Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ   អាយ៉ាត់:
وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ غَضۡبَٰنَ أَسِفٗا قَالَ بِئۡسَمَا خَلَفۡتُمُونِي مِنۢ بَعۡدِيٓۖ أَعَجِلۡتُمۡ أَمۡرَ رَبِّكُمۡۖ وَأَلۡقَى ٱلۡأَلۡوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأۡسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُۥٓ إِلَيۡهِۚ قَالَ ٱبۡنَ أُمَّ إِنَّ ٱلۡقَوۡمَ ٱسۡتَضۡعَفُونِي وَكَادُواْ يَقۡتُلُونَنِي فَلَا تُشۡمِتۡ بِيَ ٱلۡأَعۡدَآءَ وَلَا تَجۡعَلۡنِي مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
150. ሙሳ እየተቆጣና እያዘነ ወደ ህዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «በእኔ ቦታ የተካችሁት ነገር ምንኛ ከፋ! የጌታችሁን ትዕዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸውና ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙን የራስ ጸጉር ወደ እርሱ እየጎተተው ያዘ:: ወንድሙም፡- «የእናቴ ልጅ ሆይ! ህዝቦቹ ናቁኝ ሊገድሉኝም ተቃረቡ:: ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ህዝቦችም ጋር አታድርገኝ።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَلِأَخِي وَأَدۡخِلۡنَا فِي رَحۡمَتِكَۖ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ
151. ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! ለኔም ለወንድሜም ማረን:: በእዝነትህ ውስጥም አስገባን። አንተም ከአዛኞቹ ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህና።» አለ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ ٱلۡعِجۡلَ سَيَنَالُهُمۡ غَضَبٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَذِلَّةٞ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُفۡتَرِينَ
152. እነዚያ ወይፈኑን አምላክ ያደረጉት ሰዎች ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ህይወት ውርደት ያገኛቸዋል:: ቀጣፊዎችን ልክ እንዲዚሁ እንቀጣለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ثُمَّ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِهَا وَءَامَنُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
153. እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም በኋላ የተጸጸቱና በአላህ ያመኑ ጌታህ ከእርሷ በኋላ መሀሪና አዛኝ ነው:: (ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى ٱلۡغَضَبُ أَخَذَ ٱلۡأَلۡوَاحَۖ وَفِي نُسۡخَتِهَا هُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ هُمۡ لِرَبِّهِمۡ يَرۡهَبُونَ
154. ሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን አነሳቸው:: በግልባጫቸውም ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ መምሪያና እዝነት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱخۡتَارَ مُوسَىٰ قَوۡمَهُۥ سَبۡعِينَ رَجُلٗا لِّمِيقَٰتِنَاۖ فَلَمَّآ أَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ قَالَ رَبِّ لَوۡ شِئۡتَ أَهۡلَكۡتَهُم مِّن قَبۡلُ وَإِيَّٰيَۖ أَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَّآۖ إِنۡ هِيَ إِلَّا فِتۡنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَآءُ وَتَهۡدِي مَن تَشَآءُۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَاۖ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡغَٰفِرِينَ
155. ሙሳም ከህዝቦቹ መካከል ለቀጠሯችን ሰባ ሰዎችን መረጠ:: ከዚያ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በደረሰባቸው ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! ብትፈልግ ኖሮ ከአሁን በፊት ባጠፋሀቸው ነበር:: እኔንም ባጠፋኸኝ ነበር:: ከእኛ መሀከል ቂሎቹ በሠሩት ጥፋት ታጠፋናለህን? ፈተናይቱ የአንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም:: በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ:: አንተ ረዳታችን ነህና:: ለእኛ ምህረት አድርግልን። እዘንልንም:: አንተ ከመሀሪዎች ሁሉ በላጭ ነህና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ