገር በተው ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለክሉትን ክፍሎች አዳንን:: እነዚያንም የበደሉትን ሰዎች ያምጹ በነበሩበት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ቀጣናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَمَّا عَتَوۡاْ عَن مَّا نُهُواْ عَنۡهُ قُلۡنَا لَهُمۡ كُونُواْ قِرَدَةً خَٰسِـِٔينَ
166. ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ሁኑ።» አልን:: (ሆኑም)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذۡ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبۡعَثَنَّ عَلَيۡهِمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَن يَسُومُهُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ ٱلۡعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እስከ ትንሳኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ወገን በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው):: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው:: እርሱም በእርግጥ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَطَّعۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ أُمَمٗاۖ مِّنۡهُمُ ٱلصَّٰلِحُونَ وَمِنۡهُمۡ دُونَ ذَٰلِكَۖ وَبَلَوۡنَٰهُم بِٱلۡحَسَنَٰتِ وَٱلسَّيِّـَٔاتِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
168. (የኢስራኢልን ልጆችን) በምድር ላይ የተለያዩ ህዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው:: ከእነርሱ መልካሞች አሉ:: ከእነርሱም ከዚያ ሌላ የሆኑ አሉ:: ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችና በመከራዎቻች ሞከርናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٞ وَرِثُواْ ٱلۡكِتَٰبَ يَأۡخُذُونَ عَرَضَ هَٰذَا ٱلۡأَدۡنَىٰ وَيَقُولُونَ سَيُغۡفَرُ لَنَا وَإِن يَأۡتِهِمۡ عَرَضٞ مِّثۡلُهُۥ يَأۡخُذُوهُۚ أَلَمۡ يُؤۡخَذۡ عَلَيۡهِم مِّيثَٰقُ ٱلۡكِتَٰبِ أَن لَّا يَقُولُواْ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡحَقَّ وَدَرَسُواْ مَا فِيهِۗ وَٱلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
169. ከኋላቸዉም መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች በእነርሱ ቦታ ተተኩ:: የዚህም የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ:: ብጤዉም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲሆኑ «በሠራነው ለእኛ ምህረት ይደርግልናል።» ይላሉ:: በአላህ ላይ በእውነት በስተቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸዉምን? በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን? የመጨረሻይቱን አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ በላጭ ናት:: አታውቁምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلَّذِينَ يُمَسِّكُونَ بِٱلۡكِتَٰبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُصۡلِحِينَ
170. እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ፤ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ ሁሉ (ምንዳቸውን እንከፍላቸዋለን):: እኛ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አናጠፋምና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-አዕራፍ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት