Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್   ಶ್ಲೋಕ:
وَٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيۡكُمۡ وَيُرِيدُ ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلشَّهَوَٰتِ أَن تَمِيلُواْ مَيۡلًا عَظِيمٗا
27. አላህ በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚከተሉ ግን ከእውነት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُخَفِّفَ عَنكُمۡۚ وَخُلِقَ ٱلۡإِنسَٰنُ ضَعِيفٗا
28. አላህ ከናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል። ሰው ደካማ ሆኖ የተፈጠረ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَأۡكُلُوٓاْ أَمۡوَٰلَكُم بَيۡنَكُم بِٱلۡبَٰطِلِ إِلَّآ أَن تَكُونَ تِجَٰرَةً عَن تَرَاضٖ مِّنكُمۡۚ وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَنفُسَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُمۡ رَحِيمٗا
29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ:: በእናንተ መካከል በመስማማት የሆነችውን ንግድ ካልሆነች በስተቀር (እሷን ግን ብሉ) :: ነፍሶቻችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ عُدۡوَٰنٗا وَظُلۡمٗا فَسَوۡفَ نُصۡلِيهِ نَارٗاۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا
30. ወሰን በማለፍ እና በመበደል ይህን የሰራ ሁሉ እሳት እናስገባዋለን:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነውና።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
إِن تَجۡتَنِبُواْ كَبَآئِرَ مَا تُنۡهَوۡنَ عَنۡهُ نُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَنُدۡخِلۡكُم مُّدۡخَلٗا كَرِيمٗا
31. ትክክለኛ አማኞች ሆይ! ከተከለከላችሁት ወንጀሎች መካክል ታላላቆችን ብትርቁ ትናንሽ ኃጢአቶቻችሁን እናብስላችኋለን:: የተከበረውንም መግቢያ (ገነት) እናስገባችኋለን::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلَا تَتَمَنَّوۡاْ مَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بِهِۦ بَعۡضَكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٞ مِّمَّا ٱكۡتَسَبُواْۖ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٞ مِّمَّا ٱكۡتَسَبۡنَۚ وَسۡـَٔلُواْ ٱللَّهَ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا
32. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ:: ለወንዶችም ከሰሩት ስራ እድል አለላቸው:: ለሴቶችም ከሰሩት ስራ እንዲሁ እድል አለላቸው:: አላህን ከችሮታው ለምኑት:: አላህ በሁሉ ነገር አዋቂ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلِكُلّٖ جَعَلۡنَا مَوَٰلِيَ مِمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَۚ وَٱلَّذِينَ عَقَدَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡ فَـَٔاتُوهُمۡ نَصِيبَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدًا
33. ለሁላችሁም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ሀብት ወራሾችን አድርገናል:: እነዚያንም (ለመረዳዳትና ለመዋረስ) በመሐላዎቻችሁ የተዋዋላችኋቸውን (ከስድስት አንድ) ድርሻቸውን ስጧቸው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ (መስካሪ) ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ