Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ   អាយ៉ាត់:
قَالَ ٱدۡخُلُواْ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِكُم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ فِي ٱلنَّارِۖ كُلَّمَا دَخَلَتۡ أُمَّةٞ لَّعَنَتۡ أُخۡتَهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُواْ فِيهَا جَمِيعٗا قَالَتۡ أُخۡرَىٰهُمۡ لِأُولَىٰهُمۡ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمۡ عَذَابٗا ضِعۡفٗا مِّنَ ٱلنَّارِۖ قَالَ لِكُلّٖ ضِعۡفٞ وَلَٰكِن لَّا تَعۡلَمُونَ
38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَتۡ أُولَىٰهُمۡ لِأُخۡرَىٰهُمۡ فَمَا كَانَ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلٖ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ
39. መጀመሪያይቱ ቡድንም ለኋለኛይቱ ቡድን «ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም ትላለች:: ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይሏቸዋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمۡ أَبۡوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلۡجَمَلُ فِي سَمِّ ٱلۡخِيَاطِۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُجۡرِمِينَ
40. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉና ከእርሷም የኮሩ ሁሉ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸዉም:: ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስም ወደ ገነት አይገቡም:: ልክ እንደዚሁ አመጸኞችን እንቀጣለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٞ وَمِن فَوۡقِهِمۡ غَوَاشٖۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّٰلِمِينَ
41. ለእነርሱም በሥራቸው ምክንያት ከገሀነም እሳት ምንጣፍ ከበላያቸዉም የእሳት መሸፈኛዎች አሉባቸው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
42. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካሞችን የሰሩ ማንኛውንም ነፍስ የችሎታዋን እንጂ አናስገድድም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلّٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهۡتَدِيَ لَوۡلَآ أَنۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُۖ لَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّۖ وَنُودُوٓاْ أَن تِلۡكُمُ ٱلۡجَنَّةُ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាក់រ៉ហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ