Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:

አል-አንዓም

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَۖ ثُمَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ
1.ምስጋና ሁሉ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረ ጨለማዎችንና ብርሃንን ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው:: ከዚያም እነዚያ በእርሱ የካዱ ሁሉ ጣዖታትን ከጌታቸው ጋር ያስተካክላሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٖ ثُمَّ قَضَىٰٓ أَجَلٗاۖ وَأَجَلٞ مُّسَمًّى عِندَهُۥۖ ثُمَّ أَنتُمۡ تَمۡتَرُونَ
2. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም የሞት ጊዜን የወሰነ ነው:: እርሱም ዘንድ ለትንሳኤ የተወሰነ ጊዜ አለ:: ከዚያም እናንተ በመቀስቀሳችሁ ትጠራጠራላችሁን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَهُوَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ يَعۡلَمُ سِرَّكُمۡ وَجَهۡرَكُمۡ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡسِبُونَ
3. እርሱም ያ በሰማያትም በምድርም ሊገዙት የሚገባው አላህ ነው:: (ሰዎች ሆይ!) ሚስጥራችሁንም ሆነ ግልፃችሁን ጠንቅቆ ያውቃል። የምትሰሩትን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ
⒋ ከጌታቸው አናቅጽ አንዱም አይመጣላቸዉም ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَقَدۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَسَوۡفَ يَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
5. ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜም በእርግጥ አስተባበሉ:: ግን የእዚያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች ቅጣት ይመጣባቸዋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ مَّكَّنَّٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَا لَمۡ نُمَكِّن لَّكُمۡ وَأَرۡسَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡهِم مِّدۡرَارٗا وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَنۡهَٰرَ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ
6. ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች መካከል ብዙዎቹን ማጥፋታችንን አላዩምን? ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው:: በእነርሱም ላይ ዝናብን የተከታተለ ሲሆን ላክን:: ወንዞችንም በስራቸው እንዲፈሱ አደረግን:: በኃጢአቶቻቸዉም ምክንያት አጠፋናቸው:: ከኋላቸዉም ሌሎችን ሰዎች በየክፍለ ዘመኑ አስገኘን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَوۡ نَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ كِتَٰبٗا فِي قِرۡطَاسٖ فَلَمَسُوهُ بِأَيۡدِيهِمۡ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ
7. በእነርሱ ላይ በወረቀት የተፃፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ ከሓዲያን «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ባሉ ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ مَلَكٞۖ وَلَوۡ أَنزَلۡنَا مَلَكٗا لَّقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ثُمَّ لَا يُنظَرُونَ
8. «በእርሱ (በሙሐመድ) ላይ መልአክ ለምን አይወረድለትም?» አሉ። ነገር ግን መላዕክን ባወረድንለትና (ባያምኑ ኖሮ) የጥፋታቸው ነገር በተፈረደ ነበር:: ከዚያም አይቆዩም ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ