કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ મુદષષિર   આયત:

ሱረቱ አል ሙደሲር

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُدَّثِّرُ
1. አንተ (ልብስ) ደራቢው ሆይ!
અરબી તફસીરો:
قُمۡ فَأَنذِرۡ
2. ተነሳና (ህዝቦችህን) አስጠንቅቅ።
અરબી તફસીરો:
وَرَبَّكَ فَكَبِّرۡ
3. ጌታህንም አክብር::
અરબી તફસીરો:
وَثِيَابَكَ فَطَهِّرۡ
4. ልብስህንም አጥራ::
અરબી તફસીરો:
وَٱلرُّجۡزَ فَٱهۡجُرۡ
5. ጣዖትንም ራቅ::
અરબી તફસીરો:
وَلَا تَمۡنُن تَسۡتَكۡثِرُ
6. ማብዛትንም የምትፈልግ ሆነህ አትለግስ::
અરબી તફસીરો:
وَلِرَبِّكَ فَٱصۡبِرۡ
7. (ብዙ ዒባዳን ከመስራት አትድከም):: ለጌታህም (ትዕዘዛዝ) ታገስ።
અરબી તફસીરો:
فَإِذَا نُقِرَ فِي ٱلنَّاقُورِ
8. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፤
અરબી તફસીરો:
فَذَٰلِكَ يَوۡمَئِذٖ يَوۡمٌ عَسِيرٌ
9. ይህን ጊዜ ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው።
અરબી તફસીરો:
عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ غَيۡرُ يَسِيرٖ
10. (በተለይ) በከሓዲያን ላይ ገር ያልሆነ ቀን ነው።
અરબી તફસીરો:
ذَرۡنِي وَمَنۡ خَلَقۡتُ وَحِيدٗا
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በብቸኝነት ከፈጠርኩት ጋር ተወኝ።
અરબી તફસીરો:
وَجَعَلۡتُ لَهُۥ مَالٗا مَّمۡدُودٗا
12. ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በዓይነቱ) አደረግኩለት።
અરબી તફસીરો:
وَبَنِينَ شُهُودٗا
13. በየአደባባዩ ተገኝ የሆኑ ወንዶች ልጆችንም ሰጠሁት።
અરબી તફસીરો:
وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمۡهِيدٗا
14. ለእርሱም ኑሮውን መዘርጋትን ዘረጋሁለት፤
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ يَطۡمَعُ أَنۡ أَزِيدَ
15. ከዚያ ልጨምርለት ይከጅላል::
અરબી તફસીરો:
كَلَّآۖ إِنَّهُۥ كَانَ لِأٓيَٰتِنَا عَنِيدٗا
16. ሰው ይከልከል! እርሱ ለአናቅጻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበርና።
અરબી તફસીરો:
سَأُرۡهِقُهُۥ صَعُودًا
17. በእርግጥ (ገሀነም ውስጥ) ችግርን አስገድደዋለሁ።
અરબી તફસીરો:
إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ
18. እርሱ (በቁርኣን ጉዳይ) አሰበ፤ ገመተም።
અરબી તફસીરો:
فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ
19. እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ!
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ
20. ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ!
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ نَظَرَ
21. ከዚያም እንደገና (በቁርኣን ጉዳይ) ተመለከተ።
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ
22. ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም::
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ
23. ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም::
અરબી તફસીરો:
فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ يُؤۡثَرُ
24. «ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
અરબી તફસીરો:
إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ
25. «ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ::
અરબી તફસીરો:
سَأُصۡلِيهِ سَقَرَ
26. ሰቀር (በተባለ የገሀነም ዋሻ ውስጥ) በእርግጥ አስገባዋለሁ::
અરબી તફસીરો:
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سَقَرُ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰቀር ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
અરબી તફસીરો:
لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ
28. (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም::
અરબી તફસીરો:
لَوَّاحَةٞ لِّلۡبَشَرِ
29. የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት።
અરબી તફસીરો:
عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ
30. በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት::
અરબી તફસીરો:
وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ
31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::
અરબી તફસીરો:
كَلَّا وَٱلۡقَمَرِ
32. (ከክህደት) ይከልከሉ:: በጨረቃ (እምላለሁ)፤
અરબી તફસીરો:
وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ
33. በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤
અરબી તફસીરો:
وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ
34. በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ።
અરબી તફસીરો:
إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ
35. (ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤
અરબી તફસીરો:
نَذِيرٗا لِّلۡبَشَرِ
36. ለሰዎች አስፈራሪ ናት።
અરબી તફસીરો:
لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ
37. ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤
અરબી તફસીરો:
كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ
38. ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት::
અરબી તફસીરો:
إِلَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡيَمِينِ
39. እነዚያ መዝገባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚሰጡት ብቻ ሲቀሩ::
અરબી તફસીરો:
فِي جَنَّٰتٖ يَتَسَآءَلُونَ
40. (እነርሱማ) በገነቶች ውስጥ ሁነው እርስ በራሳቸው ይጠያየቃሉ::
અરબી તફસીરો:
عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
41. ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ)
અરબી તફસીરો:
مَا سَلَكَكُمۡ فِي سَقَرَ
42. (ከዚያ ለእነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል።) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
અરબી તફસીરો:
قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ
43. «ከሰጋጆች አልነበርንም።
અરબી તફસીરો:
وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ
44. «ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም።
અરબી તફસીરો:
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ
45. «ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር።
અરબી તફસીરો:
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
46. «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤
અરબી તફસીરો:
حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ
47. «እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ
અરબી તફસીરો:
فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ
48. እናም በዚያ ቀን የአማላጆች (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም።
અરબી તફસીરો:
فَمَا لَهُمۡ عَنِ ٱلتَّذۡكِرَةِ مُعۡرِضِينَ
49. ከ(ቁርኣን) ከግሳጼም የሚያፈገፍጉበት ምን ምክኒያት አላቸው?
અરબી તફસીરો:
كَأَنَّهُمۡ حُمُرٞ مُّسۡتَنفِرَةٞ
50. እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዩች ይመስላሉ::
અરબી તફસીરો:
فَرَّتۡ مِن قَسۡوَرَةِۭ
51. ከአንበሳ የሸሹ
અરબી તફસીરો:
بَلۡ يُرِيدُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُؤۡتَىٰ صُحُفٗا مُّنَشَّرَةٗ
52. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል ለእያንዳንዱ ሰው የተዘረጉ ጹሑፎችን በእጁ እንዲሰጥ ይፈልጋል::
અરબી તફસીરો:
كَلَّاۖ بَل لَّا يَخَافُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ
53. ከዚህ መሰል ተግባራቸው ይከልከሉ:: ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት አይፈሩም::
અરબી તફસીરો:
كَلَّآ إِنَّهُۥ تَذۡكِرَةٞ
54. ይከልከሉ፤እርሱ(ቁርአን) መገሰጫ ነው።
અરબી તફસીરો:
فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ
55. ስለዚህ የፈለገ ሰው ቁርኣንን ይገሰጽበታል::
અરબી તફસીરો:
وَمَا يَذۡكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ هُوَ أَهۡلُ ٱلتَّقۡوَىٰ وَأَهۡلُ ٱلۡمَغۡفِرَةِ
56. ሆኖም (ሰዎች) አላህ ካልፈለገ በስተቀር አይገሰጹም:: አላህ የመፈራት ባለቤት ነው:: (ለፈሩትም) የምህረት ባለቤት ነው::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ મુદષષિર
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

અમ્હેરિક ભાષાતર

બંધ કરો