Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
۞ وَلَوۡ أَنَّنَا نَزَّلۡنَآ إِلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ وَكَلَّمَهُمُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَحَشَرۡنَا عَلَيۡهِمۡ كُلَّ شَيۡءٖ قُبُلٗا مَّا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُوٓاْ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ يَجۡهَلُونَ
111. እኛ ወደ እነርሱ መላዕክትን ባወረድንም ኖሮ ሙታንን ባነጋገሩዋቸውና ነገሩን ሁሉ በቡድን በቡድን በእነርሱ ላይ በሰበሰብንም ኖሮ አላህ ካልሻ በስተቀር የሚያምኑ ባልሆኑ ነበር:: ግን አብዛኞቻቸው ይህንን እውነታ ይስታሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوّٗا شَيَٰطِينَ ٱلۡإِنسِ وَٱلۡجِنِّ يُوحِي بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٖ زُخۡرُفَ ٱلۡقَوۡلِ غُرُورٗاۚ وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُۖ فَذَرۡهُمۡ وَمَا يَفۡتَرُونَ
112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ለነብያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የሆኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን:: ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል የተዋበን ንግግር ይጥላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በፈለገ ኖሮ ይህን ጸያፍ ተግባር ባልሰሩት ነበር:: ከቅጥፈታቸዉም ጋር ተዋቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِتَصۡغَىٰٓ إِلَيۡهِ أَفۡـِٔدَةُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ وَلِيَرۡضَوۡهُ وَلِيَقۡتَرِفُواْ مَا هُم مُّقۡتَرِفُونَ
113. ሊያታልሉ የሚጥሩትና የነዚያም በመጨረሻይቱ ህይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደ እርሱ እንዲያዘነብሉ፤ እንዲወዱትና እነርሱ ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡتَغِي حَكَمٗا وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ إِلَيۡكُمُ ٱلۡكِتَٰبَ مُفَصَّلٗاۚ وَٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡلَمُونَ أَنَّهُۥ مُنَزَّلٞ مِّن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّۖ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ
114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ መጽሐፍን የተብራራ ሆኖ ወደ እናንተ ያወረደ ሲሆን ከአላህ ሌላ ዳኛን እፈልጋለሁን? በላቸው:: እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ቁርኣን ከጌታህ ዘንድ በእውነት የተወረደ መሆኑን በትክክል ያውቃሉ:: እናም ከተጠራጣሪዎቹ አትሁን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ صِدۡقٗا وَعَدۡلٗاۚ لَّا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِهِۦۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
115. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተፈጸመች:: ለቃላቱ ምንጊዜም ለዋጭ የለም:: እርሱ ሰሚውና አዋቂው ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن تُطِعۡ أَكۡثَرَ مَن فِي ٱلۡأَرۡضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ
116. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ካሉት መካከል አብዛኞቹን ብትከተል የአላህን መንገድ ያሳስቱሀል:: ጥርጣሬን እንጂ ሌላን አይከተሉምና:: እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ مَن يَضِلُّ عَن سَبِيلِهِۦۖ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ
117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከመንገዱ የሚሳሳቱትን አዋቂ ነው:: እርሱም ተመሪዎቹን እንዲሁ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَكُلُواْ مِمَّا ذُكِرَ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ إِن كُنتُم بِـَٔايَٰتِهِۦ مُؤۡمِنِينَ
118. (ሰዎች ሆይ!) በአናቅጹም አማኞች እንደሆናችሁ ሲታረድ የአላህ ስም በእርሱ ላይ የተወሳበትን እንሰሳ ብቻ ብሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ