Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: Gafir   Ajet:

ጋፊር

حمٓ
1. ሓ፤ ሚይም፤
Tefsiri na arapskom jeziku:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ
2. የመጽሐፉን መውረድ አሸናፊው አዋቂው ከሆነው ከአላህ ብቻ ነው::
Tefsiri na arapskom jeziku:
غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوۡبِ شَدِيدِ ٱلۡعِقَابِ ذِي ٱلطَّوۡلِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ إِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ
3. ኃጢአት መሀሪና ጸጸትን ተቀባይ፤ ቅጣተ ብርቱ፤ የልግስና ባለቤት ከሆነው አላህ ብቻ የተወረደ ነው:: ከእርሱ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ የለም:: መመለሻዉም ወደ እርሱ ብቻ ነው::
Tefsiri na arapskom jeziku:
مَا يُجَٰدِلُ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَلَا يَغۡرُرۡكَ تَقَلُّبُهُمۡ فِي ٱلۡبِلَٰدِ
4. በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡
Tefsiri na arapskom jeziku:
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۖ وَهَمَّتۡ كُلُّ أُمَّةِۭ بِرَسُولِهِمۡ لِيَأۡخُذُوهُۖ وَجَٰدَلُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّ فَأَخَذۡتُهُمۡۖ فَكَيۡفَ كَانَ عِقَابِ
5. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦች ከኋላቸዉም አህዛቦች አስተባበሉ:: ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፤ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ:: ያዝኳቸዉም። ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَكَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ
6. ልክ እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በአላህ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች::
Tefsiri na arapskom jeziku:
ٱلَّذِينَ يَحۡمِلُونَ ٱلۡعَرۡشَ وَمَنۡ حَوۡلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيُؤۡمِنُونَ بِهِۦ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْۖ رَبَّنَا وَسِعۡتَ كُلَّ شَيۡءٖ رَّحۡمَةٗ وَعِلۡمٗا فَٱغۡفِرۡ لِلَّذِينَ تَابُواْ وَٱتَّبَعُواْ سَبِيلَكَ وَقِهِمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤ በእርሱም ያምናሉ። ለነዚያ ላመኑትም (እንዲህ እያሉ) ምህረትን ይለምኑላቸዋል: «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምህረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፤
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: Gafir
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje