Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್   ಶ್ಲೋಕ:

አን-ኒሳዕ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ وَخَلَقَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا وَبَثَّ مِنۡهُمَا رِجَالٗا كَثِيرٗا وَنِسَآءٗۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِي تَسَآءَلُونَ بِهِۦ وَٱلۡأَرۡحَامَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيۡكُمۡ رَقِيبٗا
1. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን፤ ከእርሷም መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውንና ከሁለቱም ብዙ ወንዶችንና ብዙ ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን (ከሚያስቆጡ) ተግባራትና ዝምድናዎችን (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ:: አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَءَاتُواْ ٱلۡيَتَٰمَىٰٓ أَمۡوَٰلَهُمۡۖ وَلَا تَتَبَدَّلُواْ ٱلۡخَبِيثَ بِٱلطَّيِّبِۖ وَلَا تَأۡكُلُوٓاْ أَمۡوَٰلَهُمۡ إِلَىٰٓ أَمۡوَٰلِكُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ حُوبٗا كَبِيرٗا
(እናንተ ኑዛዜ ተቀባዮች ሆይ! ) ለየቲሞች ገንዘቦቻቸውን ስጡ:: (ከመሀከሉም) መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ ገንዘቦቻችሁ (በመቀላቀል) አትብሉ:: እርሱ ትልቅ ኃጢአት ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَإِنۡ خِفۡتُمۡ أَلَّا تُقۡسِطُواْ فِي ٱلۡيَتَٰمَىٰ فَٱنكِحُواْ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثۡنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَۖ فَإِنۡ خِفۡتُمۡ أَلَّا تَعۡدِلُواْ فَوَٰحِدَةً أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۚ ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُواْ
3. (እናንተ ሙስሊም ወንዶች ሆይ) በናንተ ስር ያሉት ሴት የቲሞችን በማግባታችሁ አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ከሴቶች መካከል ለእናንተ የመረጣችሁትን (ደስ ያሏችሁን) ሁለት ሁለት ሶስት ሶስትና አራት አራት አግቡ:: በሚስቶች መካከል አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ግን አንዲትን ሴት ብቻ ወይም ንብረታችሁ የሆኑት ሴት ባሪያዎችን ብቻ (በሚስትነት) ያዙ:: ይህም (ሴትን ልጅ) እንዳትበድሉ በጣም የቀረበ ተግባር ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَءَاتُواْ ٱلنِّسَآءَ صَدُقَٰتِهِنَّ نِحۡلَةٗۚ فَإِن طِبۡنَ لَكُمۡ عَن شَيۡءٖ مِّنۡهُ نَفۡسٗا فَكُلُوهُ هَنِيٓـٔٗا مَّرِيٓـٔٗا
4. ለሴቶች መህሮቻቸውን ደስተኞች ሆናችሁ ስጧቸው። ለእናንተ ከእርሱ የተወሰነን ነገር ራሳቸው ቢለግሱላችሁ ግን በእርካታና በምቾት ሆናችሁ ብሉት (ተጠቀሙበት)።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلَا تُؤۡتُواْ ٱلسُّفَهَآءَ أَمۡوَٰلَكُمُ ٱلَّتِي جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمۡ قِيَٰمٗا وَٱرۡزُقُوهُمۡ فِيهَا وَٱكۡسُوهُمۡ وَقُولُواْ لَهُمۡ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗا
5. (ኃላፊዎች ሆይ!) ያን አላህ ለእናንተ መቋቋሚያ (መጠቃቀሚያ) ያደረገላችሁን ገንዘባችሁን (የያዛችሁላቸውን) ለቂሎች (ለአዕምሮ ደካሞች) አትስጧቸው:: ከእርሷም መግቧቸው:: ከእርሷ አልብሷቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ንግግር ተናገሯቸው።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱبۡتَلُواْ ٱلۡيَتَٰمَىٰ حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغُواْ ٱلنِّكَاحَ فَإِنۡ ءَانَسۡتُم مِّنۡهُمۡ رُشۡدٗا فَٱدۡفَعُوٓاْ إِلَيۡهِمۡ أَمۡوَٰلَهُمۡۖ وَلَا تَأۡكُلُوهَآ إِسۡرَافٗا وَبِدَارًا أَن يَكۡبَرُواْۚ وَمَن كَانَ غَنِيّٗا فَلۡيَسۡتَعۡفِفۡۖ وَمَن كَانَ فَقِيرٗا فَلۡيَأۡكُلۡ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِذَا دَفَعۡتُمۡ إِلَيۡهِمۡ أَمۡوَٰلَهُمۡ فَأَشۡهِدُواْ عَلَيۡهِمۡۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبٗا
6. (ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው:: ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው:: በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው:: (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል:: ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ:: በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ