Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
فَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل رَّبُّكُمۡ ذُو رَحۡمَةٖ وَٰسِعَةٖ وَلَا يُرَدُّ بَأۡسُهُۥ عَنِ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉልህ፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው:: ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ህዝቦች ላይ አይመለስም።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
سَيَقُولُ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكۡنَا وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ حَتَّىٰ ذَاقُواْ بَأۡسَنَاۗ قُلۡ هَلۡ عِندَكُم مِّنۡ عِلۡمٖ فَتُخۡرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَخۡرُصُونَ
148. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች አላህ በሻ ኖሮ እኛም ሆነ አባቶቻችን በአላህ ባላጋራንና አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር።» ይላሉ:: ልክ እነዚህ እንደ አስተባበሉህ ሁሉ እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩ ሕዝቦችም ብርቱ ቅጣታችንን እስከ ቀመሱ ድረስ አስተባበሉ:: «ለእኛ ታስተምሩን ዘንድ ማጋራታችሁን ለመውደዱ እናንተ ዘንድ እውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አትከተሉም:: እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ فَلِلَّهِ ٱلۡحُجَّةُ ٱلۡبَٰلِغَةُۖ فَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ
149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የተሟላው ማስረጃ የአላህ ማስረጃ ብቻ ነው:: በፈለገ ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ هَلُمَّ شُهَدَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ يَشۡهَدُونَ أَنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَ هَٰذَاۖ فَإِن شَهِدُواْ فَلَا تَشۡهَدۡ مَعَهُمۡۚ وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ وَهُم بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ
150. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ አላህ ይህንን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን እስቲ አምጡ።» በላቸው:: ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር:: የእነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን፤ የእነዚያንም በጌታቸው ሌላን የሚያስተካክሉ ሲሆኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ قُلۡ تَعَالَوۡاْ أَتۡلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمۡ عَلَيۡكُمۡۖ أَلَّا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗاۖ وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُم مِّنۡ إِمۡلَٰقٖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُكُمۡ وَإِيَّاهُمۡۖ وَلَا تَقۡرَبُواْ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَۖ وَلَا تَقۡتُلُواْ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
151. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ኑ ጌታችሁ በእናተ ላይ እርም ያደረገውን ነገርና (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ። እርሱም በአላህ ምንንም ነገር አታጋሩ:: ለወላጆቻችሁም በጎ ስራን ስሩ:: ልጆቻችሁንም ድህነትን ፈርታችሁ አትግደሉ:: እኛ እናንተንም ሆነ እነርሱን እንመግባችኋለንና:: ወደ ግልፅም ይሁን ድብቅ መጥፎ ስራ አትቅረቡ:: ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሀቅ ቢሆን እንጂ አትግደሉ:: ይሀችሁ! ታውቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ