Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: Gafir   Ajet:
۞ وَيَٰقَوۡمِ مَا لِيٓ أَدۡعُوكُمۡ إِلَى ٱلنَّجَوٰةِ وَتَدۡعُونَنِيٓ إِلَى ٱلنَّارِ
41. «ወገኖቼ ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለእኔ ምን አለኝ!
Tefsiri na arapskom jeziku:
تَدۡعُونَنِي لِأَكۡفُرَ بِٱللَّهِ وَأُشۡرِكَ بِهِۦ مَا لَيۡسَ لِي بِهِۦ عِلۡمٞ وَأَنَا۠ أَدۡعُوكُمۡ إِلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡغَفَّٰرِ
42. « (እናንተ) በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ እውቀቱ የሌለኝ ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ! እኔ አሸናፊና መሀሪ ወደ ሆነው አላህ እጠራችኋለሁ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
لَا جَرَمَ أَنَّمَا تَدۡعُونَنِيٓ إِلَيۡهِ لَيۡسَ لَهُۥ دَعۡوَةٞ فِي ٱلدُّنۡيَا وَلَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَنَّ مَرَدَّنَآ إِلَى ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ
43. «በእርግጥ ወደ እርሱ የምትጠሩኝ ጣዖት ለእርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተሰሚ ጥሪ የለዉም። መመለሻችንም እርግጥ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ወሰን አላፊዎችም እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَسَتَذۡكُرُونَ مَآ أَقُولُ لَكُمۡۚ وَأُفَوِّضُ أَمۡرِيٓ إِلَى ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ
44. «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሱታላችሁ:: ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።»
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَوَقَىٰهُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِ مَا مَكَرُواْۖ وَحَاقَ بِـَٔالِ فِرۡعَوۡنَ سُوٓءُ ٱلۡعَذَابِ
45. ካሴሯቸዉም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው::
Tefsiri na arapskom jeziku:
ٱلنَّارُ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا غُدُوّٗا وَعَشِيّٗاۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدۡخِلُوٓاْ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ أَشَدَّ ٱلۡعَذَابِ
46. እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት ገሀነምን አስገቧቸው» ይባላል።
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَإِذۡ يَتَحَآجُّونَ فِي ٱلنَّارِ فَيَقُولُ ٱلضُّعَفَٰٓؤُاْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُنَّا لَكُمۡ تَبَعٗا فَهَلۡ أَنتُم مُّغۡنُونَ عَنَّا نَصِيبٗا مِّنَ ٱلنَّارِ
47. በእሳት ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ አስታውስ: ደካማዎቹም ለነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ አሁን ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُلّٞ فِيهَآ إِنَّ ٱللَّهَ قَدۡ حَكَمَ بَيۡنَ ٱلۡعِبَادِ
48. እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈርዷል» ይላሉ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ فِي ٱلنَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ٱدۡعُواْ رَبَّكُمۡ يُخَفِّفۡ عَنَّا يَوۡمٗا مِّنَ ٱلۡعَذَابِ
49. እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ ለአንድም ቀን ያቃልልን።» ይላሉ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: Gafir
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje