Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: Gafir   Ajet:
رَبَّنَا وَأَدۡخِلۡهُمۡ جَنَّٰتِ عَدۡنٍ ٱلَّتِي وَعَدتَّهُمۡ وَمَن صَلَحَ مِنۡ ءَابَآئِهِمۡ وَأَزۡوَٰجِهِمۡ وَذُرِّيَّٰتِهِمۡۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
8. «ጌታችን ሆይ! እነርሱም ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸዉም ከዝርዮቻቸዉም የበጀውን ሁሉ እነዚያንም ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አስገባቸው፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው ነህና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَقِهِمُ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ وَمَن تَقِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ يَوۡمَئِذٖ فَقَدۡ رَحِمۡتَهُۥۚ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
9. «ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፤ በዚያ ቀንም የምትጠብቀውን በእርግጥ አዘንክለት:: ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው::»
Tefsiri na arapskom jeziku:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُنَادَوۡنَ لَمَقۡتُ ٱللَّهِ أَكۡبَرُ مِن مَّقۡتِكُمۡ أَنفُسَكُمۡ إِذۡ تُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلۡإِيمَٰنِ فَتَكۡفُرُونَ
10. እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው።» በማለት ይጠራሉ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
قَالُواْ رَبَّنَآ أَمَتَّنَا ٱثۡنَتَيۡنِ وَأَحۡيَيۡتَنَا ٱثۡنَتَيۡنِ فَٱعۡتَرَفۡنَا بِذُنُوبِنَا فَهَلۡ إِلَىٰ خُرُوجٖ مِّن سَبِيلٖ
11. «ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን:: ሁለትንም ሕይወት ህያው አደረግከን:: በኃጢአቶቻችንም መሰከርን። ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
ذَٰلِكُم بِأَنَّهُۥٓ إِذَا دُعِيَ ٱللَّهُ وَحۡدَهُۥ كَفَرۡتُمۡ وَإِن يُشۡرَكۡ بِهِۦ تُؤۡمِنُواْۚ فَٱلۡحُكۡمُ لِلَّهِ ٱلۡعَلِيِّ ٱلۡكَبِيرِ
12. (ከሀዲያን ሆይ!) «ይሃችሁ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለሆናችሁ ነው:: ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለሆነው አላህ ብቻ ነው::» (ይባላሉ)
Tefsiri na arapskom jeziku:
هُوَ ٱلَّذِي يُرِيكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ وَيُنَزِّلُ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ رِزۡقٗاۚ وَمَا يَتَذَكَّرُ إِلَّا مَن يُنِيبُ
13. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ለአምላክነቱ ምልክቶችን የሚያሳያችሁ፤ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው:: ወደርሱም የሚመለስ ሰው ቢሆን እንጂ ሌላው አይገሰጽም::
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَٱدۡعُواْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَٰفِرُونَ
14. አላህንም ከሓዲያን ቢጠሉም (እንኳ) ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
رَفِيعُ ٱلدَّرَجَٰتِ ذُو ٱلۡعَرۡشِ يُلۡقِي ٱلرُّوحَ مِنۡ أَمۡرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ لِيُنذِرَ يَوۡمَ ٱلتَّلَاقِ
15. እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው:: የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ ራዕይን ያወርዳል::
Tefsiri na arapskom jeziku:
يَوۡمَ هُم بَٰرِزُونَۖ لَا يَخۡفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِنۡهُمۡ شَيۡءٞۚ لِّمَنِ ٱلۡمُلۡكُ ٱلۡيَوۡمَۖ لِلَّهِ ٱلۡوَٰحِدِ ٱلۡقَهَّارِ
16. እነርሱ ከመቃብር በሚወጡበት ቀን ከእነርሱ ምንም ነገር በአላህ ላይ አይደበቅም:: «ንግስናው ዛሬ ለማን ነው?» ይባላል:: «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» ይባላል::
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: Gafir
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje