Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್   ಶ್ಲೋಕ:
لَّا يَسۡتَوِي ٱلۡقَٰعِدُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ غَيۡرُ أُوْلِي ٱلضَّرَرِ وَٱلۡمُجَٰهِدُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۚ فَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ عَلَى ٱلۡقَٰعِدِينَ دَرَجَةٗۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَفَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ عَلَى ٱلۡقَٰعِدِينَ أَجۡرًا عَظِيمٗا
95. ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም:: በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ:: ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ):: ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
دَرَجَٰتٖ مِّنۡهُ وَمَغۡفِرَةٗ وَرَحۡمَةٗۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمًا
96. ከእርሱ ዘንድ በሆኑ ደረጃዎች አበለጠ:: ምህረትንም አደረገ:: እዝነትንም አዘነላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِيٓ أَنفُسِهِمۡ قَالُواْ فِيمَ كُنتُمۡۖ قَالُواْ كُنَّا مُسۡتَضۡعَفِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ قَالُوٓاْ أَلَمۡ تَكُنۡ أَرۡضُ ٱللَّهِ وَٰسِعَةٗ فَتُهَاجِرُواْ فِيهَاۚ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا
97. እነዚያ ለእምነት ሲሉ ባለመሰደድ ነፍሶቻቸውን በዳዮች ሆነው መላዕክት የገደሏቸው መላዕክት ለእነርሱ «በምን ነገር ላይ ነበራችሁ?» ይሏቸዋል። «በምድር ውስጥ ደካሞች ነበርን።» ይላሉ:: «የአላህ ምድር ትሰደዱባት ዘንድ ሰፊ አልነበረችምን?» ይሏቸዋል። እነዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
إِلَّا ٱلۡمُسۡتَضۡعَفِينَ مِنَ ٱلرِّجَالِ وَٱلنِّسَآءِ وَٱلۡوِلۡدَٰنِ لَا يَسۡتَطِيعُونَ حِيلَةٗ وَلَا يَهۡتَدُونَ سَبِيلٗا
98. ከወንዶችና ከሴቶች ከህፃኖችም ሲሆኑ ከሀገራቸው ለመውጣት መላን የማይችሉና መንገድንም የማይመሩ ደካሞች ባለመሰደዳቸው ግን ምንም ቅጣት የለባቸዉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَأُوْلَٰٓئِكَ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَعۡفُوَ عَنۡهُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَفُوًّا غَفُورٗا
99. እነዚያ አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል:: አላህም ይቅር ባይና መሀሪ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
۞ وَمَن يُهَاجِرۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ يَجِدۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُرَٰغَمٗا كَثِيرٗا وَسَعَةٗۚ وَمَن يَخۡرُجۡ مِنۢ بَيۡتِهِۦ مُهَاجِرًا إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ يُدۡرِكۡهُ ٱلۡمَوۡتُ فَقَدۡ وَقَعَ أَجۡرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
100. በአላህ መንገድ የሚሰደድ ሁሉ በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል:: ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ስደተኛ ሆኖ ከቤቱ የሚወጣና ከዚያ በመንገድ ላይ ሞት የሚያገኘው ምንዳው በእርግጥ በአላህ ዘንድ ተረጋገጠ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَإِذَا ضَرَبۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَلَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٌ أَن تَقۡصُرُواْ مِنَ ٱلصَّلَوٰةِ إِنۡ خِفۡتُمۡ أَن يَفۡتِنَكُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْۚ إِنَّ ٱلۡكَٰفِرِينَ كَانُواْ لَكُمۡ عَدُوّٗا مُّبِينٗا
101.(አማኞች) በምድር ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ሊያውኳችሁ እንደሆነ ብትፈሩ ከሶላቶች መካከል ከፊሎችን (ባለ አራት አራት ረካአ የሆኑትን ቁጥራቸውን ወደ ሁለት ሁለት በመቀነስ) ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም። ከሓዲያን ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅನ್ನಿಸಾಅ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ