Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ   អាយ៉ាត់:
فَإِذَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡحَسَنَةُ قَالُواْ لَنَا هَٰذِهِۦۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةٞ يَطَّيَّرُواْ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓۗ أَلَآ إِنَّمَا طَٰٓئِرُهُمۡ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ مَهۡمَا تَأۡتِنَا بِهِۦ مِنۡ ءَايَةٖ لِّتَسۡحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ
132. «በማንኛይቱም ተዓምር ልትደግምብን ብታመጣም የምናምንልህ አይደለንም።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلۡجَرَادَ وَٱلۡقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ وَٱلدَّمَ ءَايَٰتٖ مُّفَصَّلَٰتٖ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ
133. ወዲያዉም የውሃን ማጥለቅለቅ፤ አንበጣን፤ ቅማልን፤ እንቁራሪቶችን፤ ደምን፤ የተለያዩ ተዓምራት ሲሆኑ በእነርሱ ላይ ላክን:: እነርሱ ግን ኮሩም:: ተንኮለኞችም ህዝቦች ነበሩ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيۡهِمُ ٱلرِّجۡزُ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَۖ لَئِن كَشَفۡتَ عَنَّا ٱلرِّجۡزَ لَنُؤۡمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرۡسِلَنَّ مَعَكَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
134. በእነርሱ ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸውም ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ መሠረት ለምንልንና ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ላንተ እናምንልሀለን:: የኢስራኢልን ልጆችም ካንተ ጋር እንለቃለን።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُمُ ٱلرِّجۡزَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ هُم بَٰلِغُوهُ إِذَا هُمۡ يَنكُثُونَ
135. ለሚደርሱበት የተወሰነ ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነርሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን አፈረሱ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ
136. እነርሱም በተዓምራታችን ስላስተባበሉና ከእርሷ ዘንጊዎች ስለሆኑ ተበቀልናቸው:: በባህር ውስጥም አሰመጥናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِينَ كَانُواْ يُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَٰرِبَهَا ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ بِمَا صَبَرُواْۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ يَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُواْ يَعۡرِشُونَ
137. እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው:: መልዕክተኛችን ሆይ! የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች:: ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ